የመንግሥቱ ዜጎች መብትና ኃላፊነቶች
2፡ የመንግስቱ ዜጎችና ኀላፊነቶቻችው፦
አማኞች ዛሬ የሚኖሩት ትኩረትን የሚከፋፍሉ፣ ጫናዎች እና ፈተናዎች በሞላበት ዓለም ውስጥ ነው። ሆኖም እግዚአብሔር ሕዝቡ የክርስቶስ አገዛዝ በሕይወታቸው ውስጥ እውን መሆኑን በሚያሳይ መንገድ የመንግሥቱ ዜጎች የመሆን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሕዝቡን ይጠራቸዋል። ስለዚህ በዚህ ተግዳሮት ውስጥ የሚኖሩ አማኞች የመንግሥቱን ኃላፊነቶች ለመወጣት እንዲችሉ የሚረዱ አንዳንድ ተግባራዊ እውነቶችን በዚህ ትምህርት እንመልከት።
2.1 በዕለታዊ ምርጫዎች በመጀመሪያ መንግሥቱን መፈልግ ፦
“ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ…” (ማቴ 6፡33)ይህ ማለት የእግዚአብሔርን አገዛዝ የውሳኔዎቻችን ማዕከል ማድረግ ማለት ነው።ይህም በሙያ ምርጫችን፣ በግንኙነታችን፣ በገንዘብ አስተዳደራችንና በአኗኗር ዘይቤአችን የእግዚአብሔርን አገዛዝ ማስቀደም ማለት ነው።
ምሳሌ፡- ቁሳዊ ስኬትን ብቻ ከማሳደድ ይልቅ ታማኝነትን፣ ልግስናን እና ክርስቶስን የመምሰል እሴቶችን መምረጥ።
2.2 በተሰበረ ዓለም ውስጥ በመንግሥቱ እሴቶች መኖር፦
“የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት። ( ሮሜ 14:17 ) ሌሎች ቁጣ የሞላባቸው ሲሆኑ፣ ታማኝነት የጎደላቸው ሲሆንና እንዲሁም ተስፋ መቁረጥ በሚያሳዩበት ሁኔታ ውስጥ እንደ አማኝ ጽድቅን፣ ሰላምን እና ደስታን ማሳየት።
ምሳሌ፡ በንግድ ስራ ሐቀኛ መሆን፣ በግንኙነት ውስጥ ይቅር ባይ መሆን እና በፈተና ውስጥ ተስፋ ሰጭ መሆን።
2.3 ወንጌልን በቃልና በተግባር ማወጅ፦
“ምስክሮቼ ትሆኑልኛላችሁ…” (የሐዋ ሥራ 1:8) በንግግሮቻችን ውስጥ ኢየሱስን ለሰውች ማካፈል/መናገርና፣ የአኗኗር ዘይቤያችን ደግሞ ፍቅሩን እንዲያንጸባርቅ ማድረግ።
ምሳሌ፡ የወንጌልን እውነትን ማሰራጨት/ ማለት በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ስለ ኢየሱስ አዳኝነት መናገር፣ ጓደኞቻችንን ወደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና ወደ ቤተክርስቲያን መጋበዝ እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያን በጨዋነት መጠቀምና ወንጌልን መመሥከር ።
2.4 ሌሎችን መውደድ እና በተግባር ማገልገል
“በፍቅር እርስ በርሳችሁ አገልግሉ። (ገላ 5:13) በማህበረሰብህ ውስጥ ፍላጎቶችን ማሟላት፣ ለድሆች፣ በብቸኝነት ለሚኖሩ እና ለተገለሉ ርህራሄ ማሳየት።
ምሳሌ፡ በመጠለያዎች ውስጥ ያሉ ሰወችን ለመርዳትና ለማግልገል የበጎ ፈቃደኝነትን ትሳታፊ መሆን፣ የታመሙትን መጎብኘት፣ ሚስዮናውያንን በምንችለው ሁሉ መድግፍ፣ የተጎዱና አዳማጭ ያጡ ሰውችን ወይም ጎረቤቶቻችንን ማዳምጥ።
2.5 ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ጸልይ እና መማለድ
“መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን…” (ማቴ 6፡10)። የእግዚአብሔር ፈቃድ በከተማችን፣ በሥራ ቦታችን እና በሕዝብ ሁል ላይ እንዲፈጸም አዘውትሮ መጸልይ።
ምሳሌ፡ ለፖለቲካ መሪዎችና ለባስልጣናት መጸለይ፣ በስደት ውስጥ ላሉ ክርስቲያኖች መጸለይ ፣እንዲሁም መንፈሳዊ መነቃቃት በምድር ላይ እንዲመጣ መጸለይ። በአለም አቀፍ ፍላጎቶችና ጉዳዮች ላይ የሚያማልዱ የጸሎት ቡድኖችን መቀላቀልና አብሮ መጸለይ።
2.6 የሀብት ታማኝ መጋቢዎች መሆን
“ባለአደራዎችም ታማኝ ሆነው መገኝት አልባቸው”። ( 1 ቆሮ 4:2 ) ገንዘብን፣ ጊዜን እና ተሰጥኦን ለእግዚአብሔር ክብር እንጂ ለራስ ወዳድነትን አላማ አለጠቀም።
ምሳሌ፡ በታማኝነት አሥራት ማውጣት፣የመንግስቱን አገልግሎት በሁሉ ነገር መደገፍ፣ ቤተ ክርስቲያንን ለመርዳት ሙያዊ ክህሎቶችን መጠቀም፣ እና ጊዜን በብቃት ማስተዳደር።
2.7 መንፈሳዊ ውጊያን ውስጥ በእምነት ጸንቶ መቆም
“የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ…” (ኤፌሶን 6፡11)። በባህል ውስጥ ከሚመጣ ኢ-መጸሐፍ ቅዱሳዊ አመለካከትም ሆነ ተግባር ጋር አልማመቻመችና በጽኑ መቃውም እንዲሁም በመጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ላይ ብቻ በፍቅር መቆም።
ምሳሌ፡- በስራ ላይ ሙስናን እምቢ ማለት፣ በግንኙነት/በትግባቦት ውስጥ ንፁህ መሆን እና ከሐሰት ትምህርቶች መጠንቀቅ።
2.8 በተስፋ እና በጉጉት መኖር
“የተባረከውን ተስፋችንን እየጠብቅን…” (ቲቶ 2፡13)። ኑሮአችን ምድራዊ ግቦችን በማሳካት ላይ ብቻ ትኩረት ማድርግ ሳይሆ ነገር ግን የጌታን ዳግም መምጣት በማሰብ እርሱን ለመቀበል ነቅተን በመጠበቅ ከዘላለም እይታ ጋር መኖር አለብን።
ምሳሌ፡ በክርስቶስ ዳግም ምጽአት ተስፋ ሌሎችን ማጽናናት፣ እንዲሁ ያ ተስፋ ውሳኔዎቻችንን እንዲቀርጽ ማአድርግ።
ማጠቃለያ
አማኞች በዚህ ዘመን የመንግሥቱን ኃላፊነቶች በሚከተሉት መንገዶች በመወጣት ይኖራሉ። በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ለእግዚአብሔር አገዛዝ ቅድሚያ በመስጠት።በስምምነት ዓለም ውስጥ በተለየ መንገድ በመኖር። በቃልም በተግባርም ክርስቶስን በማወጅ። ሌሎችን በፍቅር በማገልገል። በምድር ላይ ስለ እግዚአብሔር ፈቃድ በመጸለይ፣ በመንግሥቱ ዓላማዎች ላይ በማተኮር ሀብቶችን በማስተዳደር። በኃጢአትና በዓለማዊ ግፊቶች ላለመረታት ጸንቶ በመቆም እና የክርስቶስን ዳግመኛ መምጣት ተስፋ በማድረግ እየጠበቁ ይኖርሉ።ይህ ነው የዜጎች ኀላፊነት።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.