Home » Sunday sermon – October 12, 2025

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር

Last updated on October 12, 2025 - by Pastor Tariku Eshetu

መንፈስ ቅዱስና የእግዚአብሔር መንግሥት ግንኙነት

መግቢያ

መንፈስ ቅዱስ እና የእግዚአብሔር መንግስት ያላቸው ግንኙነት ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት በጣም አስፈላጊ ነው።ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስና የእግዚአብሔር መንግሥት ግንኙነት በመዳን ላይ፣ በልውጠት ላይ እና በተለዕኮ ስራ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥራ በቅጡ እንድንረዳና በመጸሐፍ ቅዱስ መሰረት ላይ እንድንቆም የሚያደርገን ነውና።በመንፈስ ቅዱስና በእግዚአብሔር መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት በጣም ጠንካራ ነው። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ላይ እንዲገለጥ፣ እንዲመሠረት፣ እና በሰዎች ውስጥ መለኮታዊ ኃይል እንዲታወቅ የሚያደርገው እንዲሁም ሰወችን የእግዚአብሔር መኖሪያ የሚያድርጋቸው እርሱ ስልሆነ።

1. መንፈስ ቅዱስ መንግሥቱን ይገልጣል ያጸናማል

የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት የእግዚአብሔር ርስትና አገዛዝ ነው።እንዲሁም በሰማይም ሆነ በምድር ፈቃዱ የሚፈጸምበት ሁኔታና ቦታ ነው ። (ማቴ 6፥10)። መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው።ስለሆነም በኃይል መንግሥቱን በሰዎች ልብ እና ሕይወት ውስጥ ያመጣል። ሉቃ 11፥20 ኢየሱስ አለ፦“እኔ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፣ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግስት ወደእናንተ ደርሳለች።” በማቴ 12፥28 ፦“ እኔ በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግስት ወደእናንተ ደርሳለች። ”ይህ የጌታ ንግግር መንፈስ ቅዱስ የሚሠራበት ቦታ መንግሥቱ የተገለጠበት ቦታ መሆኑን ያረጋግጣል ነው።

2. መንፈስ ቅዱስ እንደ የመንግሥት ዜጎች እንድንኖር ያበረታታናል

መንግሥቱ የወደፊት ነገር ብቻ አይደለም። በመንፈስ የተወለዱ ሰዎች ውስጥ አሁን ያለ እውነት ነው። ዮሐ 3፥5 – ኢየሱስ አለ፦ “ከውሃና ከመንፈስ ያልተወለደ ሰው ወደ መንግሥቱ መግባት አይችልም።” መንፈስ ቅዱስ አዲስ ልደትን ይሰጣል ማለትም በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ መዳን ማግኝት ነው። ቲቶ 3:5 ይህም ሰዎችን ወደ መንግሥቱ ውስጥ ያስግባል።መንፈስ ቅዱስ የዳነውን አማኝ፦ ያድርበታል፣ ለቤዛ ቀን ያትመዋል፣ይቀድሰዋል፣ወደ እውነት ሁሉ ይመራዋል፣ያስተምረዋል፣ ያጽናናዋል፣የስጋን ስራ መግድል ያስችለዋል፣የመንግስቱን ወንጌል እንዲሰብክ መንፈሳዊ ስጦታን ይሰጠዋል፣ በኀይል ይሞላዋል.......ወዘተ።

3. መንፈስ ቅዱስ የመንግሥቱን ባህሪ ያሳያል

መንግሥቱ መንፈሳዊ ባህሪ ነው ያለው ። ከዚህ የተነሳ ዋጋ የሚሰጠው ለጽድቅ፣ለቅድስና፣ለወንድማማች መዋድድ፣ለእግዚአብሔር ፈቃድ መፈጸምና ከዓለም ፈጽሞ ስለመለየት እና በአንጻሩ በመንፈስ መመላለስን የሚጠይቅ ነው። ሮሜ 14፥17 በአጠቃላይ የእግዚአብሔር መንግሥት መብላትና መጠጣት መገለጫ ባህሪው አይደለም። ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ የሚፈጸም ጽድቅ ሰላም እና ደስታ ነው።እነዚህ የመንግስቱ ባህሪያት በሰው ጥረት አይመጡም። መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ህይወት ውስጥ እንዲፈሩ ያድርጋችዋል እንጂ።ገላ 5፥22–23። መንፈስ ቅዱስ የመንግሥቱን ሕይወት በውስጣችን ይፈጥራል።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.