Home » Sunday sermon – November 17, 2024

በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅ

Last updated on November 17, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ለሞት ከተሰጠ ሰውነት መዳን

ንባብ:- ሮሜ 7:13-25

ዓላማ

-በአማኝ ህይወት ውስጥ የሚከናወነው ትግል ለምን እንደሆነ በቃሉ መሰረት ማወቅ።
- ለሞት የተሰጠ ሰውነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በቃሉ መሰረት መረዳት።
- አማኝ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት የሚድንበትን መንገድ በቃሉ መሰረት መረዳት።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት እንደተመለከትነው አማኝ ከህግ እስራት አርነት የሚወጣው ህግን በመፈፀም ለመፅደቅ በመታገል
ሳይሆን በክርስቶስ ስጋ ለህግ በመግደል መሆኑን ነበር። በዛሬው ትምህርት ደግሞ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ስለ መዳን
እንማራለን።

1: ለሞት የተሰጠው ሰው ማነት

1:1 በህጉ አማካይነት ኃጢአተኛ የሆነውና የሞተው ተፈጥሮ ቁ 13
1:2 ከህግ የተነሳ ለኃጢአት ባርነት የተሸጠ ስጋ ቁ 14
1:3በዳነው ሰው የሚኖር ኃጢአት ቁ 18;20

2: ለሞት የተሰጠው ሰውነት መግለጫዎች

2:1 የውስጥ ሰውነት የማይፈልገውን ማድረግ ቁ 15-20
2:2 ፈቃድ ቢኖረውም መልካም ለማድረግ አለመቻል
2:3 ከአእምሮ ህግ ጋር በሚዋጋ የኃጢአት ህግ የውስጥ ሰውነትን መዋጋት

3: ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ለመዳን:-

3:1 በውስጡ ሰውነት በእግዚአብሔር ህግ መደሰት።
3:2 በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን ማመስገን
3:2 በአእምሮአችን ለእግዚአብሔር ህግ መግዛት
3:3 በስጋችን ለኃጢአት ህግ መገዛት

ማጠቃለያ

በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ ያገኘ ሰው ድኖአል። ከዚህ የነሳ በህይወቱ ውስጥ ትግል አለ። ይህም ትግል በዳነው ማንነትና በኃጢአተኛው ተፈጥሮ መካከል የሚደርግ ትግል ነው። አማኝ በኃጢአተኛው ተፈጥሮ ከሚደርስበት ተፅኖ በመዳን እንደ ፃድቅ ስው ለመኖር በእግዚአብሔር ህግ መደሰት፣ እግዚአብሔርን በክርስቶስ ኢየሱስ ማመስገን ፣ በአእምሮው ለእግዚአብሔር ህግ መገዛትና በስጋው ለኃጢአት ህግ መግዛት አለበት። ይህ ለሞት ከተሰጠ ሰውነት የሚዳንበት መንገድ ነውና።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.