Home » Sunday sermon – December 22, 2024

በወንጌል የተገለጠው ፅድቅና

Last updated on December 22, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

የአሁኑ ዘመን መከራ

የንባብ ክፍል:- ሮሜ 8:18-27

ዓላማ

- በእምነት የፀደቁ አማኞች ከመከራ ነፃ አለመሆናቸውን ማሳሰብ።
- በእምነት የፀደቁ አማኞች ከአሁኑ ዘመን መከራ ይልቅ ተስፋቸው ላይ እንዲያተኩሩ ማሳሰብ።
- በእምነት የፀደቁ አማኞች በመከራ ውስጥ ሲያልፉ መንፈስ ቅዱስ እንደሚረዳቸው ማረጋገጥ።

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት በእምነት የፀደቁ የእግዚአብሔር ልጆች በመንፈስ ቅዱስ ስጋን የመግደል እዳ እንዳለባቸው፤ እንዲሁም በዚህ ምድር ምልልሳቸው በመንፈስ ቅዱስ በመመራት እንደሆነ እና ከክርስቶስ ጋር ወራሾች መሆናቸውን ተመክተናል። በዛሬው ትምህርት ደግሞ በእምነት የፀደቁ አማኞች የአሁኑን ዘመን መከራ እንዴት እንደሚያሸንፋትና በመንፈስ ቅዱስ ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ መታመን እንማራለን።

1: የፀደቁ አማኞች በአሁኑ ዘመን መከራ የሚቀበሉበት ምክንያት

1:1 በዚህ በወደቀ ዓለም ውስጥ ስለሚኖሩ። ዮሐ 16:33
1:2 እምነታቸው ስለሚፈተን። 1 ጴጥ 1:6-7
1:3 የክርስቶስ አገልጋዮች ስለሆኑ። 2ቆር 11:22-29
1:4 በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ስለሚኖሩ። ማቴ 24:9-25

2: አማኞች የሚንቁበት ምክንያቶች። ሮሜ 8:19-25

2:1 ሊገለጥላቸው ያለው ክብር ታላቅ ስለሆነ።
2:2 የሰውነታቸው ቤዛ የሆነውን ልጅነት ተስፋ ስለሚያደርጉ።
2:3 የእግዚአብሔር ልጅነት ደረጃዎች:-
2:3:1 በእግዚአብሔር ሀሳብ አስቀድሞ መወሰን። ኤፌ 1:5
2:3:2 አሁን ያገኝነውና የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን የተቆጠርንበት። ገላቲ 3:26 ሮሜ 8:14
2:3:3 በክርስቶስ. ያገኘነውን ውርስ ሙሉ በሙሉ የምንረዳበት። ሮሜ 8:23
2:4ተስፋቸውን ለመያዝ በመንፈስ ቅዱስ ስለሚቃትቱ።

3: የመንፈስ ቅዱስ ስራ እማኞች በመከራ ሲልፉ

3:1 በድካማቸው ያግዛቸዋል።
3:2 ስለ እነርሱ ይቃትታል/ይማልዳል።
3:3 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ያስታውቃቸዋል።

ማጠቃለያ

አማኞች በዚህ ዓለም ሲኖሩ ከመከራ ነፃ እንደሚሆኑ መፀሀፍ ቅዱስ አያስተምርም። ነገር ግን በመከራ እንዳይሸነፉ ማድረግ ያለባቸውን ያሳስባቸዋል።በዚህ መሰረት ዛሬ በተለያየ መከራ ውስጥ የምናልፍ አማኞች በመከራችን ላይ ሳይሆን ትኩረታችን በተስፋችን ላይ እናድርግ ። ያኔ መከራችን ይሸነፋል።ደግሞም በመንፈስ ቅዱስ ላይ እንታመን እርሱ ስለኛ ይማልዳልና። ለኛ ሊገለጥ ካለው ክብር ጋር ሲመዛዘን የአሁን ዘመን ስቃይ ምንም አይደለም!!!!

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.