- አማኞች የመንፈስ ቅዱስንም ሆነ የአማኝን ማንነት በቃሉ መሰረት ማውቅ አለባቸው። - አማኞች ከመንፈስ ቅደስ ጋር በቃሉ መሰረት እንዴት ተግባቧት ማድረግ እንደሚችሉ ማሳሳብ - አማኞች በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መንፈሳዊ ህይወትን መኖርና እግዚአብሔርን ማገልገል ይችላሉ።
አማኞች በዚህ አለም ሲኖሩ እግዚአብሔርን የሚስከብር ህይወት መኖርና እግዚአብሔርን ማገልገል ይጠበቅባቸዋል። ነገር ግን እነዚህን ነገሮች በራሳቸው ማድረግ ደግሞ አይችሉም ።ስለዚህ መንፈስ ቅዱሳን መተዋወቅ እና በርሱ መታገዝ ያስፈልጋቸዋል።ይህንንም ለማድረግ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የመተዋወቅን ትርጉም ፣ የመንፈስ ቅዱስን ማንነት እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስን እና የአማኞችን ማንነት በቃሉ ልክ ማወቅ ያስፈልጋቸውል። እኛም ይህን እውነት ቀጥለን እንመለከታለን።
1:1 ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንደምንኖር ማወቅ ነው። 1:2 መንፈስ ቅዱስ አፅናኛችን እንደሆነ ማወቅ ነው። 1:3 መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን እንዳለ ማውቅ ነው።
2:1:1 መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ሐዋ 5:3-4 2:1:2 መንፈስ ቅዱስ የስላሴ አካል ነውና ማቴ 28:19-20 2:1:3 መንፈስ ቅዱስ እኔ ባይ አካል ነው። ዮሐ 16:25-26 2:1:3 መንፈስ ቅዱስ እውቀት፣ፈቃድና ስሜት ያለው አካል ነው።1ቆሮ 2:10-11,12:11 ኤፌ 4:30; ሮሜ 8:9
2:2:1 የእግዚአብሔር ቤተመቅደሶች ናቸው። 2:2:2 የመንፈስ ቅዱስ መኖሪያዎች ናቸው። 2:2:3 ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ ቅዱሳን ናቸው። 2:2:4 ከመንፈስ ቅዱስ የተነሳ መንፈሳውያን ናቸው። 2:2:5 የአማኝ ስጋው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ነውና።
እንደ አዲስ ኪዳን ትምህርት ከሆነ አማኞች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር መተዋወቅ ይችላሉ። ለዚህም በመጀመሪያ ከመንፈስ ቅደስ ጋር የመተዋወቅን ትርጉም በቃሉ መሰረት ማውቅ እና የመንፈስ ቅዱስንና የአማኙንም ማንነት በቃሉ ልክ ማወቅ ያስፈልጋቸዋል።ስለዚህ ቃሉ የሚለውን ማውቅ ማመንና መታዘዝ ከመንፈስ ቅደስ ጋር ለመተዋወቅ ወሳኝ ነው። ስለሆነም ቃሉን እንወቅ እንመን እንታዘዝ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንተዋወቃለንና።
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.