የእግዚአብሔር መንግሥት በመክብብ መጽሐፍ
“ንጉሡን ፍራ፣ ስጦታውን ተቀበል፣ ለዘላለም ሕይወት ኑር”
ዋና ምንባብ: መክብብ 12:13–14 መክብ 3:1–14፤ 5:18–20፤ 8:12–13
የመክብብ መጽሐፍ አጭር ታሪካዊ መነሻ (ታሪካዊ ዳራ)
የመክብብ መጽሐፍ ከኢዮብ፣ ከመዝሙረ ዳዊት፣ ከምሳሌ እና ከማህለየ መሃልይ ዘሰሎሞን መጽሐፍት ጋር አብሮ የሚቆጠር የብሉይ ኪዳን የጥበብ መጻሕፍት አካል ነው። መጽሐፉ ሁላችንንም የሚነካውን አለምአቀፋዊ ጥያቄ በቅንነት ይመረምራል ይህም ሞት፣ አፍትሃዊነት፣ ለውጥ እና አለመረጋጋት በሁሉ ላይ በሚደርሱበት ጊዜ ለሕይወት ዘላቂ ትርጉም የሚሰጠው ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ይመልሳል።
ደራሲው እና የተጻፈበት ዘመን
ደርሲውን በተመልከት ሁለት አመለካከቶች አሉ ባህላዊ/ጥንታውያን አና የዘመናዊው ምሁራን አመለካከት ናቸው።ጥንታውያኑ ጸሐፊው ሰለሞን የዳዊት ልጅ ነው ብለወ ያምናሉ ዘመናዊዎቹ ምሁራን ደግሞ የሰሎሞንን የንጉሥነት ድምፅ በመጠቀም የጻፈ ማንነቱ ያልታወቀ የኋላ ዘመን የእስራኤል ሊቅ እንደጻፈው አድርገው ይረዱታል።
የስነ-ጽሑፍ ሁኔታ (Literary Setting)
መክብብ የቀላል ታሪክ ወይም የሕጎች ስብስብ አይደለም ነገር ግን የጥበብ አስተምሮ/አስተማሪ (Reflections) ሥራ ነው። ምሳሌዎችን፣ ግጥሞችን፣ጥልቅ ምልክታዎችን፣ ጥያቄዎችን፣ የግል ምስክርነቶችን፣ አባባሎችን እና ተደጋጋሚ ቃላትን ይጠቀማል።የመጸሐፉ ዋናው ሐረግ እንዲህ ይላል፡ “ከንቱ፣ ከንቱ፣ ሁሉ ከንቱ ነው።” መክብብ 1:2
አብዛኛውን ጊዜ “ከንቱ” ተብሎ የሚተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል “ሄበል” (hebel) ይባላል። ትርጉሙም ትንፋሽ/ትነት፣ጭጋግ ወይም ቀጭን የውሀ ጉም (mist)፣ አለያም በፍጥነት የሚያልፍና ለመያዝ አስቸጋሪ የሆነ ነገር ማለት ሊሆን ይችላል።ሰባኪው ይህን ቃል ሲጠቅም ሕይወት ምንም ዋጋ የላትም ብሎ እያስተማር አይደለም።ይልቁንም ሰባኪው የሚያስተምረው “ከፀሐይ በታች” ያለ ሕይወት ከምድራዊ እይታ አንጻር ብቻ የሚታይ ጊዜያዊ፣ እርግጠኛ ያልሆነ እና የመጨረሻውን ትርጉም መስጠት የማይችል መሆኑን ለማሳሰብ ነው።
ሌላው አስፈላጊ ሐረግ “ከፀሐይ በታች” የሚለው ነው። ይህም ሰዎች በዚህ የወደቀ ዓለም ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ሕይወት ያመለክታል ይህም ሥራ፣ ሕመም፣ ሞት፣ አፍትሃዊነት፣ ደስታ፣ እርጅና፣ አለመረጋጋት እንዲሁም የሰውን ልጅ ወስንነት የሚያመለክት ነው።
መጽሐፉ አማኞች አሁን በዚህ ዓለም ውስጥ በእግዚአብሔር ግዛት/አገዛዝ ሥር እንዲኖሩ ይጣራል።ከዚህ የተነሳ የመጸሐፉ የመጨረሻው ትእዛዝ “ምስጢርን ሁሉ ተረዳ” ፣ “ሀብታም ሁን” ወይም “ወደ ፊትህን ተቆጣጠር” የሚል አይደለም። ይልቁንም፡ “እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዛቱንም ጠብቅ” የሚል ነው።
መግቢያ
በዚህ ዘመን ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት በአንድ መንገድ ብቻ ነው የሚረዱትና የሚፈልጉት ስለዚህ ኃይልን፣ ብልጽግናን፣ ሰላምን፣ ተአምራትን፣ ድልን እና በረከትን ብቻ ማየት ይፈልጋሉ። በእርግጥም የእግዚአብሔር መንግሥት የእግዚአብሔርን አገዛዝ፣ ኃይል፣ ጽድቅ እና በረከትን ያካትታል። ነገር ግን የመክብብ መጽሐፍ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በጣም አስፈላጊ የሆነን ሌላ ነገር ያስተምረናል ይህም በእግዚአብሔር መንግሥት በረከቶች ከመደሰታችን በፊት፣ አስቀድመን ለንጉሡ መገዛት እንዳለብን ያስተምረናል።መክብብ “የእግዚአብሔር መንግሥት” የሚለውን ቀጥተኛ ሐረግ ደጋግሞ አይጠቀምም። ሆኖም ሙሉው መጽሐፍ እግዚአብሔር ገዢ ንጉስ ነው ወደ ሚለው እውነት ያመለክተናል።እንዲህ በማለት እርሱ ከጊዜ በላይ ነው። እርሱ ከሰው ጥበብ በላይ ነው። እርሱ ከሀብት በላይ ነው። እርሱ ከመንግሥታት በላይ ነው። እርሱ ከኢፍትሃዊነት በላይ ነው። እርሱ ከሞት በላይ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ንጉሥ ነው ይለናል።ከዚህ በመነሳት ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከመክብብ መጽሐፍ ሦስት እውነቶችን እንመለከታለን፡
1. እግዚአብሔር በጊዜ/በወቅት ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው መክ 3:1, 11, 14
“ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፥ ከሰማይም በታች ለሚከናወነው ለማንኛውም ነገር ውቅት አለው።” መክ 3:1
መክብብ ምዕራፍ 3 ሕይወት የሚለዋወጡ ወቅቶች እንዳሏት ያስተምረናል። ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ለማዘን ጊዜ አለው፥ ለመጨፈርም ጊዜ አለው ወዘተ......። ይህ ክፍል ባጠቃላይ ሁሉንም ነገር በእጃችን እንደማንቆጣጠር በአጽኖት ያሳስበናል።በርግጥም በሕይወታችን ውስጥ የሚከሰቱትን ነገሮች ሁሉ መቆጣጠር አንችልም። የምንወለድበትን ጊዜ አንመርጥም። ጊዜን ማስቆም አንችልም። ሁልጊዜ ሕመምን መከላከል አንችልም። ነገ የሚያመጣውንም ነገር ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አንችልም። ነገር ግን አንድ መልካም ዜና አለ እንዲህ የሚል እግዚአብሔር በአገዛዝ ላይ ነው (ሁሉ በዕርሱ ቁጥጥር ስር ነው) የሚል። መክብብ 3:11 እንዲህ ይላል፡ “ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው…”የሚል ነው። እግዚአብሔር ለሁሉም ነገር ጊዜና ዓላማ አለው። አንዳንዴ የእርሱን ጊዜ አንረዳውም። እንጸልያለን፣ ነገር ግን መልሱ የዘገየ ይመስላል። ጠንክረን እንሰራለን፣ ነገር ግን ውጤቱ በፍጥነት አይታይም።ለፈውስ፣ ለስጦታ/ለአቅርቦት፣ለምሪት ወይም ለዕረፍት እርሱን እንጠብቃለን።በዚህም ይድክመናል ይህን ጊዜ አንድ ነገር ማስታወስ አለብን፡ እግዚአብሔር በጊዜ ላይ ንጉሥ ነው፣ደግሞም ፈጽሞ አይዘገይም የሚለውን።
እግዚአብሔር በእኛ ፕሮግራም ላይሰራ ይችላል፣ ነገር ግን ሁልጊዜ በጥበቡና በስልጣኑ ይሰራል፤ስለዚህ የእኛ ኃላፊነት እያንዳንዱን ወቅት መቆጣጠር አይደለም። የእኛ ኃላፊነት ወቅቶችን የሚቆጣጠረውን እርሱን ማመን ነው።መክብብ 3:14 እንዲህ ይላል፡ “እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ለዘላለም እንዲኖር አወቅሁ… ሰወች ያከብሩት ዘንድ ይህን አደርገ።
እኛ የምንገነባቸው ነገሮች ለዘላለም ላይኖሩ ይችላሉ። ገንዘባችን ለዘላለም ላይኖር ይችላል። ጉልበታችን ለዘላለም ላይኖር ይችላል። እግዚአብሔር የሚያደርገው ነገር ግን ለዘላለም ይኖራል።
የተግባር ተዛምዶ (ትግበራ)
• ምናልባት ዛሬ በአስቸጋሪ ወቅት ውስጥ ብንሆን።
• ለጸሎት መልስ እየጠበቅን ቢሆን።
• የመከፋት ሁኔታ ገጥሞን ቢሆን።
• በሐዘን ውስጥ ብንሆን።
• ስለ ወደፊትህ እርግጠኛ ባንሆን።
እግዚአብሔር የረሳን መስሎ ይሰማን ይሆናል።ይሁን እንጂ እንዲህ ያለው ወቅታችን ንጉሡን እንድንጠራጠር እንዲያደርግን አንፍቀድ።ምክንያቱም አስቸጋሪ ወቅት ላይ አለን ማለት እግዚአብሔር ትቶናል ማለት አይደለምና።የጸሎት መልስ ዘገየ ማለት እግዚአብሔር ከልክሎናል ማለት አይደለም።ይልቁንም ወቅቶችን የሚገዛው እግዚአብሔር አሁንም በሕይወታችን ውስጥ እየሰራ ነው።ስለዚህ ለራሳችን እንዲህ እንበል: “ወቅቱን ባልረዳውም፣ ንጉሡን አመናለሁ።”
2. እውነተኛ እርካታን የሚሰጠው እግዚአብሔር ብቻ ነው መክብብ 2:10–11፤ 5:18–20
ሰባኪው ሰዎች ዛሬም የሚያሳድዱትን ነገር ሁሉ በመፈለግ የርካታን ትርጉም ለማግኘት አሰሰ። ተድላን፣ ጥበብን፣ ጠንካራ ሥራን፣ ሀብትን፣ ታላላቅ ሕንፃዎችን፣ ስኬትን እና ንብረቶችን ተከተለ። ነገር ግን ብዙ ነገሮችን ካገኘ በኋላ፣ ሁሉ “ከንቱነትና ነፋስን እንደ መከተል” እንደሆነ ተርዳ ተናገረም። “ከንቱ” ማለት እንደ ትንፋሽ ወይም ጉም ማለት ነው። እንደ ጠዋት ጤዛ (ጉም) ማለት ነው። ለጥቂት ጊዜ ልናየው እንችላለን፣ ነገር ግን ልንይዘው አንችልም። በፍጥነት ይጠፋል ማለት ነው።
ሰባኪው ህብታና ንብረት ነፍስን ማረካት እንደማይችል ተማረ። ገንዘብ ይጠቅማል፣ ነገር ግን ገንዘብ እርካታ ሰጪ አይደለም። ስኬት መልካም ነው፣ ነገር ግን ስኬት እርካታ ሰጪ አይደለም። ትምህርት ዋጋ አለው፣ ነገር ግን ትምህርት እርካታ ሰጪ አይደለም። ሥራ አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን ሥራ እንደ አምላክ መታምኛ አይደለም። ሰዎች አስፈላጊ ናቸው፣ ነገር ግን ሰዎች አምላክን የሚተኩ አይደሉም።ምክንያቱም መልካም ነገሮችን የመጨረሻና የእርካታ ምክንያት ስናደርጋቸው፣ እነዚያ ነገሮች ጣዖታት ይሆናሉና።
ከዚህ እውነት አንጻር መክብብ 5:18 እንዲህ ይላል፡ “እንሆ እኔ ያየሁት መውልካምና የተዋብ ነገር ሰወ እግዚአብሔር በስጠው በህይወቱ ዘመን ሁሉ ይበላና ይጠጣ ዘንድ፥ ከጸሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ሁሉ ደስ ይለው ዘንድ ነው ይህ እድል ፈንታው ነውና።” መጽሐፍ ቅዱስ ምግብ፣ ሥራ፣ ቤተሰብ እና ምድራዊ በረከቶች ክፉ ናቸው ብሎ አያስተምርም። እነርሱ በእግዚአብሔር የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው። ችግሩ የሚጀምረው ሰጪውን ከማምለክ ይልቅ ስጦታውን ማምለክ ስንጀምር ነው።
እግዚአብሔር የእርሱን ስጦታዎች በምስጋና እንድንደሰትባቸው እንጂ የማንነታችንና የደስታችን ምንጭ አድርገን በእነርሱ ላይ እንድንደገፍ አይፈልግም።ይህም የእግዚአብሔር መንግሥት እውነተኛ እርካታ የሚመጣው ንጉሡን በማወቅና በመታዘዝ እንደሆነ ያሳየናል።ስለዚህ እውነት ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡ “ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል” ማቴዎስ 6:33 እግዚአብሔር የመጀመሪያ ቦታ ሲይዝ፣ ሌሎች በረከቶች ተገቢውን ቦታ ያገኛሉ።
ለምስሌ
አንድ ሰው ትልቅ ቤት ሊኖረው ይችላል ነገር ግን ከቤቱ የተሳ የሚያገኘ ሰላም አይኖረውም። አንድ ሰው ገንዘብ ሊኖረው ይችላል ነገር ግን በገንዝቡ ብቻ ደስታ አይኖረውም። አንድ ሰው ብዙ ወዳጆች ሊኖሩት ይችላል ነገር ግን ብቸኝነት ይሰማዋል። አንድ ሰው ስኬታማ የሥራ ሕይወት ሊኖረው ይችላል ነገር ግን አሁንም ባዶነት ይሰማዋል። ለምን? ምክንያቱም የሰው ልብ በጊዜያዊ ነገሮች ሊሞላ ከሚችለው በላይ ጥልቅ ስለሆነ ነው። እግዚአብሔር በፈጠረው የሰው ልብ ውስጥ ያለውን ባዶ ቦታ መሙላት የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነውና።
የተግባር ተዛምዶ (ትግበራ)
ራስችንን እንጠይቅ፡ “ለእርካታዬ በምን ላይ እየተደገፍኩ ነው?” በገንዘብ፣በግንኙነት፣በሥራ በሰዎች ሙገሳ ስላገኘሁ/ተቀባይነት ስላልኝ ነው? በስኬቶቼ በእቅዶቼ፣ ከእነዚህ ነገሮች መካከል አንዱም እግዚአብሔርን ሊተካ አይችልም።የእግዚአብሔር መንግሥት እግዚአብሔርን አስቀድመን ከሁሉ በላይ እንድናስቀምጥ ይጠራናል።ምክንያቱም ክርስቶስ በልባችን ውስጥ ንጉሥ ሲሆን፣ ለበረከቶች ባሪያ ሳንሆን በበረከቶች መደሰት እንችላለንና።
3. እግዚአብሔር በሰው ሕይወት ሁሉ ላይ ይፈርዳል መክብብ 12:13–14
በመክብብ መጽሐፍ መጨረሻ ላይ፣ሰባኪው የመጨረሻውን እውነት በመናገር ሀሳቡን ይደመድማል እንዲሲል “እግዚአብሔርን ፍራ፥ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው ሁለንተና (ሙሉ ግዴታው) ነውና።” እግዚአብሔርን መፍራት ማለት በፍርሃት ተውጠን ከእርሱ መሸሽ ማለት አይደለም። ነገር ግን እርሱን ማክበር፣ ማምለክ፣ ሥልጣኑን ማክበር እና ቃሉን መታዘዝ ማለት ነው። እግዚአብሔርን መፍራት ማለት እርሱ ቅዱስ እንደሆነና እኛ ደግሞ በፊቱ ተጠያቂዎች መሆናችንን ማወቅ ማለት ነው።
ስባኪው በመቀጠል እንዲህ ይላል፡ “እግዚአብሔር ሥራን ሁሉ፥ የተሰወረውንም ነገር ሁሉ፥ መልካምም ቢሆን ወይም ክፉ፥ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።” አንድ ቀን እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ይቆማል። ከእርሱ የተሰወረ ምንም ነገር የለም። እግዚአብሔር የአደባባይ ሕይወታችንን ያያል። እግዚአብሔር የግል ሕይወታችንን ያያል። እግዚአብሔር ድርጊታችንን ያያል። እግዚአብሔር ቃላቶቻችንን ይስማል።እግዚአብሔር የልባችንን ሃሳብ ይመረምራል እግዚአብሔር ሚስጥራዊ ውሳኔዎቻችንን ይመለከታል።ይህም ማንም አያውቅም ብለው በማሰብ በዓመጽ ለሚቀጥሉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ነው። እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል።
በአንጽሩ በኀጢአታቸው ለሚጸጸቱና ንሰህ ለሚገቡ ታማኝ አማኞች ደግሞ ማበረታቻ ነው። ምናልባት ሰዎች የጸሎት ተጋድሎአችንን አያዩ ይሆናል። መስዋዕትነታችንንም አያዩ ይሆናል። አገልግሎታችንን አያዩ ይሆናል። ታዛዥነታችንን አይረዱት ይሆናል። ነገር ግን እግዚአብሔር ያያል። መክብብ 8:12 እንዲህ ይላል “ኀጥእ መቶ ወንጀል ሰርቶ ዕድሜው ቢረዝምም እግዚአብሔር የሚያከብሩ ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላቸው ሰወች መልካም እንዲሆንላቸው ዐውቃለሁ።” ይላል
ኃጢአተኞች ለጥቂት ጊዜ የሚበልፀጉ ሊመስሉ ይችላሉ፣ ነገር ግን በነርሱ ላይ የእግዚአብሔር የመጨረሻ ፍርድ እርግጠኛና የማይቀር ነው። ጻድቃን ለጥቂት ጊዜ ሊሰቃዩ ይችላሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር አይረሳቸውም።ይህንን እውነት ለማስገንዘብ የመክብብ መጸሐፍ ጊዜያዊውን የብልጽግና ገጽታ እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ሰዎች ከተሰጠው ዘላቂ መልካም ነገር ጋር ያነጻጽረዋል።
ይህ እውነት ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊመራን ይገባል።ምክንያቱም እግዚአብሔር የተሰወረውን ነገር ሁሉ የሚፈርድበት ከሆነ፣ እኛ በራሳችን መልካምነት በፊቱ መቆም አንችልምና የሚያድነን ያስፈልገናል።ሁላችንም ኃጢአት ሠርተናል።ሁላችንም ወድቀናል።ሁላችንም የራሳችንን ሕይወት ለመምራት ሞክረናል ግን አልቻልንም።እኛ በዚህ ውስጥ እያለን ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከ መጣ። እርሱ ያለ ኃጢአት ኖረ፣ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፣ ከሞት በድል ተነሳ።በኢየሱስ ክርስቶስ ስናምን ይቅርታን፣ አዲስ ሕይወትን እና በእግዚአብሔር የዘላለም መንግሥት ውስጥ የዘላለም ቦታን እናገኛለን።ስለዚህ ኢየሱስ አዳኛችን ብቻ አይደለም፤ እርሱ ንጉሣችንም ጭምር ነው እንጂ።በመሆኑም ኢየሱስ ከኃጢአታችን እንዲታደገን ብቻ መጠየቅ የለብንም። ሕይወታችንንም ለንጉሥነቱ ማስገዛት አለብን።
ማጠቃለያ
መክብብ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ግልጽ መለዕክት ይሰጠናል።ይህም እግዚአብሔር በጊዜ/በወቅት ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።እውነተኛ እርካታን የሚሰጠው እግዚአብሔር ብቻ ነው። እግዚአብሔር በሰው ሕይወት ሁሉ ላይ ይፈርዳል። የሚል እንደሆነ አይተናል። ከፀሐይ በታች ያለው ነገር ሁሉ ጊዜያዊ ነው። ገንዘብ ጊዜያዊ ነው። ጉልበት ጊዜያዊ ነው። ስኬት ጊዜያዊ ነው። ንብረት ጊዜያዊ ነው። በምድር ላይ ያለው ሕይወት እንኳ ጊዜያዊ ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ብቻ ዘላለማዊ ነው።ስለዚህ ሕይወታችንን በሚታዩ ነገሮች ላይ ብቻ አንገንባ። ለንጉሡ እንኑር። እግዚአብሔርን እንፍራ። ትእዛዛቱን እንጠብቅ። በጊዜው እንመካ። ስጦታዎቹን በምስጋና እንቀበል።በፊቱ ለፍርድ ለመቆም እንዘጋጅ። እግዚአብሔር መንግሥቱን አስቀድመን እንድንፈልግ እና ለክብሩ በታማኝነት እንድንኖር ይርዳን።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.