መንፈስ ቅዱስና የእግዚአብሔር መንግሥት ግንኙነት
መግቢያ
መንፈስ ቅዱስ እና የእግዚአብሔር መንግስት ያላቸው ግንኙነት ምንድነው? የሚለውን ጥያቄ ማንሳት በጣም አስፈላጊ ነው።ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስና የእግዚአብሔር መንግሥት ግንኙነት በመዳን ላይ፣ በልውጠት ላይ እና በተለዕኮ ስራ ውስጥ ያለውን የእግዚአብሔርን ሥራ በቅጡ እንድንረዳና በመጸሐፍ ቅዱስ መሰረት ላይ እንድንቆም የሚያደርገን ነውና። በመንፈስ ቅዱስና በእግዚአብሔር መንግሥት መካከል ያለው ግንኙነት በጣም ጠንካራ ነው። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምድር ላይ እንዲገለጥ፣ እንዲመሠረት፣ እና በሰዎች ውስጥ መለኮታዊ ኃይል እንዲታወቅ የሚያደርገው እንዲሁም ሰወችን የእግዚአብሔር መኖሪያ የሚያድርጋቸው እርሱ ስልሆነ።
1. መንፈስ ቅዱስ መንግሥቱን ይገልጣል ያጸናማል
የእግዚአብሔር መንግሥት ማለት የእግዚአብሔር ርስትና አገዛዝ ነው።እንዲሁም በሰማይም ሆነ በምድር ፈቃዱ የሚፈጸምበት ሁኔታና ቦታ ነው ። (ማቴ 6፥10)። መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ስለሆነም በኃይል መንግሥቱን በሰዎች ልብ እና ሕይወት ውስጥ ያመጣል። ሉቃ 11፥20 ኢየሱስ አለ፦“እኔ በእግዚአብሔር ጣት አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፣ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግስት ወደእናንተ ደርሳለች።” በማቴ 12፥28 ፦“ እኔ በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግስት ወደእናንተ ደርሳለች። ”ይህ የጌታ ንግግር መንፈስ ቅዱስ የሚሠራበት ቦታ መንግሥቱ የተገለጠበት ቦታ መሆኑን ያረጋግጣል ነው።
2. መንፈስ ቅዱስ እንደ የመንግሥት ዜጎች እንድንኖር ያበረታታናል
መንግሥቱ የወደፊት ነገር ብቻ አይደለም። በመንፈስ የተወለዱ ሰዎች ውስጥ አሁን ያለ እውነት ነው። ዮሐ 3፥5 – ኢየሱስ አለ፦ “ከውሃና ከመንፈስ ያልተወለደ ሰው ወደ መንግሥቱ መግባት አይችልም።” መንፈስ ቅዱስ አዲስ ልደትን ይሰጣል ማለትም በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ መዳን ማግኝት ነው። ቲቶ 3:5 ይህም ሰዎችን ወደ መንግሥቱ ውስጥ ያስግባል። መንፈስ ቅዱስ የዳነውን አማኝ፦ ያድርበታል፣ ለቤዛ ቀን ያትመዋል፣ይቀድሰዋል፣ወደ እውነት ሁሉ ይመራዋል፣ ያስተምረዋል፣ ያጽናናዋል፣ የስጋን ስራ መግድል ያስችለዋል፣የመንግስቱን ወንጌል እንዲሰብክ መንፈሳዊ ስጦታን ይሰጠዋል፣ በኀይል ይሞላዋል.......ወዘተ።
3. መንፈስ ቅዱስ የመንግሥቱን ባህሪ ያሳያል/ያለብሳል
መንግሥቱ ባህሪ መንፈሳዊነት ያለው ነው። ከዚህ የተነሳ ዋጋ የሚሰጠው ለጽድቅ፣ለቅድስና፣ለወንድማማች መዋድድ፣ለእግዚአብሔር ፈቃድ መፈጸምና ከዓለም ፈጽሞ ስለመለየት ከፍተኛ ትኩርት ይሰጣል። እና በአንጻሩ ደግሞ በመንፈስ መመላለስን የሚጠይቅ ነው። ሮሜ 14፥17 በአጠቃላይ የእግዚአብሔር መንግሥት መብላትና መጠጣት መገለጫ ባህሪው አይደለም። ነገር ግን በመንፈስ ቅዱስ የሚፈጸም ጽድቅ ሰላም እና ደስታ አይነተኛ የባህሪው መገልጫ ነው።እነዚህ የመንግስቱ ባህሪያት በሰው ጥረት አይመጡም። መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ህይወት ውስጥ እንዲፈሩ ያድርጋችዋል እንጂ።ገላ 5፥22–23።እንደሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ የመንግሥቱን ሕይወት በውስጣችን ይፈጥራል።ስለዚህ የመንግስቱ ባህርያት በአማኞች/በመንግስቱ ዜጎች ይገልጣል ወይም ይታያል።
4. የመንፈስ ቅዱስ ኃይል የመንግሥቱ ማረጋጋጫ ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ኀይል የእግዚአብሔር መንግስት በዚህ ምድር የመገለጡ ወይም የመምጣቱ አይነተኛ ማርጋገጫ ነው።ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እኔም በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ እንግዲያስ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።” ማቴ 12፥28 ይህ በጌታ ኢየሱስ የተደረገው ተግባርና የተነገርው ገለጣ የሚያረጋግጠው የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በምድር ላይ መታየት የእግዚአብሔር መንግሥት ወደኛ መድረሱንና እየሰራ መሆኑን ነው። ጌታችን ኢየሱስ ድንቆችን አደርገ፣ድውዮችን ፈወሰ፣በአጋንንት የታሰሩትን አርነት/ነጻ አወጣ፣ የእግዚአብሔርን መንግስት ሰበከ። ይህን ሁሉ ያደርገው በመንፈስ ቅዱስና በኀይል ተቀብቶ ነበር። ሐዋ 10:38
እነዚህ የእግዚአብሔር መንግስት መገልጥ ማስርጃ የሆኑ እና በመንፈስ ቅዱስ ኀይል የተፈጽሙ የጌታ ተግባርት በእርሱ ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ ከማድረግ ይልቅ በቅጣይነት በመንግስቱ ዜጎች/አማኞች ህይወት ውስጥ እንዲቅጥል ጌታችን ኢየሱስ ወደአባቱ ተመልሶ ከመሔዱ በፊት እንዲህ በማልት ተዕዛዝን ሰጠ ፦ “ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሶስተኛውም ቅውን ከሙታን ይነሳል በስሙም ንሰሀና የኀጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰብካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል።እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። እነሆ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኆለሁ እናንተ ግን ከላይ ኀይል እስክትቀበሉ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ”። ሉቃ 24:46-49 ይህም የእግዚአብሔር መንግስት መገለጥ በአማኞች ህይወት ውስጥ ቀጣይ መሆኑን የሚያረጋግጥ ያደርገዋል።
በኢየሱስ በማመነቸው ምክንያት መንፈስ ቅዱስን የሚቀበሉ አማኞች ሁሉ የእግዚአብሔር መንግስት ዜጎች ይሆናሉ ስለዚህም መንፈስ ቅዱስ ያድርባችዋል።1ቆሮ 6:19-20 ይህ በውስጣቸው ያደረው መንፈስ ደግሞ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በመስጠት በኀይል ይሞላችዋል።ስለዚህም ያመኑትን እነዚህ ምልክቶች ይከተሉዋችዋል።ማር 16:17።ይህም የእግዚአብሔር መንግስት ወደ እኛ የመድርሱ ማስረጃ ነው።
5. መንፈስ ቅዱስ መንግሥቱን ያስፋፋል፦
ጌታችን ኢየሱስ ወደ አባቱ ከመሔዱ በፊት ለተከታዮቹ እንዲህ አለ፦ “መንፈስ ቅዱስ በላያችሁ በወርደ ጊዜ፣ ኃይልን ትቀበላላችሁ.............ምስክሮች ትሆናላችሁ።” ሐዋ. 1፥8 ይህ እውነት የሚያረጋግጠው አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የመንግሥቱን ወንጌል ለዓለም ሁሉ እንዲያደርሱ መላካቸውንና ኀላፊነት መወሰዳችውን ነው። ማንኛውም ሰው በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ ዳግም ሲወልድ ይድናል፣ ከኀጢአት ኀይል ነጻ ሲወጣ ወይም ሲለወጥና የመንግስቱን ወንጌል ላልስሙት ሲያሰማ ደግሞ መንግሥተ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ይሰፋል።ይህም የመንፈስ ቅዱስ የስራ ውጤት ነው።ሀይልን መቀበልና ምስክር መሆን።
6.መንፈስ ቅዱስ ለሚመጣው ፍጹም መንግሥት አማኞችን ያዘጋጃል
መንፈስ ቅዱስ የሚመጣውን ፍጹም መንግሥት በርግጠኝነት የምንቀበልበትን ዋስትና የመዳናችንን ወንጌል በስማንበት ቅጽበት ይሰጠናል።እንዲሁም የመንግስቱን ህይወት ጣዕም በማቅመስ የርስታችን መያዣ/ቀብድ በመስጠት ድኅነታችንን ያርጋግጠልናል። “ እናንተ ደግሞ የእውነትን ቃል ይኸውም የመዳችሁን ወንጌል ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ እርሱም የረስታችን መያዣ ነው፣..... ።” ኤፌ. 1፥13-14 ስለዚህ ወደ ፍጹሙ መንግስት እንደምንገባ እርግጠኝች ስለሆንን ሞትን አንፍራም። ምክንያቱም ሞት በዳንበት ጌታ ለዘላለም ተሸንፎአልና።
ማጠቃለያ፦
መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር መንግስት ጋር ያለው ግንኙነት የሚገለጠው በአማኙ ህይወት ውስጥ ነው። ስለሆነም መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን መንግስት በአማኝ ህይወት ውስጥ ይገልጣል ያጸናማል፣ እንደ የመንግሥት ዜጎች እንድንኖር ያበረታታናል፣የመንግሥቱን ባህሪ ያሳያናል፣የመንግስቱን ሐይል በህይወታችን ይገልጣ፣ መንግስቱን በእኛ ያሰፋል፣ እንዲሁም ለሚመጣው ፍጹም መንግስትያዘጋጀናል። ይህም አማኞች የተለወጠ የህይወት ስርዓት እንዲኖራችው ያደርጋል። በእግዚአብሔር መንግስትና በመንፈ ቅዱስ መካከል ያለውን ግንኙነት መረዳት የመንግስቱን ህይወት በመንፈስ ቅዱስ እንድንኖር ያስችለናል።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.