የአገልግሎት ክፍሎች

የቤተክርስቲያኒቱ የአገልግሎት ክፍሎች እንቅስቃሴ

card-edge-2

የጸሎት አገልግሎት

በአጥቢያይቱ ውስጥ ያሉ አማኞች ሁሉ በጸሎትe ህይወታቸው እንዲያድጉና በግል ህይወታቸው የእግዚአብሔርን ህልውና (መገኘት) መለማመድ እንዲችሉ ከሰኞ እስከ አርብ ዘወትር ከ5-6 ኤም እና ሐሙስ ምሽት ከ8፡00-9፡00ፒ.ም የሚቆይ የጸሎት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

card-edge-3

የህንጻ ግዢ ገቢ አሰባሳቢ አገልግሎት

እየተጠቀምነበት ያለውን ህንጻ ለመግዛት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር በተለያየ መንገድ ገቢ በማሰባሰብ ያገለግላል፡፡

card-edge-7

የቤተክርስቲያኒቱ የመዝሙር አገልግሎት

በአጥቢያይቱ መደበኛ አገልግሎት ላይ ሰዎ እግዚአብሔርን እንዲያምልኩ፣ እንዲያመሰግኑና እንዲያከብሩ በዝማሬ አገልግሎት ህዝቡን ወደ እግዚአብሔ መገኘት ይመራሉ፡፡

card-edge-1

የአጥቢያይቱ አድቫይዘሪ ኮሜቴ

የቤተክርስቲያኒቱን አጠቃላይ የአገልግሎትና የሂሳብ እንቅስቃሴ በመምራት የአጥቢያይቱ አገልግሎት በተሳለጠ ሁኔታ እንዲፈጽም ይሰራል፡፡

card-edge-5

የአጥቢያይቱ የሚዲያ አገልግሎት

በአጥቢያ ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የሚሰጡ ትምህርቶች በተለያየ የአለማችን ክፍል ለሚገኙ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎ እንዲደርስ በማድረግ ሰዎች የመንግስቱን ወንጌል እነዲሰሙና ከሰህተት ትምህርት እንዲጠበቁ ከፍተኛ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡

card-edge-4

የልጆች አገልግሎት

የተለያዩ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ልጆችን በእድሜያቸው መጠን የትምህርት መርሃ ግብር በማዘጋጀት አመቱን ሙሉ እንዲማሩ ያደርጋል፡፡ ወላጆችን ከልጆች ጋር ለማቀራረብ እንዲያግዝ በማሰብ ለወላጆች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች በመስጠት ወላጆችን ያግዛል፡፡

card-edge-6

የአዋቂዋች አገልግሎት

የወንድሞችና የእህቶች አገልግሎት ተደራጅተው በአጥቢያይቱ ውስጥ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይሰጣሉ

  1. የፍቅር በተግባር አገልግሎት
  2. የጉብኝት አገልግሎት
  3. የወንጌል ስርጭት አገልግሎት
  4. በአጥቢያየይቱ መደበኛ አገልግሎት ውስጥ መሳተፍ