አማኞች ለተቀበሉት ጥሪ የሚመጥን ኑሮ እንዲኖሩ ማሳሰብ። አማኞች የአገልግሎት ስጦታዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታት። አማኞች ለመንፈሳዊ እድገት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ማሳሰብ።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ደብዳቤው የመጀመሪያ ክፍል ላይ ነገረ ድህነትን በተመለከት ዝርዝር ጉዳዮችን ከፃፈ በኃላ፣ በቀጣይነት ለዳነው ሰው እንዲህ ብሎ ጥሪ ያቀርባል “ለተቀበላችሁት ጥሪ ተገቢውን ኑሮ እንድትኖር እለምናለሁ” የሚል ተማፅኖን ያሰማል። በቀጣይነትም እንዴት መኖር እንደሚገባ ዝርዝር ትምህርት ያስተምራል ከነዚህ ትምህርቶች የወሰኑትን በዚህ ጊዜ እንመለከታለን።
1:1:1 ለዚህ ኑሮ የጠራን ጌታ ነው። 1:1:2 ጥሪው እኛ ጋር እንዲደርስ ዋጋ ተከፍሎበታል። 1:1:3 ጥሪው ትሁት፣የዋህና ታጋሽ መሆን ይጠይቃል።
1:2:1 ውደ አንድ ተስፋ ስለተጠራን። 1:2:2 አንድ አካል ስለተደርግን። 1:2:3 በሁላችን ውስጥ አንድ መንፈስ ስላለ። 1:2:4 የሁላችን ጌታ አንድ ስለሆነ። 1:2:5 አንድ እምነትና አንድ ጥምቀት ስላለን። 1:2:6 በሁላችን የሚሰራ አንድ አባት ስላለን።
2:1 የክርስቶስ ሞት፣መቅበር፣መነሳትና መክበር ውጤቶች ስለሆኑ። 2:1 ስጦታዎች የተስጡት በአላማና በምክንያት ስለሆነ። 2:3 የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማውቅ ወደሚገኘው አንድነት ስለሚያደርሱን።
3:1 ለልዩ ልዩ የትምህርት ነፋስ እንዳንጋለጥ። 3:2 በሰወች ረቂቅ ተንኮል እንዳንታለል። 3:3 እውነትን በፍቅር መናገር እንድንችል። 3:4 በነገር ሁሉ ወደ ክርስቶስ ለማደግ። 3:5 እርስ በርስ ተያይዘን ለመስራትና በፍቅር እንድናድግ።
ክርስትና አንድ የታወቀ የሀይማኖት መሪ የመሰረተው ሀይማኖት አይደለም።ነገር ግን እግዚአብሔር በልጁ ሞት፣ መቀበር፣መነሳትና መክብር ምክንያት ሰወች የኃጢአት ይቅርታ እንዲቀበሉ ለቀረበላቸው አምላካዊ ጥሪ በእምነት ምላሽ የሰጡ ሰወች አንድነት እንጂ። ስለዚህ ይህን ጥሪ የተቀበሉ ሁሉ ደግሞ ለጥሪው የሚመጥን ኑሮ እንዲኖሩ ግዴታ አለባቸው። ስለዚህ ለጥሪያችን የሚመጥነውን ኑሮ በቃሉ መስፈርት እኑር።
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.