- መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንደምንችል በቃሉ ማረጋገጥ። - መንፈስ ቅዱስን የመቀበል የመጀመሪያን ገፅታ ማመላከት - መንፈስ ቅዱስን የመቀበላችን የመጀመሪያ ገፅታ ውጤት ምን እንደሆነ በቃሉ ማረጋገጥ።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን ላገኛቸው የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ያቀረበላቸው ጥያቄ ከየት ቤተ እምነት ናችሁ የሚል ሳይሆን ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን? የሚል ነበር ። የጥያቄው ምክንያቶች ሁለት ነበሩ የመጀመሪያው የእውነተኛ አማኝነት ማስረጃ መንፈስ ቅዱስን መቀበል መሆኑና ሌላው ደግሞ መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ለመርዳት ነበር። በዚህ መሰረት እኛም በዚህ ዘመን መንፈስ ቅዱስን መቅበል እንደምንችል የሚያረጋግጥልን የቃሉን እውነትና መንፈስ ቅዱስን የመቀበል የመጀሪያ ገፅታ ከነውጤቱ በዚህ ትምህርት እንመለከታለን
1:1 በመጨረሻው ዘመን ውስጥ መህኖራችን።ት° ኢዩ 2:28-29ሐዋ2:17። 1:2 ጌታችን የሰጠው ተስፋ መፀም። ዮሐ 7:37-39,ሐዋ 2:32-33 1:3 የተስፋው ቃል በሩቅ ያሉትን ሁሉ ማጠቃለሉ።ሐዋ 2:38-39
2:1 የዳግም ልደት የግሪክ ቃል ትርጉም “ፓሊንግኔዥያ” “አዲስ ልደት” ወይም “መታደስ “የሚል ነው። 2:2 የዳግም ልደት መፀሐፍ ቅደሳዊ ትርጉም:- የእግዚአብሔር ፍቅርና ምህረት በመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ነው። ቲቶ3:5 2:3 ከሙትነት ወደ ህያወነት መለወጥ ነው። ኤፌ 2:1-5 2:4 የድነት የመጀመሪያው ልምምድ ነው። ዮሐ3:3-5
3:1 የሰው ልብ ይለወጣል ህዝብ 36:25-27 3:2 መንፈሳዊ ሕያውነት ይከሰታል ኤፌ 2:5 3:3 መንፈስ ቅዱስ በአማኙ ውስጥ ያድራል። ዮሐ14:15-17 1ቆሮ 6:19 3:4 የአማኙ ድነት የተረጋገጠ ይሆናል። ኤፌ1:13-14 3:5 የአማኙ ውስጣዊ ማንነትና ተፈጥሮ ይቀይራል።2ቆሮ 5:17
ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን በማለት ሐዋርያው የጠየቀውን ጥያቄ ዛሬ ብንጠየቅ መልሳችን ምን ይሆን? የምናቀርበውስ ማስረጃ ምንድ ነው?ቅዱስ ቃሉ እንደሚለው መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ዳግም ተወዶል። ዳግም የተወለደም መንፈስ ቅዱስን ተቀብሏል።መንፈስ ቅዱስን የተቀበለ ድግሞ ለዘላለም ድኗል። የዳነ ሁሉ መንፈሳዊ ስጦታን ተቀብሏል። ስለዚ ዛሬ መንፈስ ቅዱስ በነዚህ ሶጧታዎች እራሱን ይገልጣል ቤተክርስቲያንን ያንፃል። ባመናችሁ ጌዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን?
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.