መንግስተ እግዚአብሔር በኢያሱ መጸሐፍ
መግቢያ
“የእግዚአብሔር መንግሥት” የሚለውን ሐረግ ስንሰማ ብዙ ሰዎች ስለ መንግሥተ ሰማያት ወይም ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብቻ እናስባለን። የኢያሱ መጽሐፍ ግን የእግዚአብሔር መንግሥት የወደፊት ብቻ ሳይሆን አሁን ያለ፣ የሚሠራ እና በእርሱ በሚታመኑት ሰዎች ሕይወት ውስጥ ኃይለኛ እንደሆነ ያስተምረናል። የኢያሱ መጽሐፍ ከእግዚአብሔር መንግስት አንጻር በእስራኤል ታሪክ ውስጥ አንድ ወሳኝ ወቅትን ዘግቧልናል ይህም እግዚአብሔር የገባውን ቃል እየፈጸመ በሕዝቡ መካከል አገዛዙን እንደመሠረተ የሚያሳየን ታሪክ ነው። ይህን ታሪክ መሰረት በማድርግ የእግዚአብሔርን መግስት ርምደታዊ የመገልጥ ሂደት እንመለከታለን።
I. እግዚአብሔር የመንግስቱ እውነተኛ ንጉሥ ነው። (ኢያሱ 1፡3–5; 5፡13–14)
ከመጽሐፈ ኢያሱ የምንማረው የመጀመሪያው እውነት ይህ ነው። እግዚአብሔር ራሱ ንጉሥ ነው የሚለውን እውነት ማረጋገጥ። ኢያሱ ጠንካራ መሪ ቢሆንም የሥልጣን ምንጭ ግን አልነበረም። ለዚህ ነበር እግዚአብሔርም እንዲህ ያለው። ከሙሴ ጋር እንደ ነበርሁ ከአንተም ጋር እሆናለሁ።
ይህ የሚያሳየን በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ያለው አመራር የሰው ኃይል ወይም ችሎታ እንዳልሆነ፣ስለ እግዚአብሔር መገኘት እና ስልጣን፣/ሀለወት እና እስራኤላውያን ያገኙት ድል ሁሉ የመጣው ከጌታ መሆኑን ነው። ጦርነቶቹ የእግዚአብሔር ጦርነቶች ነበሩ። ምድሪቱ የእግዚአብሔር ስጦታ ነበረች። ዛሬም ቢሆን የእግዛብሔር መንግሥት የሚቋቋመው በህይውታችን ውስጥ የሚሰራው ውሳኔያችንን፣ ድርጊታችንንና ልባችንን እንዲገዛ ስንፈቅድለት ነው። እግዚአብሔር ዙፋኑን/ስልጣኑን አያጋራም ምክንያቱም ዘለዓለማዊ ንጉሥ ነውና።
II. መንግሥቱ በአምላካዊ ተስፋዎች ላይ የተመሠረተ ነው።ኢያሱ 21፡43-45
ሁለተኛው እውነት ይህ ነው።የእግዚአብሔር መንግሥት የተፈጸሙ ተስፋዎችን የያዘ መንግሥት ነው።እግዚአብሔር ምድሪቱን ለዘሩ እንደሚሰጥ ለአብርሃም ከትውልድ በፊት ተስፋ ሰጥቶ ነበር።በኢያሱ ዘመን ይህ ተስፋ ፍጻሜውን አግኝቷል። እግዚአብሔር ከገባላቸው መልካም ተስፋዎች ሁሉ አንድም ቃል እንዳልቀረ ቅዱሳት መጻሕፍት ይነግሩናል።
ይህም የእግዚአብሔር መንግሥት ተስፋ እምነት የሚጣልበት መሆኑን ያስታውሰናል።የእግዚአብሔር መንግስት የእግዚአብሔር ቃል የሚፍጸምበት ነው። የሰው መንግሥት ይነሣል ይወድቃል፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ግን በታማኝነት ስለተመሠረተ ሁሌም ጸንቶ ይቆማል። ከዚህ እውነት በመነሳት ዛሬ እግዚአብሔር በቃሉ አማካይነት እንደሚስራ ሙሉ በሙሉ ልናምን እንችላለን። የእግዚአብሔር ቃል ፍጹም ቢዘገይም ይፈጸማል።
III. በመንግሥቱ ውስጥ የመኖር መንገድ መታዘዝ ነው።ኢያሱ 1:7-8; 7፡11
የኢያሱ መጽሐፍ ታዛዥነት በእግዚአብሔር መንግሥት ሕይወት ውስጥ ዋና ነገር እንደሆነ ያስተምረናል። እግዚአብሔር ኢያሱን በቀንና በሌሊት ቃሉን እንዲያሰላስል አዘዘው። እስራኤል ሲታዘዙ ድል እና ሰላም አግኝተዋል። አልታዘዝም ሲሉ ሽንፈትንና ውድቀት አጋጠማቸው። ይህም አንድ ጠቃሚ መንፈሳዊ መርሕ ያስተምረናል የእግዚአብሔር ኃይል ከእግዚአብሔር መመሪያዎች የተለየ አለመሆኑን፣ የንጉሱን ሥልጣን እየተቃውምን የመንግሥቱን በረከቶች መጠየቅ አንችልም። መታዘዝ ሕጋዊነት/legagalism ውስጥ መግባት ማለት አይደለም ለእግዚአብሔር በታማኝነት የሚገለጽ ፍቅር ነው።
IV. መንግሥቱ ዕረፍትንና ውርስን ያመጣል ኢያሱ 11:23; 23፡1
መጽሐፈ ኢያሱ የመጭርሻ ምንባባት እንደሚያረጋግጡት የእስራኤል ሕዝብ ወደ ዕረፍቱ ገባ። ርስታቸውን ተቀበሉ። ይህ ዕረፍት የእግዚአብሔር መንግሥት የወደፊት ሁኔታ ምልክት ነው። በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር የድኅነት ፍጻሜ፣የሞት ዘለአላማዊ መወግድ እና ሰላም በፍጻሜ የተረጋገጠ ነው።የህዘቡ ርስታቸውን መውርስ ወደ አንድ ትልቅ እውነታ ይጠቁማሉ። ይህም እግዚአብሔር ህዝቡ በመንፈሳዊ እረፍት እንዲኖሩና ሙሉ በሙሉ በእርሱ እንዲታመኑ የሚፈልግ መሆኑ። እውነተኛ እረፍት ከንብረት፣ ከስኬት ወይም ከስልጣን አይመጣም። ነግር ግን በእግዚአብሔር መንግሥት ሥር ከመኖር የሚመጣ ነው።
V. የመንግሥቱ ማንን እንደምናገለግል የመምረጥ ውሳኔ ይጠይቅል ኢያሱ 24፡14–15
"አሁንም እግዚአብሔርን ፍሩ፥ በቅንነትና በታማኝነትም አምልኩት... እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን። ኢያሱ መጽሐፉን የጨረሰው ስለ መንግሥቱ በተነሳ ጥያቄ ነው። የእግዚአብሔር አገዛዝ ውሳኔን ይፈልጋል። መንግሥቱ በግዳጅ የሚኖርበት አይደለም ነገር ግን በሰወች ነጻ ፈቃድ የተመረጠ ነው።ስልዚህ እያንዳንዱ ትውልድ እግዚአብሔር በእውነት በሕይወታቸው ይነግስ የሚለውን መወሰን አለበት።
ማጠቃለያ
የኢያሱ መጽሐፍ የእግዚአብሔር መንግሥት እውነተኛ፣ ኃይለኛ እና ንቁ/የሚሰራ እንደሆነ ያሳየናል። እግዚአብሔር ንጉሥ ነው። የገባው የተስፋ ቃል ሳይፈጸም አይቀርም። ለእግዚአብሔር መታዘዝ በረከትን ያመጣል። እምነት ወደ መንግስቱ ዕረፍት ይመራናል የሚለውን እውነት ያስተምረናል። ዛሬም፣ እግዚአብሔር መንግሥቱን የሚገነባው በነዚህ መርሆዎች መሰረት ለመኖር በሚመርጡ ልቦች ውስጥ ነው። ኢያሱ እንዳለው እንዳለው "እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን" ብለን መንግስቱን እንምረጥ። መንግስቱ ሁሉን ትገዛልችና።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.