ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ለመተዋወቅ ልናደርገው የሚገባን ምንድ ነው የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ባለፈው ሳምንት የእግዚአብሔርን ቃል ማሰላሰልና በፀሎት የመትጋትን አስፈላጊነት ተመልክተን ነበር።በዛሬው ትምህርት ደግሞ የአምልኮና የምስጋና ድባብን የማሳደግ አስፈላጊነትን እንመለከታለን።
1:1 ትርጉም/ብይን:- እግዚአብሔርን በማንነቱ ማምለክና ልብን ለእርሱ አሳልፎ መስጠት ነው። 1:2 መዝሙሮችን መዘመር ብቻ ሳይሆን እርሱን በመታዘዝ፣በማክበር እና በመውደድ መኖር ነው። 1:3 የምናደርገውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር ማድረጋችንን እርግጠኛ መሆን ነው። 1:4 አምልኮ በመንፈስ መመራትና በእውነት የተሞላ መሆን አለበት። 1:5 አምልኮ ነፍስን ለእግዚአብሔር መስዋእት አድርጎ መስጠት ነው። 1:6 አምልኮ ለእግዚአብሔር የማያቋርጥ የምስጋና መስዋዕት ማቅረብ ነው።
2:1 መዝሙር መዘመር። መዝ 95:1-2,ኤፌ5:19;መዝ 100:4-5 2:2 ሁል ጊዜ ሰለ ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን 2:3 ለቸርነቱ፣ለታማኝነቱና ለኃይሉ እግዚአብሔርን ማክበር።
3:1 መንፈስ ቅዱስ ይናገራል 3:2 ሰውች ለአገልግሎት በቤ/ክ ይለያሉ 3:3 ሰወች በመንፈስ ቅዱስ ለወንጌል ይላካሉ።
አማኞች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በጥልቀት ሊተዋወቁ እንደሚገባቸው የአዲስ ኪዳን ትምህርት ነው። ያለእርሱ አማኞች ምንም መሆንም ማድርግም አይችሉምና። ስለዚህ በመንፈስ ቅዱስ ጋር በጥልቀት ለመተዋወቅ የአምልኮና የምስጋና ድባብ በመካከላችን ሊኖር ይገባል። ለዝህም እያንዳንዱ አማኝ የአምልኮን ምንነት ማውቅ፣ የአምልኮን መገለጫዎች ማወቅና ማምለክ እንዲሁም በአምልኮ ውስጥ ለሚመጣው የመንፈስ ቅዱስ ድምፅ መታዛዝ ያስፈልገዋል።ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ለመተዋወቅ የአምልኮና የምስጋናን ድባብ እናሳድግ!!!!!!!!!!!!
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.