ገንዘብ በእግዚአብሔር መንግስት ውጥ መጠቀም
የንባብ ክፍል፦ ማቴዎስ 6፥19–24፤ 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥6–10፣ 17–19
መግቢያ
ገንዘብ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ በጣም ከተለመዱት ጉዳዮች አንዱ ቢሆንም፣ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ መንፈሳዊ ማንነታችንን በጉልህ ከሚያሳዩ ነገሮችም አንዱ ነው። ኢየሱስ ስለ ገንዘብ በተደጋጋሚ ተናግሯል፤ ይህን ያደረገው ገንዘብ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ከሁሉ የላቀ ነገር ስለሆነ ሳይሆን፣ ልባችንን ለማግኘት ከእግዚአብሔር ጋር በቀላሉ ስለሚወዳደር ነው። ምክንያቱም ገንዘብን የምንይዝበት መንገድ ማንን እንደምናምን፣ ምን እንደምንፈራ እና ከሁሉ በላይ ለምን ነገር ዋጋ እንደምንሰጥ ግልጥ አድርጎ ያሳያል። ብዙ ሰዎች የፋይናንስ ሰላም የሚገኘው በዋናነት ብዙ በማግኘት፣ ብዙ በመቆጠብ ወይም የተሻለ ምክር በማግኘት ይመስላቸዋል። እርግጥ ነው እነዚህ ነገሮች ሊረዱ ይችላሉ፣ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ከዚህ ይልቅ ጠለቅ ያለ እውነትን ያስተመረናል። ስለዚህ የሚከተሉትን መርሆዎች ማወቅና ተግባራዊ ማድረግ ተጥቃሚዎች እንሁን።
1፡እንደ አማኝ ማድርግ የማንችለውን ማወቅ
- በማቴዎስ ምዕራፍ 6 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ግልጽ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል እንዲህ በማለት “ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ በአንድነት መገዛት አትችሉም”። ይህ ማለት ገንዘብ ክፉ ነው ማለት አይደለም።ገንዘብ የመግዛት ኃይል ስላለው የሚገዛችሁን ምረጡ ማለት ነው እንጂ።ምክንያቱም ገንዘብ በእግዚአብሔር ሥልጣን ሥር ካልተገዛ እኛን መግዛት ይጀምራልና።በመሆኑም፣ክርስቲያናዊ የገንዘብ አያያዝ በጀት ስለማውጣት ብቻ የሚነጋገር አይደለም። ስለ አምልኮ፣ ስለ ጥበብ እና ስለ ምስክርነት ጭምር የሚነጋገርም ነው እንጂ።
- መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው ገንዘብን በክርስቶስ ጌትነት ስር ለማስገዛት የመጀመሪያው ጉዳይ የባንክ አካውንታችን መጠን ሳይሆን የልባችን ሁኔታ መስተካከል ነው።ምክንያቱም አንድ ሰው ድሃ ሆኖ ታማኝ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ባለጸጋ ሆኖ የገንዘብ ባሪያ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እውነተኛው ጥያቄ “ገንዘቤን እንዴት ላስተዳድር?” የሚለው ብቻ ሳይሆን “ክርስቶስ በገንዘቤ ላይ እንዴት ይነግሣል?” የሚለውን ቀዳሚ የአማኝ ሀላፊነት ተግባራዊነት ማርጋገጥ ነው።
- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ ገንዘብን ማገልገል ምን ማለት ነው፦ እግዚአብሔርን እንደ ብቸኛ ሀብትና መታመኛ ከመቁጠር ይልቅ፣ ለሀብት ወይም ለገንዘብ ተገዥ መሆን እና ሀብትን እንደ ትልቅ ውድ ነገር መቁጠር ማለት ነው። ይኸም ማለት እቅዶቻችንንና ባህሪያችንን ሁሉ ገንዘብ ሊሰጠን የሚችለውን ጥቅም ለማሳደግ ብቻ ማስላት ማለት ነው።
- ይህ በተግባር ምን ማለት ነው? ሕይወታችን በገንዘብ ተስፋዎች ዙሪያ ይሽከረከራል በየቀኑ “ከገንዘብ ምን ዓይነት ጥቅሞችን ማግኘት እችላለሁ?” ብለን እንጠይቃለን፣ እንዲሁም ከፍተኛ የፋይናንስ ትርፍ ወደሚያስገኝልን አቅጣጫ ምርጫዎቻችንን እንቀይሳለን።
- ገንዘብ ጌታታችን ይሆናል ምን ማለት ነው?፦ የገንዘብን “ጥያቄዎች” እንሰማለን፣ ፍላጎቶቹንም እንታዘዛለን፤ የዚህን ጌታ ፍላጎት (ክፍያዎችን፣ የዕዳ ጫናን፣ ማኅበራዊ ደረጃን፣ ደኅንነትን/የመኖር ዋስትናን) ለማሟላት ማንኛውንም ዋጋ እንከፍላለን፣ እንዲሁም ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ገንዘብ እንዲወስንልን እንፈቅዳለን ማለት ነው።
- ልባችን ለሀብት የተገዛ ይሆናል ምን ማለት ነው?፦ ኢየሱስ ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም፤ ወይም አንዱን ጠልታችሁ ሁለተኛውን ትወዳላችሁ (ማቴዎስ 6:24) ይላል።ልባችን ለሀብት የተገዛ ይሆናል ወይም ገንዘብን ማገልገል ማለት ታማኝነታችን፣ ተስፋችን እና ደኅንነታችን/የመኖር ዋስትናችን በእግዚአብሔር ላይ ሳይሆን በሀብት/በገንዘብ ላይ እንዲያርፍ ማድረግ ማለት ነው።
- ገንዘብን እያገለገልን መሆኑን እንዴት እናውቃልን? ገንዘብን ማገልገል በገንዘብ በአጠቃቀማችንና በሕይወት ዘይቤአችን ላይ ይንጸባረቃል። ገንዘብን እያገለገልን መሆናችንን ማወቅ የምንችለው ገንዘባችን ወዴት እንደሚሄድና የያዝናቸው ንብረቶች ስለ ውስጣዊ ፍላጎታችን ምን እንደሚመሰክሩ በማየት ነው።ስግብግብነት፣ ራስ ወዳድነት የሞላበት ምቾት ወይም ለድሆች ለመርዳት ፈቃደኛ አለመሆን አብዛኛውን ጊዜ ገንዘብን ማገልገልን የሚያሳዩ ጥሩምልክቶች ናቸው።
- እግዚአብሔርን ማገልገልና ገንዘብን ማገልገል ልዩነት፦ አንድ ልብ ማለት ያለብን ነገር ቢኖር የሀብት መኖር እና ሀብትን ማገልገል አንድ አለመሆናቸውን ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ሀብት እኛን ከእግዚአብሔር የመሳብ አዝማሚያ ስላለው በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ “አታላይ” እና እንቅፋት እንደሆነ ያስጠነቅቃል፣ ስለዚህ ለእርሱ ባልተገዛንበት ጊዜ እግዚአብሔርን ለማክበር ልንጠቀምበት እንችላለን።
ማጠቃለያ
ገንዘብን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለእግዚአብሔር በማስግዛት ለመጠቀም እንዲሁም በገንዘብ እግዚአብሔርን እያከበርንና እያገለገልን ለመኖር እንድንችል ለገንዘብና ለእግዚአብሔር በአንድ ጊዜ መገዛት የማንችል መሆኑን መገንዘብና ከገንዝብ ባርነት ነጻ ሊያወጣን ለሚችለው ለቃሉ የእውነት መርህ እርሳችንን እንስጥ።ለገንዘብና ለእግዚአብሔር በአንድ ላይ መገዛት አንችልምና።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.