ትምህርት ሶስት፦ በቅድስና እና በመንፈሳዊ ኃይል ማደግ
ዓላማ
- አማኞች መንፈስ ቅዱስን መቀበላችውን የሚያረጋግጡበትን እውነት በቃሉ ማሳየት።
- መንፈስ ቅዱስን የመቀበል ሁለተኛውን ገጽታ በቃሉ ማሳየት።
- በመንፈስ ቅዱስ መቀድስና የመንፈስ ቅዱስን ሀይል መሞላትን አንድነትና ልዩነት በቃሉ ማረጋገጥ።
መግቢያ
ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን ያገኛችውን አማኞች የጠየቃቸው መሰረታዊ ጥያቄ “ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን” የሚል ነበር ለዚሀም ምክንያቱ መንፈስ ቅዱስን መቀብል የእውነተኛ አማኝነት ማስረጃ ስለሆን እና ሌላው ደግሞ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንዲችሉ ሊርዳቸው ነበር። እኛም ይህን መሰርት አድርገን መንፈስ ቅዱስን የመቀበልን ማስረጃ ሁለተኛውን ገጽታ በዚህ ትምህርት እንመለከታልን።
1፡ መቀደስና ቅዱስ መሆን
1:1 መቀደስ በባህሪ እና በምግባር ኢየሱስን የመምሰል የህይወት ዘመን ሂደት ነው።
1:2 በመዳን ይጀምራል አማኙ በታዛዥነትነ በቅድስና ሲያድግ ይቀጥላል ቅዱስ መሆን።
1:3 የመንፈስ ቅዱስ ሚና በቅድስና ቅዱስ በመሆን ውስጥ 1ኛ ቆሮንቶስ 6:11,2ቆሮ 3:18፣ገላትያ 5:22-23
1፡3:1 በድኅነት ይለየናል።
1:3:2 ባህሪያችንን ይለውጣል
1:3:3 ወደ ክርስቶስ መልክ መለወጥ የመንፈስ ስራ ነው።
1:3:4 በውስጣችን ቅዱስ ፍሬ ያፈራል።
2፡ በመንፈስ ቅዱስ መቀደስና በኃይል መኖር 1ኛ ተሰሎንቄ 4፡3; የሐዋርያት ሥራ 1፡8፣ሮሜ 8:13-16
2:1 የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመኖር ኃይል ይሰጠናል።
2:2 የስጋን ስራ በመግደል በህይወት ያኖርናል።
2:3 በዕለት ተዕለት ኑሮአችን እርሱ ይመራናል።
2:4 የእግዚአብሔር ልጅነታችንን ያረጋግጣል።
2:5 ለማገልገል እና ለመመስከር መለኮታዊ ጥንካሬን ይሰጠናል።
3፡ መቀደስና በኀይል መሞላት አብረው ሲስሩ
3:1 ለቅድስና ኀይልን ማግኘት ይሆናል።
3:2 ውስጣዊ ንፅህና እና ውጫዊ ኃይል ማግኘት ይሆናል።
3:3 በመንፈስ ቅዱስ መሰራትና የመንፈስ ቅዱስ መሳሪያ መሆን ።
3:4 የመንፈስ ፍሬን ማፍራትና ስጦታዎችን መለማመድ ይሆናል።
ማጠቃለያ
አማኝ መንፈስ ቅዱስን የመቀበሉ ጉዳይ ምርጫ ሳይሆን የግድ ነው።ምክንያቱም መንፈስን መቀበል የእውነተኛ አማኝነት ማረጋገጫ ነውና።ለዚህ ነበር ሐዋርያው በኤፌሶን ያገኛቸውን አማኞች “ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን”? ብሎ የጠቃቸው።መንፈስ ቅዱስን መቀበል የሚረጋገጠው ደግሞ እርሱ በህይወታችን ውስጥ በሰራውና በቀጣይነት በሚሰራው ስራ ነው።ይህም በዳግም ልደት ይጀምርና በቀጣይነት ደግሞ እየቀደሰ በሀይል ይሞላናል።ስለዚሀ ክርስትና በመንፈስ ቅዱስ ዳግም መወልድ፣በመንፈስ ቅዱስ ያለማሰለስ መቀደስ እና በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች በሚገለጥ የመንፈስ ቅዱስ ኀይል እየተሞሉ መኖር ነው። ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀበላችሁን የሚለው ጥያቄም የሚፈልገው መልስ ይህንን ነው።
Source: https://cmaeec.com/w...

John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.