Home » Sunday sermon – August 31, 2025

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር

Last updated on August 31, 2025 - by Pastor Tariku Eshetu

ትምህርት ሰባት፦ የመንግስቱ መሰረታውያንን ማወቅ

አማኞች የመንግሥቱ ዜጎች ሶስተኛው መስርታውያን ናቸው።

የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች በክርስቶስ በኩል ከጨለማው ስልጣን አገዛዝ የዳኑ እና በእግዚአብሔር አገዛዝ ስር ያሉትን አማኞች ያቀፈ ነው። የእርሱን በጎነት ለመናገር የተመርጠ ቅዱስ ህዝብና የንጉስ ካህናት የሆኑ የአማኞች ስብስብ ነው።ቆላ 1፡13-14 1ኛ ጴጥ 2:9፡

1. የመንግሥቱ ዜግነት ፍቺ

የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጋ መሆን ማለት፦ በክርስቶስ የተስበክውን የእግዚአብሔር መንግስት የምስራች በመቀበል አዲስ ማንነት መያዝ እና በታማኝነት ለእርሱ በመግዛት መኖር ማለት ነው። ይህ ዜግነት በመልካምድራዊ ወሰን ወይም በፖለቲካ ርዕዮት ከሚገልጸው ምድራዊ ዜግነት የተለየ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥት ዜግነት መንፈሳዊ ነው። የሚግኘውም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና በመንፈስ ዳግም በመወለድ ብቻ ነው።
ዮሐንስ 3፡3, 5።ቲቶ 3:3-7 1ጴጥ 1:22-23

2.የመንግስቱ ዜግንት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት

- የእግዚአብሔር መንግሥት ዜግነት ከምድራዊ ኃይል ወይም ሥርዓት ጋር የተያያዘ ሳይሆን ከክርስቶስ የጽድቅ ግዛት ጋር የተያያዘ ነው። ዮሐ 18:36፡ ኢየሱስ መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም በማለት ይህን አረጋግጦል።
- ስለዚህ አማኞች በዋነኛነት የሚገለጹት በምድራዊ ብሔራቸው ሳይሆን የእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግሥት አባል በመሆን ነው። ፊል 3:20 አገራችን ግን በሰማይ ነው፥ ከዚያም የሚመጣውን መድኃኒት እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን።በማለት ቅዱስ ቃሉ ይህን እውነት ያረጋግጣል።
- ወደ መንግስቱ ህጋዊ ሽግግር የሚከናወነው በድነት ጊዜ ነው። ከሰይጣን አገዛዝ ነጻ ወጥቶ ወደ ወደ እገዚአብሔር አገዛዝ በደሙ የኀጢአት ስርየት በማግኘት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት መፍለስ ወይም ህጋዊ ሽግግር ማድረግ ነው። ። ቆላ 1:13 እርሱ ከጨለማ ግዛት አዳነን፥ ወደ ፍቅሩም ልጅ መንግሥት አፈለሰን።
- የመንግስቱ ዜግነት ማለት ደግሞ በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ መካተት ማለት ነው።ይህም ማለት ከቅዱሳን ጋር ባለሀግር መሆን ከእንግድነትና ከምጻተኝነት ነጻ መውጣት ማለት ነው። ኤፌ 2:19 እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።

3. የመንግሥቱ ዜጎች ባህሪያት

በመንፈስ ዳግመኛ የተወለዱ ናቸው። ዮሐ 3፡3-5። በክርስቶስ ጌትነት ስር ይኖራሉ። ሮሜ 14፡17 የመንግሥቱን ጽድቅ፣ ሰላም እና በመንፈስ የሆነ ደስታ ይለማመዳሉ ። እንደ ፍቅር፣ ፍትህ፣ ትህትና፣ ምሕረት ያሉ የመንግሥቱን እሴቶችን ያለማመቻመች ይለማመዳሉ ማቴ 5–7፣ የመንግስቱ ስብከት። በምድር ላይ ያሉ የመንግስቱ አምባሳደሮች/እንደራሴዎች ናችው። 2ኛ ቆሮ 5፡20። በዚህ ዓለም ምጻተኞች እና እንግዶች ናቸው። 1ኛ ጴጥሮስ 2፡11 ምክንያቱም የመጨረሻው መኖሪያቸው በእግዚአብሔር መንግሥት ነውና።

4. የመንግሥቱ ዜጎችና መብቶቻችው

የኃጢአት ስርየት እና ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ አግኝተዋል። ኤፌሶን 1:7 ወደ እግዚአብሔር መገኘት እና ተስፋዎች መድረስ ሆኖላቸዋል። ዕብ 4፡16። ከክርስቶስ ጋር የዘላለም ርስት ይወርሳሉ። ሮሜ 8፡17 የአብርሕም ዘር እንደተስፋው ቃልም ወራሾች ናችው። ገላትያ 3፡26–28።የርስታቸው መያዣ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ መታተምን አግኝተዋል። ኤፌ 1:14 የእግዚአብሔር ቤተመቅደስ ወይም ማደሪያ ሆነዋል።1ቆሮ 3:16-17 2ቆሮ 6:16

5. የመንግሥቱ ዜጎችና ኃላፊነቶቻችው

ለንጉሱ መታዘዝ ዮሐ 14: 15 "ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ" አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ማቴ 6፡33። በዓለም ውስጥ እንደ ጨው እና ብርሃን ኑሩ ማቴ 5፡13-16።ክርስቶስን እንደ አምባሳደሮች በታማኝነት መወከል 2ኛቆሮ5፡20።ሰወችን መውደድ እና ማገልግል።ገላ 5፡13

ማጠቃለያ

የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጋ በክርስቶስ የተቤዠ፣ በአገዛዙ ሥር የሚኖር፣ እና የመንግሥቱን ሙላት ለዘለዓለም እየጠበቀ በዓለም ላይ ሲኖር የመንግስቱን እሴቶች በማንጸባርቅ የሚኖር ሰው ነው። ይህ ማለት የመንግስቱ ዜጎች ማንነት፣ ታማኝነት እና የወደፊት መዳረሻ የሚወሰነው በምድራዊ መንግስታት ሳይሆን በእግዚአብሔር ዘላለማዊ አገዛዝ ውስጥ በመሆናችው ነው ማለት ነው።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.