Home » Sunday sermon – June 1, 2025

ባመናችሁ ጌዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን???

Last updated on June 1, 2025 - by Pastor Tariku Eshetu

ዓላማ

- መንፈስ ቅዱስን መቀበል የእውነተኛ እምነት ማስረጃ መሆኑን ማመላከት።
- መንፈስ ቅዱስን መቀበላችን ማስረጃው የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መቀበል መሆኑን ማመላከት።
- መንፈስ ቅዱስን መቅበል የሚያስፈልግበትን መሰረታዊ ምክንያት ማመላከት።

መግቢያ

ጌታችን ኢየሱስ የአይሁድ የዳስ በዓል በሚከበርበትና ከበዓሉም ታላቁ በተባለው ቅን ላይ ድምፁን ከፍ አድርጎ በመጮህ ”ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ” በማለት በርሱ ለሚያምኑት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን የመቀበል ጥሪ አቀረበ። ለዚህ ጥሪ ምላሽ የሰጡና መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን እንዴት እንደተቀበሉ ፍለጋቸውን እንዴት መከተል እንደሚገባን በዚህ ትምህርት እንመለከታለን።

1: ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ምን አረጉ?

1:1 የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሳኤ በቃሉ መሰረት አመኑ። ሉቃ 24:36-45,ሐዋ 1:1-3
1:2 ንስሀና የኃጢአት ስርየት በስሙ እንደሆነ ለመመስከር ወሰኑ።ሉቃ 24:47 ሐዋ 1:8
1:3 የእግዚአብሔርን መንግስት በመረዳት ተቀበሉ። ሐዋ 1:3

2: ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን እንዴት ተቀበሉ?

2:1: መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል በትጋት ፀለዩ። ሉቃ 24:49; ሐዋ 1:5; 14
2:2 በቃሉ መሰረት መስተካከል ያለበትን አስተካከሉ። ሐዋ 1:15-26
2:3 በአንድ ልብ አንድ ላይ ሆነው ጠበቁት።ሐዋ 2:1-2::

3: ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉ ምን ሆነ? ሐዋ 1:3-4

3:1 ከሰማይ ድምፅ መጣ የነበሩበትን ቤት ሞላው።
3:2 ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።
3:3 መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታን ሰጣቸው።
3:4 መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸውን ስጦታ መለማመድ ጀመሩ።

ማጠቃለያ

ጌታችን ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስን የመቀበልን ጥሪ ለአማኝ ሁሉ ነው ያቀረበው።ስለዚህ ሐዋርያት የተቀበሉትን መንፈስ ለመቀበል ትንሳኤውን በቃሉ ልክ እንመን፣ምስክሮቹ ለመሆን እንወስን፣መንግስቱን በቃሉ ልክ እንረዳና እንቀበል፣ በተስፋው ቃል መስፈርት እስክንቀበል ድረስ ተግተን እንፀልይ ጊዜ ስጥተን የእርሱን መገኘት እንፈልግ።እርሱም በቃሉ የታመነ ስለሆነ ይመጣል ስጦታንም ይሰጠናል። ስጦታንም ስንቀበል በእምነት እንልማመድ። ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን ለሚለው ጥያቄ በጥቅስ ብቻ ሳይሆን በተግባር ምላሽ እንስጥ።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.