Home » Sunday sermon – May 25, 2025

ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ማወቅ አለብን!!!

Last updated on May 25, 2025 - by Pastor Tariku Eshetu

ንባብ 1ቆሮ 12:1-31

ዓላማ

- አማኞች ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ማወቅ አስፈላጊያቸው እንደሆነ ማሳሰብ።
- ቤተክርስቲያንና መንፈሳዊ ስጦታዎች ያላቸውን ግንኙነት ማስገንዘብ።
- ቤተክርስቲያን እስካለች የፀጋ ስጦታዎች መስራት እንደማያቆሙ ማረጋገጥ።

መግቢያ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፃፋቸው መልእክቶቹ አማኞች ስለ ሶስት ነግሮች እውቀት አልባ መሆን እንደማይገባቸው አሳስቦአል።እርሱም በሮሜ 11:25 ከህዝበ እስራኤል ጋር የተያያዘውን የእግዚአብሔር ዘላለማዊ እቅድ በተመለከተ፣1ተሰ 4:13 ደግሞ ስለ ጌታችን ስለኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ምፀአት በተመለከተ እና በዚህ 1ቆሮ 12:1 ደግሞ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተመለከተ ነው ። ስለዚህ እኛም ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ልናውቅ የሚገቡንን እውነቶች ከተጠቀሰው ምንባብ የሚከተሉትን እውነቶች እንመለክታለን።

1: መንፈሳዊ ስጦታዎች የመንፈስ ቅዱስ መናገሪያዎች ናቸው።1ቆሮ 12:1-3

1:1: እግዚአብሔር ከጦዖታት እንደሚለይ ያረጋግጣሉ።
1:2: መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስን ጌትነት ያርጋግጥባቸዋል።

2: መንፈሳዊ ስጦታዎች የመንፈስ ቅዱስ መገለጫዎች ናቸ። 1ቆሮ 12:4-11

2:1 ልዩ ልዩ ናቸው የሚገልጡት መንፈስ አንድ ነው።
2:2 አገልግሎታቸው ልዩ ልዩ ነው የሚያገለግሉት አንድ ጌታ ነው።
2:3 አስራራቸው ልዩ ልዩ ነው በሁሉም የሚሰራው አንዱ እግዚአብሔር ነው።
2:4 ለአማኞች በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የሚሰጡ ናቸው።

3: የቤተክርስቲያን ማንነትና መንፈስዊ ስጦታዎች 1ቆሮ 12: 12-31

3:1 የቤተክርስቲያን ማንነት 1ቆሮ12:12-26

3:1:1 በአንዱ መንፈስ አንድ አካል የተደርገች ነች።
3:1:2 አንዱን መንፈስ የጠጣች ነች።
3:1:3 ልዩ ልዩ ብልቶች ግን አንድ አካል ነች።
3:1:4 የሁሉም ብልቶች ሚና እኩል የሆነበት የክርስቶስ አካል ናት።
3:1:5 ስሜትን መጋራት ያለባት የክርስቶስ አካል ናች።

3:2 መንፈሳዊ ስጦታውችና ቤተክርስቲያን 1ቆሮ12:27-31

3:2:1 መንፈሳዊ ስጦታዎች እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ውስጥ ያደረጋቸው ናቸው።
3:2:1 መንፈሳዊ ስጦታዎች በልዩ ልዩ መንግድ በቤተክርስቲያን ውስጥ ይሰራሉ።
3:2:2 ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ስጦታን በብርቱ መፈልግ ይገባታል።
3:2:3 ቤተክርስቲያን የሚበልጠው መንገድ ልታውቅ ይገባታል።

ማጠቃለያ

ቅዱስ ቃሉ እንደሚያስተምረው ቤተክርስቲያን ድርጅት ብቻ ሳትሆን ህያው የሆኑ እና ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስጦታን ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበሉ ብልቶች ያሉባት የክርስቶስ አካል ናት። ስለዚህ እግዚአብሔር አሁን በርሷ በኩል ይናገራል። በሆኑም በዚህች ህያው ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሁሉ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ሊያውቁና ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበሉትን መንፈሳዊ ስጦታ ሊለማመዱ እንዲችሉ ስለ መንፈሳዊ ስጦታዎች ማወቅ ይገባቸዋል። ስለመንፈሳዊ ስጦታዎች ምን ያህል ያውቃሉ?

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.