Home » Sunday sermon – September 22, 2024

የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት ወይስ በሌላ

Last updated on September 22, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ንባብ:-ሮሜ 4:1-25

ዓላማ

-የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት ብቻ የሚግኝ መሆኑን በቃሉ ማረጋገጥ
- በእምነት የእግዚአብሔርን ፅድቅ ማግኘት የብሉይና የሀዲስ ኪዳን ትምህርት መሆኑን በቃሉ ማረጋገጥ
- የእግዚአብሔር ፅድቅ ማንንና ምን በማመን እንደሚገኝ በቃሉ ማረጋገጥ

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት እንደተመለከትነው የእግዚአብሔርን ፅድቅ በተመለከተ በአይሁድና በአህዛብ መካከል ምንም ልዩነት እለ መኖሩን፣ ህግና ነቢያት የመሰከሩለት የእግዚአብሔር ፅድቅ ያለ ህግ መገለጡንና የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያፅድቅ አንድ አምላክ እንዳለ ተመልክተናል።በዛሬው ትምህርት ደግሞ የእግዚአብሔር ፅድቅ በብሉይም ሆነ በሀዲስ በእምነት ብቻ መሆኑን በቃሉ መሰረት እንማራለን።

1: በእምነት መፅደቅ በብሉይ ኪዳን

1:1 አብርሃም በእምነት እንጂ በስራ አለመፅደቁ ተነግሮአል።
1:2 መፀሀፍ አብርሃም በእምነት መፅደቁን አረጋግጦል።
1:3 በእምነት የፀደቀ ሰው ብፁዕ መሆኑን መፀሀፍ አረጋግጦአል።
1:4 ግርዘት በእምነት ለተገኘው እምነት ማህተም እንጂ ፅድቅ የሚገኝበት እንዳልሆነ ተረጋግጦል።
1:5 አብርሃም ከመገረዙ በፊት የነበረውን የእምነት ፈለግ የሚከተሉ ሁሉ እንደሚፀቁ ተረጋግጦአል
1:6 ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት መፅደቅ ነው እንጂ በህግ መፅደቅ እይደለም።

2: አብርሃም የፀደቀበት የእምነት አይነት

2:1 በተፃፈው የእግዚአብሔር ቃል ላይ ብቻ የተመሰረተ ነው።
2:2 በእግዚአብሔር ህይወት ሰጪነት ላይ በመታመን የተመሰረተ ነው።
2:3 በተስፋ ቃልና በተስፋ ሰጪው እግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ ነው።

3: በእምነት የሚገኘው የእግዚአብሔር ፅድቅ

3:1 ስለ እምነት የተቆጠረ የእግዚአብሔር ፅድቅ ነው።
3:2 በአብርሃም ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም
3:3 ስለበደላችን አልፎ የተሰጠውን ለሚያምን ሁሉ የሚቆጠር ነው።
3:4 እኛን ስለማፅደቅ ከሙታን የተነሳውን ለሚያምኑ ሁሉ የሚቆጠር ነው።
3:5 ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን አባቱ እንዳስነሳው ለሚያምን ሁሉ የሚቆጠር ነው።

ማጠቃለያ

መፀሀፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው የእግዚአብሔር ፅድቅ የሚገኘው በእምነት ብቻ ነው።ስለዚ አይሁድም ሆኑ
አህዛብ ስለበደላችን ታልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማፅደቅም ከሙታን የተነሳውን ኢየሱስን አባቱ ከሙታን እንዳስነሳው ሊያምኑ ያስፈልጋቸዋል። ይህን የሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ፅድቅ ልክ እንደ አብርሃም ይቆጠርላቸዋል።ከዚህ ወጪ ያለው ትምህርት ሁሉ ሀሰትና ምንፍቅና ነው። የእግዚአብሔር ፅድቅ በሀሰትና በምንፍቅና ትምህርት አይገኝም በእምነት
እንጂ።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.