Home » Sunday sermon – December 15, 2024

በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ

Last updated on December 15, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

የእግዚአብሔር ልጅነት

የንባብ ክፍል:- ሮሜ 8: 12-16

ዓላማ

- በእምነት የፀደቁ የእግዚአብሔር ልጆች የስጋን ስራ የመግደል ሀላፊነት አለባቸው።
- በእምነት የፀደቁ የእግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔር አብን አባት ብለው መጥራት. ይችላሉ።
- በእምነት የፀደቁ የእግዚአብሔር ልጆች የእግዚአብሔር ውራሾች ናቸው።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት እንደተመለከትነው በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉ ሁሉ አሁን ኩነኔ የለባቸውም። በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የህይወት መንፈስ ህግ ከኃጢአትና ከሞት ህግ አርነት አውጥቶአቸዋልና።በዛሬው ትምህርት ደግሞ በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅና የእግዚአብሔር ልጅነትን ልክ እንመለከታለን።

1: የእግዚአብሔር ልጆች ዕዳ አለባቸው። ሮሜ 8;12-13

1:1 እንድ ስጋ ፈቃድ ያለመኖር ዕዳ አለባቸው።
1:2 የስጋን ስራ በመንፈስ የመግደል ዕዳ አለባቸው።

2: የእግዚአብሔር ልጆች ምልልስ ።ሮሜ 8:14-16

2:1 በእግዚአብሔር መንፈስ ይመራሉ።
2:2 እግዚአብሔር አብን አባት ብለው መጥራት ይችላሉ።
2:3 መንፈስ ቅዱስ ልጅነታቸውን ያረጋግጥላቸዋል።

3: የእግዚአብሔር ልጆች የእግዚአብሔር ወራሾች ናቸው። ሮሜ 8:17

3:1 የእግዚአብሔር ወራሽነት የልጅነት መብታቸው ነው።
3:2 ከክርስቶስ ጋር ጋር ይከብራሉ።
3:3 ከክርስቶስ ጋር አብረው ይወርሳሉ።

ማጠቃለያ

በወንጌል የተግለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት የተቀብሉ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ። ልጆች የሆኑ ሁሉ የስጋን ስራ በመንፈስ የመግደል እዳቸውን ይወጣሉ።ደግሞም በእግዚአብሔር ልጅነታቸው ልክ ይመላለሳሉ።
በዚህ ልክ ልጆች ስለሆኑ ከክርስቶስ ጋር አብረው የእግዚአብሔር ወራሾች ይሆናሉ።በወንጌል የገለጠውን የእግዚአብሔር
ፅድቅ በእምነት ተቀብለዋልና።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.