Home » Eve sermon – December 31, 2024

በፊታችን ያለውን ሩጫ በትግስት እንሩጥ!!

Last updated on December 31, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

የንባብ ክፍል:- ዕብ 12:1-6

ዓላማ

- በአዲሱ ዓመት ትኩረታችንን በኢየሱስ ላይ እንዲያደርጉ ማሳሰብ።
- በአዲሱ ዓመት በፊታቸው ያለውን ሩጫ በትግስት እንዲሮጡ ማሳሰብ።
- ትኩረታችንን በኢየሱስ ላይ የማድረግ አስፈላጊነትን ማሳሰብ።

መግቢያ

ሰወች አዲስ አመት በመጣ ቁጥር ሁለት ነገሮችን ያደርጋሉ ይህም ባለፈው አመት የመጡበትን መንግድ መገምገም እና ሰለአዲሱ አመት ምሪት ማግኘት ወይም ማቀድ ነው ።ስለዚህ እኛም መጪውን አመት በተመለከተ ከቃሉ ምሪትን ለማግኘት ወይም ለማቀድ እንድንችል የሚከተሉትን የቃሉን መርሆዎች እከተል።

1: ሩጫችንን ለመሮጥ በዙሪያችን ያሉ ምስክሮችን ማየት

1:1 በእምነታቸው የተመሰከራላቸው ናቸው።
1:2 የተሰጠውን የተስፋ ቃል ገና ያላገኙ ናቸው።
1:3 ያለኛ ፍፁማን ያልሆኑ ናቸው።

2: ለመሮጥ እንድንችል ምን እናድርግ?

2:1 ማስወገድ ያለብንን ሁሉ እናስወግድ

2:1:1 ሸክምን ሁሉ ማስወገድ
2:1:2 ቶሎ የሚከበንን ኃጢአት ሁሉ ማስወገድ።

2:2 የእምነታችንን ራስና ፈፃሚ መመልከት።

2:2:1 በፊቱ ስላለው ደስታ ነውርን ናቀ።
2:2:2 በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀልን ታግሰ።
2:2:3 በኃጢአተኞች በደረሰበት ተቃውሞ ፀና።
2:2:4 በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀመጠ።

3: ኢየሱስን የመመልከት ውጤት ምንድ ነው?

3:1 በነፍሳችን ዝለን እንዳንወድቅ ያደርገናል።
3:2 ከኃጢአት ጋር መጋደልና ኃጢአትን መቃወም ያስችለናል።
3:3 በልጅነት የህይወት ስርዓት መኖር ያስችለናል።

ማጠቃለያ

በዚያ ዘመን የነበሩ አማኞች የገጠማቸውን ተግዳሮት እልፈው በፊት ለፊታቸው ያለውን ሩጫ ሮጠው እንደጨረሱ፤እኛም ሩጫችን ለመሮጥና ለመጨረስ በዙሪያችን ያሉ ምስክሮችን ተመልክተንና የእምነታችንን ራስና ፈፃሚ ምሳሌ አርገን በፊታችን ያለውን ሩጫ በ2025 እንሩጥ። በነፍሳችን ሳንዝል ኃጢአትን በተጋድሎ በመቃውም እንድ እግዚአብሔር ልጆች እንድንኖር ጌታ አመቱን ይሰጠን!!!!!

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.