በዕዳ ባርነት ውስጥ የዚህ ዓለም የገንዝብ አስተዳደር ስራዓት መትረፍ
(የብድር ካርዶችን /Credit cards በጥበብ ማስተዳድር )
ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያስገነዝቡት፣ ዕዳ ውስጥ መግባት በራሱ ኃጢአት ባይሆንም፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሚመርጠው ከሁሉ የተሻለው መንገድ ግን አይደለም። ምክንያቱም ለመበደር ስንመርጥ፣ እምነታችንንና መተማመኛችንን በእግዚአብሔር ላይ ከማድረግ ይልቅ በብድር ካርድ ወይም በአበዳሪው ላይ እያደረግን በመሆናችን ነው። በምሳ 22፥7 ላይ “ሀብታሞች በድሆች ላይ ይገዛሉ፥ ተበዳሪም ለአበዳሪ ባሪያ ነው” እንደሚለው። መበደር በጣም በፍጥነት ወደ ልማድ ወይም ወደ ማያልቅ አዙሪት ሊቀየር ይችላል፤ ይህም ከጌታና እርሱ ከሚሰጠን ነፃነት ይበልጥ ያርቀናል የዕዳ ባሪያዎችምያ ደርገናል።ስለዚህ ወደዚህ አዙሪት ወደሞላው ባርነት ውስጥ ላለመግባትና የገባንም ካለን በቅዱስ ቃሉ መርህ መስረት ነጻ እንድንወጣ የሚከተሉትን እውነቶች ልብ ማለት ይጠቅማል።
ዋስ ከመሆን መራቅ (AVOID SURETY)
መጽሐፍ ቅዱስ ዋስ ከመሆን ወይም ለከፍተኛ ግዴታ ወይም ዕዳ ሲባል በገንዘብ፣ በንብረት አለያም በከፊል ክፍያ ዋስትና ከመስጠት መራቅ እንዳለብን በግልጽ ያስተምራል። ምሳ 11፥15 “ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራ ያገኘዋል ዋስትና ለመስጠት እጅ የማይመታ ግን ምንም አይደርስበትም።” ይላል በተጨማሪም ምሳ 22፥26-27 ከዋስትና ጋር የተያያዙ ተጨማሪ አደጋዎችን ያስታውሰናል “በዋስትና ቃለ እጅ አትምታ ለብድር ተያዥ አትሁን የምትከፍለው ካጣህ የምትተኛበትን ዐልጋ ከስርህ ይወስድብሀል” ይላል ። ስለዚህ ገንዘብን በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለማስተዳደር ይህን መርህ መከትል አማራጭ የለውም ማለት ነው።
የድንገተኛ አደጋ ቁጠባ ፈንድ ይኑረን (HAVE AN EMERGENCY SAVINGS FUND)
የፋይናንስ መረጋጋትን ለማግኘት በሚደረገው ጉዞ ይህ ምናልባት ልንከተለው ከሚገባን በጣም አስፈላጊ መመሪያዎች አንዱ ነው።አብዛኞቹ አሜሪካውያን የ500 ዶላር ቁጠባ እንኳ እንደሌላቸው ጥናቶች ያመላክታሉ። ይህንን በእያንዳንዱ ቤተሰብ ላይ ካለው አስደናቂ የዕዳ መጠን ጋር ስናያይዘው፣ የብድር ካርድ ዕዳ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ወረርሽኝ መሆኑ ምንም አያስደንቅም።
ምሳ 21፥20 “የከበር መዝገብና ዘይት በጠቢብ ሰው ቤት ይኖራል፤ አዕምሮ የሌለው ሰው ግን ይውጠዋል።” ይላል። ጤናማ የቁጠባ ሒሳብ በማዘጋጀት፣ ለድንገተኛ አደጋ ወይም ላልታሰበ ወጪ በብድር ካርዶችዎ ላይ ከመደገፍ ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል።ይህንን ቁጠባ በአንስተኛ ዶላር ቁጠባ ጀምረን ቀስ በቀስ የአንድ ዓመት የኑሮ ወጪያችንን ሊሸፍን ወደሚችል ደረጃ ማሳደግ እንችላለን።ይህን መርህ ላለመከተል ብዙ ጊዜ የሚጠቀስውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ጠጋ ብለን ማየት ጠቃሚነት አለው።
የጌታ ኢየሱስ ትምህርት ምንድነው?
ማቴ 6:19–21 “ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ/ሀብት አታከማቹ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ/ሀብት አከማቹ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።”
ትርጉሙን በቀላል ደረጃዎች እንመልከተው፦
1. “በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ”
“ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ” ማለት፦ ጊዜያዊና አስተማማኝ ባልሆኑ ነገሮች ማለትም ገንዘብ፣ ንብረት፣ ማዕረግ፣ ዝና፣ ምቾት፣ ስኬት ወዘተ ለመሰብስብ ብቻ አትኑሩ ማለት ነው።
“ብልና ዝግ በሚያጠፉት” የሚለው ደግሞ ቁሳቁሳዊ ነገሮች ይበላሻሉ፣ ያረጃሉ፣ ዋጋቸውንም ያጣሉ።ስለዚህ መታምኛ አታድርጓቸው ማለት ነው
“ሌቦች ቆፍረው በሚያጠፉት” በምድር ላይ ያለ ማንኛውም ነገር በድንገት ሊጠፋ ይችላል (ስርቆት፣ ቀውስ፣ ሞት፣ የኢኮኖሚ ለውጥ ሊያገኘው ይችላል) ።አስተማማኝ መመኪያ ሊሆን አይችልም ማለት ነው
ስለዚህ ኢየሱስ ገንዘብ ማግኘት፣ ንብረት ማፍራት ወይም በጥበብ ማቀድ ኃጢአት ነው እያለ አይደለም።ነገር ግን የሚያስጠነቅቀው ምድራዊ ነገሮችን የደህንነታችን የመጨረሻ ዋስታና፣ የደስታችንና የማንነታችን ልክ “መዝገባችንን/ሀብታችንን” ስላለማድረግ ነው።
2. “በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ”
“ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ” ማለት፦ሕይወታችንን ዘለዓለማዊ ዋጋ ባላቸውና በእግዚአብሔር ዘንድ ቅቡልነት ባላቸው ነገሮች ላይ ማፈስ ማለት ነው።
የ“በሰማይ መዝገብ” መሰብሰብ ማለት፦ እግዚአብሔርን መውደድና መታዘዝ። በኢየሱስ ስም ሌሎችን ማገልገል።በቅድስናና በታማኝነት መኖር። ገንዘብን፣ ስጦታዎቻችንና ጊዜአችንን ለእግዚአብሔር መንግሥት ዓላማዎች ማዋል፤ ወንጌልን ለጠፉት ማካፈል፣ ደቀ መዛሙርትን ማፍራት፣ የምህረትና የፍትህ ሥራዎችን መስራት ማለት ነው። እነዚህ ነገሮች ሊጠፉ፣ ሊሰረቁ ወይም ሊበላሹ አይችሉም።ምክንያቱም እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ ያያል፣ ያስባልምና ነው።
3. “መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና”
ይህ የመጨረሻው ጥቅስ ጉዳዩ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ያብራራል፦
መዝገብ፦ ከሁሉም በላይ አብልጠን የምንወደው፣ የምንከተለውና የምንጠብቀው ነገር ማለት ነው።
ልብ፦የውስጥ ሕይወታችንን ማልትም ምኞቶቻችን፣ ፍቅራችን፣ የቅድሚያ አሰጣጣችንን ፣ አቅጣጫ ያመለክታል።ከዚህ አንጻር ኢየሱስ እያለ ያለው መዝገባችን አድርገን የምንየዘው ማንኛውም ነገር ልባችንን ወደዚያ አቅጣጫ ይስበዋል ማለት ነው። እንጂ ገንዘብን ወይም ሀብትን በጽድቅና በጥበብ ማስተዳደር እምነት ማጣት ነው እያለ አይደልም።ስለዚህ መዝገባችን ምድር ላይ ከሆነ፣ ልባችንም ከምድር ጋር ይያያዛል። መዝገባችን በላይ በሰማይ ከሆነ፣ ልባችንም ወደ እግዚአብሔርና ወደ መንግሥቱ ይሳባል ማለት ነው።
ስለዚህ ማቴ 6:19–21 አማኞችን እንዲህ ሲል ይጠራል፦ይህ ዓለም ብቻ እንዳለ አድርገው በማስብ መኖርን አቆሙ።እንዲሁም እግዚአብሔር ዋጋ በሚሰጣቸውና ለዘለዓለም በሚኖሩ ነገሮች ላይ መዋዕለ ነዋያችንን ማፍሰስ ጀምሩ ይለናል። የገንዘብ፣ የጊዜና የጉልበት አጠቃቀማችን ደግሞ እግዚአብሔር እራሱ ትልቁ መዝገባችን መሆኑን የሚያሳይ ይሁን ማለት ነው። ስለዚህ ይህን ጥቅስ ጠቅሶ መርህ ማፍረስ ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርምና እንጠንቀቅ።
በጀት ማዘጋጀት (CREATE A BUDGET)
ይህ መርህ ዕዳ ላለባቸውም ለሌለባቸውም ይሠራል። ገንዘባችን ወዴት እየሄደ እንደሆነና ምን ዓይነት ዓላማ እያገለገለ እንደሆነ ለማየት በጀትን መከተል ፍጹም ተመራጭ መንገድ ነው።በጀት በማዘጋጀት ከአቅም በላይ ከሆነ የብድር ካርድ ዕዳ ነጻ መውጣት ከፈለግን፣ ከክርስቲያን የብድር አማካሪዎች (Christian Credit Counselors) ጋር መገናኘትና ሙያዊ ምክር ማግኘት ያስፈልግናል። የእነርሱን ከፍተኛ ሥልጠና ያገኙ የአማካሪዎች ቡድን ካገኘን ካርዶቻችንን በትክክለኛው መንገድ የምንጠቀምበትን ዕቅድ ለማውጣት ሊረዱን ይችላሉ።
ማስተዋል ያለብን ነገር ቢኖር፣ የብድር ካርድ ለሁሉም ሰው የሚሆን አለመሆኑን ነው!ስለዚህ ካርድ መጠቀም ከመቀጠላችን ወይም አዲስ ካርድ ከማውጣታችን በፊት ለራሳችን ታማኝ እንሁን እና ስለ ውሳኔያችን እንጸልይ። ካርዳችንን በትክክለኛው መንገድ ለመጠቀም ጥበብ የተሞላበት አስተዳደርና ሥርዓት (discipline) ይጠይቃል፤ ስለዚህ በትክክለኛው መንገድ እንደማንይዘው ካወቅን፣ ራስችንን ከዕዳና ከሥቃይ የማዳን ኀለፊነት አለብን።
ዕዳዎን ለመክፈል ዕቅድ ማውጣት ከፈለጉ፣ በ“ዕዳ በረዶ ኳስ” (Debt Snowball) ማስያ ሒሳብ ይጀምሩ። ዕዳዎን ከፍለው ለመጨረስ በትክክል ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድብዎ፣ ምን ያህል ወለድ ማዳን እንደሚችሉ እና ሊከተሉት የሚገባውን የክፍያ መርሃ ግብር በትክክል ያሳየዎታል። ለመጠቀም ቀላል ስለሆነ ዛሬውኑ መጠቀም መጀመር ይቻላል!
የበረዶ ኳስ ዕዳ መክፈያ ዘዴ (Debt snowball) መጀመሪያ አነስተኛውን ዕዳ በመክፈል እና በሌሎቹ ዕዳዎች ላይ ዝቅተኛውን የክፍያ መጠን ብቻ በመክፈል ዕዳን ለመጨረስ የሚረዳ መንገድ ነው። አነስተኛው ዕዳ ተከፍሎ ሲያልቅ፣ ለዚያ ይከፈል የነበረውን ገንዘብ ቀጥሎ ወዳለው አነስተኛ ዕዳ በማዛወር የ"በረዶ ኳስ" አይነት ተፅዕኖ መፍጠር።
እንዴት እንደሚሰራ
ዕዳዎችዎን ከአነስተኛ የዕዳ መጠን ወደ ትልቅ በማደራጀት ይዘርዝሩ።
በየእያንዳንዱ ዕዳ ላይ አነስተኛውን የክፍያ መጠን መክፈል።
ማንኛውንም የተረፈ ተጨማሪ ገንዘብ በአነስተኛው ዕዳ ላይ መጨመር።
ያ ዕዳ ከተከፈለ በኋላ፣ የዚያን ክፍያ መጠን ቀጥሎ ወዳለው አነስተኛ ዕዳ መውሰድ።
· ቀላል ምሳሌ፦ የ$500፣ $1,500 እና 500 ዕዳን ለመክፈል ይረባረባሉ፣ ከዚያ ወደ $1,500 ዕዳ ይሸጋገራሉ፣ በዚሁ መልኩ ይቀጥላሉ።
ሰዎች ለምን ይጠቀሙበታል
ፈጣን ስኬቶችን ስለሚሰጥ ተነሳሽነትን ይፈጥራል።
ለመከተል ቀላል እና ግልጽ ነው።
አስፈላጊ ማስታወሻ ስለ የበረዶ ኳስ ዕዳ መክፈያ ዘዴ
የበረዶ ኳስ ዘዴ የወለድ መጠን ቅደም ተከተልን ግምት ውስጥ አያስገባም፤ ይህም ከፍተኛ ወለድ ያለበትን ዕዳ መጀመሪያ ከሚከፍለው "የበረዶ መንሸራተት ዘዴ" (Debt avalanche method) ይለየዋል።
ማጠቃለያ
ዳግም እንደተወለደና የእግዚአብሔርን መንግስት እንዳየ አማኝ በዚህ ምድር ወይም ዓለም ውስጥ ስንኖር ልንከተለው ከሚገባን የመንግስቱ ስርዓትና መርህ መካከል ገንዝብን በአግባቡ ማስተዳድር አንዱ ነው።ይህንንም ለማድርግ እንድንችል ለገንዘብና ለእግዚአብሔር በአንድ ላይ መግዛት እንደማንችል ማውቅ፣ሁሉ የእግዚአብሔር መሆኑንና እኛ ባለአደርዎች መሆንችንን ማወቅና ሀላፊነታችንን መወጣት፣መንፈሳዊ ጠበብን መሞላት፣ለጋስነትን መለማመድ እና በዕዳ ባርነት እንዳንያዝ በቅዱስ ቃሉ መርህ መስረት በመኖር ነጻነታችንን ማስጠበቅ አለብን።እንዲህ ገንዘብን በእግዚአብሔር መንግስት ልናስተዳድር ይገባናልና።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.