-በፍጥረታዊውና በመንፈሳዊው ሰው መካከል ያለውን ልዩነት በቃሉ ማሳየት። -እውነተኛው መንፈሳዊነት መፀሀፍ ቅዱሳዊ እንደሆነ ማረጋገጥ። -የእግዚአብሔርን ጥበብ ማግኘት ለእነተኛው መንፈሳዊ ሰው ብቻ እንደሆነ ማረጋገጥ።
የእግዚአብሔር ጥበብ ከዚህ ዓለም ጥበብ የተለየ እና የዚህ አለም ግዥዎች የማያውቁት መሆኑን፤እንዲሁም እግዚአብሔር ለሚወዱት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚሰጣቸው መሆኑን ተምረን ነበር።በዛሬው ትምህርት ደግሞ ይህን በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠውን የእግዚአብሔር ጥበብ ማን መቀበል እንደሚችል እንመለከታለን።
1:1:1 መንፈስ ቅዱስ የለውም። 1:1:2 ከመንፈስ ቅዱስ የሆነውን ነገር መቀበል አይችልም። 1:1:3 ከመንፈስ ቅዱስ የሆነው ነገር ለርሱ ሞኝነት ነው። 1:1:4 ከመንፈስ ቅዱስ የሆነውን ነገር አይገነዘብም።
1:2:1 መንፈስ ቅዱስ አለው። 1:2:2 በመንፈስ ቅዱስ የመንፈስ ቅዱስን ነገር ይመረምራል። 1:2:3 እርሱ በማንም አይመረመርም። 1:2:4 የክርስቶስ ልብ/አዕምሮ አለው።
2:1 በክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ጋር መግናኘት ነው። ዮሐ 14:6 2:2 በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መሞላት ነው። ሐዋ ሉቃ 24:49, ሐዋ1:8 2:3 በቅዱስ ቃሉ መመራት ነው።መዝ 119:105,9 2:4 በአእምሮ መታደስ መለወጥ ነው። ሮሜ 12:2 2:5 በመታዘዝ የሚገለጥ እምነት ነው።ያዕ 2:14
የእግዚአብሔርን ጥበብ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለመቀበል መንፈሳዊ ስው መሆን ይጠይቃል።ስለዚ መንፈሳዊ ሰው ለመሆንና የእግዚአብሔርን ጥበብ በመንፈስ ቅዱስ ለመቀበል በፍጥረታዊውና በመንፈሳዊ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት በቃሉ መሰረት መለየት እና በመንፈሳዊነታችን ላይ እርግጠኛ መሆን ይጠይቅል። በቀጣይነትም ወደ እውነተኛውና መፀሐፍ ቅዱሳዊ ወደሆነው መንፈሳዊነት በቃሉ መሰረት መግባት ያሰፈልግል። ይህን በተመለከተ ሳምንት እንማራልን።
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.