ትምህርት፦ አምስት የመንግስቱ መሰረታውያንን ማወቅ
ዓላማ
• አማኞች የመንግሥቱን እውነተኛ ተፈጥሮ ማወቅና የእግዚአብሔር መንግሥት የወደፊት ቦታ ብቻ ሳይሆን የእርሱ አገዛዝ አሁን እና ለዘላለም በሕይወታችን ውስጥ እንደሆነ ማስገንዘብ።
• የመንግሥቱ ዜጎች ማንነታቸውን በመቀበል እንደ የተዋጁ ሰዎች እሴቶቻቸውንና ድርጊቶቻቸውን ከግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በማስማማት የመንግሥቱን አስተሳሰብ ይዘው እንዲኖሩ ማሳሰብ።
• አማኞች የመንግሥቱን እሴቶች በዕለት ተዕለት ሕይወት በመኖር ለዓለም ምስክር እንዲሆኑና በመንፈስ ቅዱስ የሆነውን ጽድቅ፣ ሰላምን እና ደስታን በንቃት እንዲከታተሉ ማሳሰብ።
መግቢያ
በአንድ መንግስት ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ስለሚኖሩብት መንግስት መሰርታውያን የማያውቁ ከሆነ በብዙ ግራ መጋባትና እርግጠኛነት ብሌለበት ህይወት ውስጥ በመኖር ይሰቃያሉ። ልክ እንደዚህ ሁሉ አማኞችም የእግዚአብሔርን መንግስት ተፈጥሮ የማያውቁ ከሆነ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ። እኛም ከዚህ ችግር ለመዳን የመንግስቱን መሰረታውያን ስለማወቅ በዚህ ትምህርት የሚከተሉትን እውነቶች በቃሉ መሰረት እንመለክታልን።
1. እግዚአብሔር ሉዓላዊ ንጉስ ነው።
እግዚአብሔር መንግስቱ ከንግስናው አይለይም።የእግዚአብሔር ሉዓላዊ ሥልጣን/ወይም ገዢነት በፍጥረት ሁሉ ላይ ነው።እግዚአብሔር ይገዛል ማንም ፈቃዱን አያግደውም።መንግስቱም ዘላልማዊ ነው።
መዝ 145:13 ዳን 4: 34-35
2. መንግስቱ እግዚአብሔር የሚገዛበት ነው።
የእግዚአብሔር መንግሥት ፈቃዱ በሚፈጸምበት በማንኛውም ቦታ ነው።ይህም ማለት በሰማይ፣ በምድር እና በሕዝቡ ልብ ውስጥ ሁሉ የእግዚአብሔር አገዛዝ አለ። መንግስቱ በመልካምድር የተግደበ አይደለም ነገር ግን ለንጉሱ በመታዘዝ የተገለጸ ነው።
ማቴ 6:10
መዝ 103:19
3. አማኞች የመንግሥቱ ዜጎች ናቸው።
የእግዚአብሔር መንግሥት በክርስቶስ በኩል ከጨለማው ስልጣን አገዛዝ የዳኑ እና ለእግዚአብሔር የተገዙትን አማኞችን ያቀፈ ነው።እነዚህ የእርሱን በጎነት ለመናገር የተመርጠ ቅዱስ ህዝብና የንጉስ ካህናት የሆነ የአማኞች ስብስብ ነው።
ቆላ 1፡13-14
1ኛ ጴጥ 2:9፡
4. የመንግስቱ ተፈጥሮ - መንፈሳዊ እና ዘላለማዊ
የእግዚአብሔር መንግሥት የሚገነባው በምድራዊ ፖለቲካ ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ጌታ ኢየሱስም መንግስቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም በሎ ነው ያረጋግጠው። ህይወቱም ጽድቅ ሰላም በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ሀሴት እንጂ መብልና መጠጥ አይድልም።
ዮሐ 18:36
ሮሜ 14:17
5. የእግዚአብሔር መንግስት የጊዜ ገደብ- አሁን እና የሚመጣው
መንግሥቱ በኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል፤ ሙሉ በሙሉ መገለጡ ግን የወደፊቱን ጊዜ ይጠብቃል።
ሉቃስ 17:21
ራእይ 11:15
ማጠቃለያ
የእግዚአብሔር መንግሥት አሁን በክርስቶስ እና በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ እና ወደፊት ክርስቶስ በክብር በሚመለስበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ የሚገለጥ የእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ በተዋጁ ህዝቡ ላይ ማለት ነው። ስለዚህ ይህን የተረዱ አማኞች ለመንግስቱ ተፈጥሮ እውነተኛ እውቅና መስጠት፣ እንደ መንግስቱ ዜጎች እውነተኛ ማንነታቸውን በመቀበል፣በእለት ተእለት ኑሮአቸው የመንግስቱን እሴቶች በተግባር እየኖሩ የጌታን መምጣትና የመንግስቱን ሙላት መጠባበቅ ይገባቸዋል። ለዚህም የመንግስቱን መሰረታውያን ማወቅ ወሳኝ የሚሆነው።
Source: https://cmaeec.com/w...

John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.