ትምህርት አስራ አምስት: የእግዚአብሔር መንግስትና ጸሎት
5፡ ምንድን ነው እንጽልይ?
እያንዳንዱ አማኝ የጌታን ጸሎት ያውቃል፣ ግን ብዙዎች ጥልቀቱን አይረዱም። ኢየሱስ “መንግሥትህ ትምጣ፣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን” ብለን እንድንጸልይ ሲያስተምረን ለፍላጎታችን ሳይሆን ስለ እግዚአብሔር ዓላማ እንድንጸልይ እያስተማረን ነው። ይህ ጸሎት ራስን የመገዛት፣ የመታዘዝ እና መንፈሳዊነታችን ከሰማይ ጋር የመስማማቱ መገለጫ ነው። ስለዚህ በዚህ ትምህርት መንግሥቱን መጸለይ ምን ማለት እንደሆነ እንመለክታልን።
5:1፡ መንግሥትህ ትምጣ በለን ስንጸልይ
ማቴዎስ 6፡9 10 በመጀመሪያ አማኞችን በቀጣይነት ደግሞ ዓለምን የሚቀይር ጸሎት እየጸለይን ነው። ኢየሱስ በመጀመሪያ መንገስቱን እንድንጸልይ ያስተማረን ለዚህ ነው ። ይህ ደግሞ የእያንዳንዱ እውነተኛ ደቀ መዝሙር የልብ ትርታ ነው። መንግሥትህ ትምጣን መጸለይ ማለት፦ እግዚአብሔር እኛን እንዲገዛ፣በእኛ እንዲገዛ፣ በእኛ እንዲሠራ እና በእኛ እንዲመለስ መጋበዝ ነው።
5:2 የመንግስትህ ትምጣ ጸሎት መፈጸም የሚጀምረው
የሰውን ልብ በመለወጥ ነው። ሉቃ 17:21”እነሆኋት የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናትና አላቸው”። መንግስቱ በመካከላችን መሆን የሚጀምረው ኢየሱስ በልባችን ውስጥ ሲነግስ ነው። ይህን እውነት መጸሐፍ ቅዱስ በትለያየ አጠራር ገልጾታል። ለምሳሌ አዲስ ፍጥረት መሆን፣ዳግም መወለድ፣ አዲስ ሰው መሆን፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን.....ወዘተ በማለት ገልጿታል። ስልዚህ “ሀሳቦቼን፣ ምርጫዎቼን፣ ግንኙነቶቼን የሚገዛው ማነው?” ብሎ መጠየቅና እግዚአብሔር አንዲግዛን መጋብዝ፣ በሁሉም የሕይወት ዘርፎቻችን የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲፈጸም መፍቀድ፣ የመንግስቱ ስልጣን እንዲሰራ እና የመንግስቱን ባህሪ እንድንልብስ መጸለይ ተገቢ ነው።
5:3 መንግሥቱ በዚህ ዓለም እንዲስራ መጸለይ።
ኢየሱስ የመንግሥቱን መምጣት አበሰረ አወጀ ማር. 1:15። ኢየሱስ የመንግሥቱን ኃይል አሳየ ወይም ገለጠ። “ዕውሮች ያያሉ፣አንካሶች ይሄዳሉ፣ለምጻሞች ይነጻሉ፣ ድንቆሮዎች ይሰማሉ፣ሙታን ይነሳሉ፣ለድሆች ወንጌል ይሰበካል፣.....”። ማቴ 11:4,12። ስለዚህ በቤተክርስቲያን ውስጥና እንዲሁም በምንኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ የእግዚአብሔር ኃይል እንዲሰራ መጸልይ ያአማኝ ኀላፊነት ነው።
5:4 መንግሥቱ በቤተ ክርስቲያን በኩል እንዲስራ መጸለይ
ጌታ እንዳስተማረው የእግዚአብሔር መንግስት እንደሰናፍጭ ዘር በትንሹ ይጀምራል ነገር ግን እያደገ ይሔዳል። በጥቂት ደቀ መዛሙርት በኢየሩስሌም ጀምሮ →ወደ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ተለወጠ። ይህ የመንግስቱ ስራ የሚከናወነው በጸጥታ ግን በኃይል እይሰራ ነው። የመንግሥቱ ተጽዕኖ የሚስፋፋው በፍቅር፣ በአገልግሎት እና በምስክርነት ነው። ስልዚህ በቤተክርስቲያን መንግስቱን መጸለይ ቀዳሚና ዋና ተግባር ነው።13፡31-33
5:6 የመንግስቱን ሙላት መጸለይ
ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም በሚመለስበት ጊዜ መንግሥቱ ሙሉ በሙሉ ትመጣለች/ትገለጣልች ራእይ 11:15
መንግሥቱ አሁን በቤተክርስቲያን በኩል እየገዛች ነው። ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አይድልም። “እነሆ የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናታና”እንደተባለ ነገ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም መምጣት በሙላት ትመጣልች/ትገለጣለች ስልዚህ በዛን ጊዜ፦ ክፋት ያበቃል ፍትህ ይመጣል፣ ፍጥረት ወደ ነበረበት ይመለሳል ማለትም እኩይ ፈጽሞ ይወገድል፣ እግዚአብሔር በሚታይ እና በዘላለማዊነት ይገዛል፣ ሞት ለቅሶና ጨለማ ለዘለዛለም ይወግዳል። ስለዚህ አሁን የመንግስቱ ዜጎች ሁሉ በጽድቅ በቅድስና እና እራስን በመግዛት እየኖሩ እንደጥንቷ ቤተክርስቲያን፡- “ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና። እያሉ መንግስቱን ይጸልያሉ።( ራእይ 22:20 )
ማጠቃለያ
በቤተክርስቲያን ዛሬ የሚጸለየው ጸሎት የመንግስት ትምጣ ጸሎት ሊሆን ይግባል። ማለትም መንግስቱ በልባችን እንዲገዛና ዓለማችንን እንዲለውጥ፣ ደግሞም በጌታችን ዳግም መምጣት የመንግስቱ ሙላት እንዲሆን በመናፍቅ ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና የሚል የመንግስቱ ናፍቆት ጸሎትን መጸለይ ማለት ነው። እርስዎ ዛሬ ምን እየጸለዩ ነው???????መንግስትህ ትምጣ ወይስ ሌላ?????
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.