ትምህርት ሶስት፦ የመንግስቱን መርሆዎች ማውቅ
ዓላማ
-በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለመኖር የመንግስቱን መርህ የማወቅ አስፈላጊነትን ማሳሰብ።
- የመንግስቱን መርህ ምንነት ማውቅ ተግቢውን የህይወት ስርዓት ለመምራት እንደሚያስችል ማመላክት።
- አማኞች እንደ እግዚአብሔር መንግስት ዜጋ እንዲኖሩ ማበረታታት።
መግቢያ
የእግዚአብሔርን መንግሥት መርሆች ማወቅ ለእያንዳንዱ አማኝ በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በሚስማማ መንገድ እንድናስብ ፣ እንድንኖር፣ እና እንድናገለግል ህይወታችንን ስለሚቀርጽው።ከዚህ እውነት አንጻር የመንግስቱን መርህ ማውቅ አስፈላጊ የሆነበትን መጸህፍ ቅዱሳዊ ቁልፍ ምክንያቶችን በዚህ ትምህርት እንመለከታልን።
1. የእግዚአብሔርን ፈቃድ እና መንገዶች መረዳት
እንደ ጽድቅ፣ ፍትህ፣ ፍቅር፣ ትህትና፣ እምነት እና ታዛዥነት ያሉ የእግዚአብሔር መንግስት መርሆዎች የእግዚአብሔርን ተፈጥሮ እና ከህዝቡ የሚጠብቀውን መላሽ ይገልጣሉ። እነዚህን ማወቃችን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር እንድንራመድ ይረዳናል (ሮሜ 12፡2)።
2. የመንግሥቱ ዜጎች ሆነን ለመኖር
ጌታችን ኢየሱስ “የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች” (ማር. 1፡15)ብሎናል ። ይህ ማለት መንግሥተ ሰማይን እየጠበቅን ብቻ አይደለም ማለት ነው። ስለሆንም የተጠራነው እንደ መንግሥት ዜጎች እንድንኖር ነው። መርሆቹን መረዳታችን ደግሞ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንድንወክል ይረዳናል (ፊልጵስዩስ 3፡20)።
3. መንፈሳዊ እድገት እና ብስለትን ያስገኝልናል።
የመንግሥቱን መሠረታዊ መርህ ማወቅ ወደ መንፈሳዊ እድገት ይመራናል። ኢየሱስ በማቴዎስ 6፡33 ላይ “አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ...”ብሎናል። ይህ ማለት ወደ ጥልቅ እምነት፣ በተልወጠ ባህርይ እና በአላማችን ላይ ትኩረት ማድረግ ነው።
4. ውጤታማ አገልግሎት እና ምስክርነት እንዲኖረ ያደርጋል
ወንጌልን ለማካፈልና በብቃት ለማገልገል በመጀመሪያ የምንወክለውን መንግሥት ማለትም እውነትን፣ ምሕረትን፣ አገልግሎትንና ቅድስናን ማወቅ አለብን። ይህ ለምስክርነታችን ትክክለኛነትን ያመጣል (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡20)።
5. በዓለም ስርዓቶች ላይ ድልን ያስገኝልናል።
የእግዚአብሔር መንግሥት የሚሠራው ከዓለም በተለየ ሁኔታ በትሕትና፣ በፍቅር እና በይቅርታ ነው። እነዚህን መርሆች መረዳታችን ዓለምን ለማሸነፍ ኃይል ይሰጠናል (ዮሐንስ 18፡36፤ 1 ዮሐንስ 5፡4)።
ማጠቃለያ
በአጠቃላይ የእግዚአብሔርን መንግሥት መርሆች ማወቅ አማኞች በዓላማ እንዲኖሩ፣ ክርስቶስን በታማኝነት እንዲያንጸባርቁ ፣ ከስህተት ትምህርትና አሰራር እዲያመልጡ እና ለሚመጣው ንግሥና/የእግዚአብሔር መንግስት ፍጻሜ እንዲዘጋጁ ኃይል ይሰጣቸዋል። ስለዚህ የመንግስቱ መርህ ማወቅ ለአማኝ ወሳኝ ነው የምንለ ለዚህ ነው። ስለዚህ የመንግስቱን መርህ እንወቅ።
Source: https://cmaeec.com/w...

John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.