Home » Sunday sermon – November 9, 2025በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር
Last updated on November 9, 2025 - by Pastor Tariku Eshetuየእግዚአብሔር መንግስትና ጸሎት
ዓላማ
የጸሎትን ትርጉም እንደ ቃሉ መርዳት
የጸሎትን መሰረት እንደቃሉ መርደት
ጸሎትን አንደ ቃሉ መጸለይ የሚያስፈልግበትን ምክንያት መርዳት
መግቢያ
የእግዚአብሔርን መንግስት የተቀበለ አማኝ በትክክል ሊገነዘበው ከሚገባ ነገሮች መካከል ጸሎትን በተመልከተ መጸሐፍ ቅዱስ የሚያስትምረውን እውነት መረዳት ነው። ምክንያቱም ጸሎት የመንግስቱ ዜጋ ከእግዚአብሔር ጋር የሚገናኝብት መንገድ ስልሆነ። ስለዚህ በዚህ ትምህርት ልናውቀው የሚገባንን እውነት ውንመልከታለን።
1:ጸሎት ምንድን ነው?
ጸሎት በሰው እና በእግዚአብሔር መካከል ያለ መንፈሳዊ ግንኙነት ነው። ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው። ጸሎት እርሱን ማምለክ፣ ማመስገን ነው። ኃጢአት መናዘዝ ነው። ልመና እና ፈቃዱን መፈለግ ነው። ጸሎት ለአማኙ መንፈሳዊ ሕይወት እስትንፋስ ነው። ጸሎት ነፍሳችን ከፈጣሪያችን ጋር የምትገናኝበት መንገድ ነው።
2፡የጸሎት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረቶች
2:1 ጸሎት መንፈሳዊ ግንኙነት ነው። "ሁልጊዜ መጸለይ እና ተስፋ ባለመቁረጥ መጸለይ።"
ሉቃስ 18:1
2:2 ጸሎት የእምነት ተግባር ነው። "በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ እንደተቀበላችሁ እመኑ ይሆንላችሁማል።ማርቆስ 11:24
2:3 ጸሎት መንፈሳዊ የሕይወት መስመር ነው። "ሳታቋርጡ ጸልዩ"1 ተሰሎንቄ 5: 17
3፡የጸሎት ዓላማዎች እና ዓይነቶች
የምስጋና እና የአምልኮ ጸሎት - ስለማንነቱ ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት.
መዝሙረ ዳዊት 100:4
ችግር ጊዜ ጸሎት/የተማጽኖ ጸሎት - በችግር ጊዜ እግዚአብሔርን ለእርዳታ መጥራት። ያዕቆ 5፡13
የኑዛዜ ጸሎት - በኃጢአታችን ማዘን እና ንስሐ መግባት1 ዮሐ1:9
የምልጃ ጸሎት - ለሌሎች መጸለይ 1 ጢሞ 2:1
የልመና ጸሎት - ለግል አስፈልጎታችን እና ጉድለታችን እግዚአብሔርን መጠየቅ።ፊል 4:6
4፡እንደ መንግስቱ ዜጎች እንዴት እንጸልይ?
በመንፈስ ቅዱስ በመመራት - ሮሜ 8፡26
ከእምነት ጋር - ማቴ 21:22
በንጹሕ ልብ - መዝ 66:18
በጽናት - ቆላ 4: 2
ማጠቃለያ
ጸሎት የአንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ እስትንፋስ ነው። ሰውነታችን ያለ አየር መኖር እንደማይችል ሁሉ መንፈሳችንም ያለ ጸሎት መኖር አይችልም። ጸሎት እምነትን ያጠናክራል። ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ይገነባል። ጸሎት ወደ እግዚአብሔር መገኘት ውስጥ ያስገባናል። ጸሎት መለኮታዊ ሀይል ወደ ህይወታችን እንዲለቀቅ ያደርጋል። ስለዚህ የጸሎትን ትርጉም በማወቅ፣ የጸሎትን መጸሀፍ ቅዱሳዊ መሰርት በመገንዝብ፣ የጸሎት አይነቶችን በመጠቀም እንደ መንግስቱ ዜጎች ጸሎትን መልማመድ ይኖርብናል።
Source: https://cmaeec.com/w...