ትምህርት ስድስት፦ የመንግስቱ መሰረታውያንን ማወቅ
ዓላማ
• አማኞች የመንግሥቱን እውነተኛ ተፈጥሮ ማወቅና የእግዚአብሔር መንግሥት የወደፊት ቦታ ብቻ ሳይሆን የእርሱ አገዛዝ አሁን እና ለዘላለም በሕይወታችን ውስጥ እንደሆነ ማስገንዘብ።
• የመንግሥቱ ዜጎች ማንነታቸውን በመቀበል እንደ የተዋጁ ሰዎች እሴቶቻቸውንና ድርጊቶቻቸውን ከግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በማስማማት የመንግሥቱን አስተሳሰብ ይዘው እንዲኖሩ ማሳሰብ።
• አማኞች የመንግሥቱን እሴቶች በዕለት ተዕለት ሕይወት በመኖር ለዓለም ምስክር እንዲሆኑና በመንፈስ ቅዱስ የሆነውን ጽድቅ፣ ሰላምን እና ደስታን በንቃት እንዲከታተሉ ማሳሰብ።
መግቢያ
በአንድ መንግስት ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦች ስለሚኖሩብት መንግስት መሰርታውያን የማያውቁ ከሆነ በብዙ ግራ መጋባትና እርግጠኛነት ብሌለበት ህይወት ውስጥ በመኖር ይሰቃያሉ። ልክ እንደዚህ ሁሉ አማኞችም የእግዚአብሔርን መንግስት ተፈጥሮ የማያውቁ ከሆነ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ይወድቃሉ። እኛም ከዚህ ችግር ለመዳን የመንግስቱን መሰረታውያን ስለማወቅ በዚህ ትምህርት
2. የእግዚአብሔር መንግሥትና የወንጌል እውነት
2፡1. እግዚአብሔር በፍጥረት ሁሉ ላይ ንጉሥና ገዥ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔርን በፍጥረት ሁሉ ላይ የበላይ ገዥ አድርጎ ይገልጸዋል።ይህም ማለት በሰማይ፣ በምድር ከምድርም በታች ያሉ ፍጥረታት በሙሉ በእርሱ ተፈጥረዋል፣በእርሱ አገዛዝና መግቦት ስር ናቸው ማለት ነው።
መዝሙር 103:191 ዜና መዋዕል 29:11
2.2 በኢየሱስ የተሰበከው የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል
በኢየሱስ የተሰበከው የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል ነው።ምክንያቱም የእግዚአብሔር አገዛዝ በሕዝቡ ልብ ውስጥ እንደሚመጣ ወይም እንደሚሆን የሚያበስር ስለሆነ።
ማቴ 3:2፤ ማቴ 4:17 ማር 1:15 ማቴ 12:28
- ዘመኑ ተፈጸመ፦ በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔር አገዛዙን ለማስተካከል አንድ ቀን መሲሑን (ክርስቶስን) እንደሚልክ ቃል ገባ።ዘፍ 3፤15 ኢየሱስ በመጣ ጊዜ፣ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው ይህ የግዛት ዘመን መጀመሩን አበሰረ። ይህ ማለት መንግሥቱ የሩቅ የወደፊት ተስፋ ብቻ ሳይሆን እውን መሆኑ እየቀረበ ነበር ማለት ነው።
- የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች፦ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች” የሚለው ሐረግ የእግዚአብሔር አገዛዙ፣ ኃይሉና ሥልጣኑ በኢየሱስ በኩል በአዲስ እና ወሳኝ በሆነ መንገድ ወደ ዓለም እየገባ ነበር ማለት ነው።
- የሚያመለክተውም ኢየሱስ በትምህርቱ፣ በተአምራቱ ፣ በኃጢአትና በአጋንንት ላይ ያለው ሥልጣን የእግዚአብሔር አገዛዝ ቀድሞውንም እንደነበረ እና ሰዎች የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ ውስጥ ሲሠራ ማየታቸው ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቅርባለች የሚለውን ያረጋገጠ መሆኑን የሚያሳይ ነው። "እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳልች” ።"ማቴ12:28
- ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ። ምላሽ ይጠይቃል የእግዚአብሔር መንግሥት ከተቃረበ ሰዎች ገለልተኛ መሆን አይችሉም። ለዚያም ነው ኢየሱስ እና ከእሱ በፊት መጥምቁ ዮሐንስ ሰዎችን ንስሐ እንዲገቡ ከኃጢአት ተመልሰው በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር በእምነት እንዲኖሩ የጠራቸው. "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ"ማቴ 4:17
ማጠቃላያ
የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት የእርሱ አገዛዝ፣ ሥልጣን እና ንግሥና ማለት ነው በአሁኑ ጊዜ በአማኞች ልብ እና ሕይወት በክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ በኩል እየሰራ ነው። ይህም የእግዚአብሔር መንግስት መሰረታውያን ከምንላችው ሁለተኛው ነጥብ ነው። በዚህ መርዳት መንግስቱን መቀብል እውነተኛ የወንጌል አማኝ ያደርጋል።እውነተኛ የወንጌል አማኞች ደግሞ የመንግስቱ ዜጎች ናቸው።
Source: https://cmaeec.com/w...

John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.