ያለኩነኔ በመንፈስ መኖር
የንባብ ክፍል ሮሜ 8:1-11
መግቢያ
በቀደመው ትምህርት ከህግ እስራት ነፃ ስለመውጣትና ለሞት ከተሰጠ ሰውነት ስለ መዳን ተምረናል።በዛሬው
ትምህርት ደግሞ ያለኩነኔ በመንፈስ ስለ መኖር እንማራለን።
1: ከኩነኔ እንዴት ነፃ መሆን ይቻላል? ሮሜ 8:4
1:1 በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆን።
1:2 ከኃጢአትና ከሞት ህግ አርነት በመውጣት።
1:3 ኃጢአት በስጋ እንደ ተኮነነ በማመን።
2: ከኩነኔ ነፃ የሆኑ እንዴት ይኑሩ? ሮሜ8:5-8
2:1 እንደ መንፈስ ፈቃድ በመመላለስ።
2:2 ስለ መንፈስ በማሰብ።
2:3 የስጋን ፈቃድ ባለመፀም።
2:4 የስጋን ሀሳብ ባለማሰብ።
3: ከኩነኔ ነፃ የመሆን ማረጋገጫ ምንድነው? ሮሜ8:9-11
3:1 በመንፈስ መሆን መቻል።
3:2 ክርስቶስ በውስጣችን በመሆኑ።
3:3 ከመንፈስ ህይወትን በማግኘት።
ማጠቃለያ
ሐዋርያው ጳውሎስ ከሮሜ1-5 በእምነት ስለመፅደቅ ፣ከ6-8 ደግሞ በእምነት የፀደቀ ሰው እንዴት መኖር እንዳለበት አስተምሮአል ። በዚህ በሁለተኛው ክፍል ከተብራራው እውነት አንዱ ከኩነኔ ነፃ መሆንና በመንፈስ የመኖር እውነት ነው። ይህን እውነት የራሳችን ለማድረግ ከኩነኔ ነፃ የሆንበትን እውነት ማወቅ፣ከኩነኔ ነፃ የሆነው በመንፈስ ለመመላለስ መሆኑን መገንዘብና ከኩነኔ ነፃ መሆናችንን ማረጋገጥ ያስፈልግናል።ለዚህም ቃሉን ማመን።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.