Home » Sunday sermon – September 14, 2025

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር

Last updated on September 14, 2025 - by Pastor Tariku Eshetu

የመንግስቱ መሰረታውያን

የመንግሥቱ ዜጎች መብቶችና ኃላፊነቶቻቸው

በአንድ መንግስት ውስጥ የሚኖሩ የመንግስቱ ዜጎች የሚኖሩበት መንግስት ውጤታማ እንዲሆን ማወቅና ማድርግ ያልባቸው ሁልት ነገሮች አሉ። እነርሱም መብትና ሐላፊነት ናቸው። የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጋ መሆን መብቶችን የሚሰጠን ብቻ ሳይሆን ኃላፊነቶቻችንንም እንድንወጣ የሚጠይቅ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። በዚህ መሰረት የእግዚአብሔር መንግስት ዜጎችን መብትና ኀላፊነት በቃሉ መሰረት እንመለክታልን።

የመንግስቱ ዜጎች ስልጣንና መብቶች

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች የሆኑት አገልጋዮች ብቻ ሳይሆኑ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው የዳኑ የንጉሥ የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች ሁሉ ናቸው። እንደ ዜጋ፣ ከክርስቶስ ጋር ባላቸው አንድነት ምክንያት መንፈሳዊ ስልጣን እና መብቶች ተሰጥቷቸዋል። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቅሱ የዜጎች ቁልፍ መብቶች ጥቂቶቹን እነሆ፡-

1. የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት

ዮሐ 1:12 ”ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው።” የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች ሙሉ የልጅነት መብቶችን ይዘው ወደ እርሱ ቤተሰብነት ተቀላቅለዋል።

2. የዘላለም ሕይወት መብት

ዮሐ 10:28፡” እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።”አማኞች በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኙ ዋስትና አላቸው።

3.ወደ እግዚአብሔር የመቅረብና ወደመገኘቱ የመግባት መብት

ኤፌ 2፡18-19 “በእርሱ በኩል ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።እንግዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።” በኢየሱስ በኩል ወደ እግዚአብሔር ዙፋን በነፃነት የመቅረብ መብት አለን።

4. የሰላም፣ የደስታ እና የጽድቅ ኑሮ መብት

ሮሜ 14:17፡” የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት እንጂ መብልና መጠጥ አይደለችምና።” ዜጎች በእግዚአብሔር መንፈሳዊ በረከቶች ስር ይኖራሉ።

5. የመጠበቅ እና የድል መብት

ኢሳ 54:17፡” በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፥ በፍርድም በሚነሳብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጅበታለሽ፤ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ይህ ርስት ነው። ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው ይላል እግዚአብሔር።” እግዚአብሔር ለህዝቡ መለኮታዊ ጥበቃውን እና በጠላት ላይ የመጨረሻውን ድል የማግኘት መብትን ይሰጣል።

6. ውርስ የማግኘት መብት

ሮሜ 8:16-17፣ ”የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ያ መንፈስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል። ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ የእግዚአብሔር ወራሾች ነና አብረንም ደግሞ እንድንከብር አብረን መከራ ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን ወራሾች ነን።”ዜጎች የእግዚአብሔር ተስፋዎች፣ በረከቶች እና የዘላለም ርስት ወራሾች ናቸው።

7. ከኃጢአት ኃይል ነፃ የመውጣት መብት

ሮሜ 6:14፡” ኃጢአት አይገዛችሁምና፡ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።” የመንግስቱ ዜጎች በቅድስና ከኀጢአት ኀይል በላይ ለመኖር እና በድል ለመጓዝ ነፃ ወጥተናል።

ማጠቃለያው

የእግዚአብሔር መንግሥት ዜጎች እንደመሆናችን መጠን ልጅ የመሆን፣ የዘላለም ሕይወት የመቀበል፣ ወደ እግዚአብሔር የመቅረብና ወደህልውናው የመግባት፣ በጽድቅ፣ በደስታ፣ በሰላም የመኖር፣የእግዚአብሔርን ጥበቃና ድል አድራጊነት የመታመን፣ የውርስ እና ከኀጢአት ኀይል ነፃነት የማግኘት መብት አለን።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.