Home » Sunday sermon – July 21, 2024

በአእምሮቹ መታደስ ተለወጡ

Last updated on July 21, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ዓላማ:- እውነተኛ ለውጥ ምን ማለት እንደሆነ በቃሉ መሰረት ማስገንዘብ።

- እውነተኛ ለውጥ ለምን እንደሚያስፈልግ በቃሉ መሰረት ማስገንዘብ።

- ከዓለማዊነት ነፃ መውጣት የሚቻለው በእውነተኛ ለውጥ እንደሆነ ማረጋገጥ።

መግቢያ

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በሮም ለሚገኙ ቅዱሳን በተከታታይ ስለ መስረታዊ የድህነት ትምህርት ከነገራቸው በኃላ ከምዕራፍ እስር ሁለት በኃላ ግን ስለ ተግባራዊው ክርስትና ያሳስባቸዋል። ይህንንም የጀመረው “በአእምሮ የመታደስን” አስፈላጊነት በማሳሰብ ነው።እኛም ለትምህርታችን የተፃፈውን እውነት ቀጥለን እንመለከታለን።

1: በአእምሮ መታደስ መለወጥ ምንድ ነው?

1:1 ከነባራዊው ዓለም የአስተሳስብ ስርአት በተለየ ማሰብ መቻል ነው።

1:2 ተድላን ፣ ንብረትንና የኑሮ ደረጃን ከማሳደድ ማረፍ ነው።

1:3 ስር ነቀል የማንነት፣ የባህርይና የኑሮ ለውጥ ማድርግ ነው።

1:4 እግዚአብሔርን ከሚቃወመው ዓላም ሙሉ በሙሉ በተቃራኒ መቆም ነው።

2: በአእምሮ መታደስ መለጥ ለምን ያስፈልጋል?

2:1 እግዚአብሔርን ብቻ ማእከል ይደረግ አምልኮ/ አገልግሎት ለመስጠት

2:2 የእግዚአብሔርን ፈቃድ በርግጠኝነት ለማወቅ።

2:3 በዚህ ዓለም እየኖሩ ከዚህ ዓለም የአስተሳሰብና የኑሮ ስርዓት ለመለየት።

ማጠቃለያ

ክርስትና የማንነት፣ የአስተሳሰብ፣ የባህርይና የኑሮ ለውጥ ነው። ይህ አይነቱ ለውጥ ድግሞ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅና እግዚአብሔርን ብቻ ማእከል ያደረገ አምልኮ/አገልግሎት መስጠት ያስችላል። ስለዚህ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ።

Source: https://cmaeec.com/w...

bible-scaled-1
በአእምሮቹ መታደስ ተለወጡ

ክርስትና የማንነት፣ የአስተሳሰብ፣ የባህርይና የኑሮ ለውጥ ነው። ይህ አይነቱ ለውጥ ድግሞ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅና እግዚአብሔርን ብቻ ማእከል ያደረገ አምልኮ/አገልግሎት መስጠት ያስችላል። ስለዚህ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ።

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.