Home » Sunday sermon – January 5, 2025

በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅና ዘላለማዊዉ አላማ

Last updated on January 5, 2025 - by Pastor Tariku Eshetu

የንባብ ክፍል:- ሮሜ 8:28- 31

ዓላማ

- ዘላለማዊውን የእግዚአብሔር ዓላማ ማወቅ ላዛሬው ህይወታችን እስፈላጊ መሆኑን ማሳሰብ።
- እግዚአብሔር ከዘላለማዊ አላማው አንፃር በህይወታችን እየሰራ መሆኑን ማሳሰብ ነው።
- የእግዚአብሔር ዘላለማዊ አላማ የጠራቸውንና ያፀደቃቸውን ማክበር መሆኑን ማሳሰብ ነው።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት ለማየት እንደሞከርነው በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት የተቀበሉ አማኞች በክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ቢሆኑም ሊገለጥላቸው ያለው ክብር ታላቅ እንደሆነና የመንፈስ ቅድስን ድርሻ ተመልክተናል ። በዛሬው ትምህርት ደግሞ በወንጌል የተግለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅና ዘላለማዊው አላማው ያላቸውን ግንኙነት እንመለከታለን።

1: ዘላለማዊው እግዚአብሔር በዛሬው ህይወታችን

1:1 እግዚአብሔር ዛሬም እየሰራ ነው።
1:2 እግዚአብሔር በጎን/መልካምን እየሰራ ነው።
1:3 እግዚአብሔር በነገሮች ሁሉ ውስጥ እየሰራ ነው።
14 ከዘላለማዊ አላማው አንፃር እየሰራ ነው።

2: ዘላለማ የእግዚአብሔር ዓላማ ምንድ ነው።

2:1 ዘላለማዊ እውቀቱን መገለጥ።
2:2 የልጁን መልክ እንድንመስል መወሰን።
2:3 በዚህ ውሳኔ መሰረት ሰወችን መጥራት።
2:4 በዚህ ውሳኔ መሰረት ሰወችን ማፅደቅ።
2:5 በዚህ ውሳኔ መሰረት የፀደቁትን ማክበር።

ማጠቃለያ

በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት የተቀበሉ ሁሉ ከእግዚአብሔር ዘላለማዊ አላማ ጋር ተገናኝተዋል።ስለዚህ መጨረሻቸው የልጁን መልክ በመምሰል መክበር ነው።ይህን እውነት የተረዱ ሁሉ ዛሬ እግዚአብሔር በሕይወታቸው ከዘላለማዊ አላማው አንፃር እየሰራ መሆኑን መገንዘብና የልጁን መልክ በመምስል ወዳለው ክብር በእምነት መርዝ ይገባቸዋል።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.