- በእምነት የፀደቁ የእግዚአብሔር ልጆች የስጋን ስራ የመግደል ሀላፊነት አለባቸው። - በእምነት የፀደቁ የእግዚአብሔር ልጆች እግዚአብሔር አብን አባት ብለው መጥራት. ይችላሉ። - በእምነት የፀደቁ የእግዚአብሔር ልጆች የእግዚአብሔር ውራሾች ናቸው።
በቀደመው ትምህርት እንደተመለከትነው በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉ ሁሉ አሁን ኩነኔ የለባቸውም። በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የህይወት መንፈስ ህግ ከኃጢአትና ከሞት ህግ አርነት አውጥቶአቸዋልና።በዛሬው ትምህርት ደግሞ በወንጌል የተገለጠው የእግዚአብሔር ፅድቅና የእግዚአብሔር ልጅነትን ልክ እንመለከታለን።
1:1 እንድ ስጋ ፈቃድ ያለመኖር ዕዳ አለባቸው። 1:2 የስጋን ስራ በመንፈስ የመግደል ዕዳ አለባቸው።
2:1 በእግዚአብሔር መንፈስ ይመራሉ። 2:2 እግዚአብሔር አብን አባት ብለው መጥራት ይችላሉ። 2:3 መንፈስ ቅዱስ ልጅነታቸውን ያረጋግጥላቸዋል።
3:1 የእግዚአብሔር ወራሽነት የልጅነት መብታቸው ነው። 3:2 ከክርስቶስ ጋር ጋር ይከብራሉ። 3:3 ከክርስቶስ ጋር አብረው ይወርሳሉ።
በወንጌል የተግለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት የተቀብሉ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆናሉ። ልጆች የሆኑ ሁሉ የስጋን ስራ በመንፈስ የመግደል እዳቸውን ይወጣሉ።ደግሞም በእግዚአብሔር ልጅነታቸው ልክ ይመላለሳሉ። በዚህ ልክ ልጆች ስለሆኑ ከክርስቶስ ጋር አብረው የእግዚአብሔር ወራሾች ይሆናሉ።በወንጌል የገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት ተቀብለዋልና።
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.