ትምህርት ሦስት:- የእግዚአብሔርን መንፈስ ለመቀበል ምን እናድርግ?
ዓላማ
- የእግዚአብሔርን መንፈስ የመቀበልን አስፈላጊነት በቃሉ ማረጋገጥ
- የእግዚአብሔርን መንፈስ መቀበል የሚቻልበትን መንገድ በቃሉ ማመላከት።
መግቢያ
የእግዚአብሔርን ጥበብ ለመካፈል ያለ መንፈስ ቅዱስ እንደማይቻል እና ለፍጥረታዊው ሰው የእግዚአብሔርን መንፈስን ጉዳይ ሊረዳውም ሆነ ሊቀበለው እንደማይችል በቀደመው ትምህርት ተመልክተናል።ዛሬ ደግሞ የእግዚአብሔርን መንፈስ ስለመቀበል በመፀሀፍ ቅዱስ ትምህርት መሰረት እንመለከታለን።
1: ስለኢየሱስ ማንነትና ማዳን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ማመን። ዮሐ 3:3-18 16:7 7:37-39
1:1 ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ማመን
1:2 በኢየሱስ አዳኝነት ብቻ ማመን።
1:3 ኢየሱስ የሰጠውን ተስፋ ማመን።
2: እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን እንዲሰጠን በእምነት መለመን።
2:1 በእምነት ለሚለምኑ መንፈስ ቅዱስ ይሰጣል ሉቃ 11:13
2:2 ያለመጠራጠር የሚለምን ይቀበላል። ያዕ 1:6
2:3 እግዚአብሔርን ለሚታዘዙ መንፈስ ቅዱስ ይሰጣል ሐዋ 5:32 ዮሐ 14-15-17
3: በህብረት ፀሎት ያለማቋረጥ መትጋት
3:1 በወንጌል ተልዕኮ በማህበር መፀለይ ሐዋ 5:32
3:2 በእውነተኛ እምነት ለመታነፅ በማህበር መፀለይ ይሁዳ 20
ማጠቃለያ
ዛሬን ጨምሮ ለሶስት ተከታታይ ሳምንታት በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔርን ጥበብ ስለመካፈል ተምረናል። ትኩረታችንም የነበረው የእግዚአብሔርን ጥበብ በመንፈስ ቅዱስ የመካፈልን አስፈላጊነት መገንዘብ፣ መንፈሳዊው ሰውና ፍጥረታዊው ሰው ያላቸውን ልዩነት ማወቅና ዛሬ እንደተመለከትነው መንፈስ ቅዱስን ለመቀበል ምን ማድረግ አለብን የሚለው እውነት አይተናል። እንግዲህ እነዚህን እውነቶች መገንዘብ እና በእምነት መለማመድ ለመንፈሳዊነታችን ወሳኝ ስለሆነ ትኩረት ልናድርግባቸው ይገባናል።
Source: https://cmaeec.com/w...

John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.