- አማኞች የእግዚአብሔር መግስትን ጽንሰ ሀሳብ በቃሉ መሰረት እንዲገነዘቡ ማድረግ። - እግዚአብሔር በግለሰብ ህይወትና በህዝቦች ታሪክ ውስጥ የሚሰራው ከመንግስቱ አንጻር እንድሆነ ማመላከት። - የእግዚአብሔር መንግስት ርምደታዊነት መጸሕፍ ቅዱሳዊ እውነት መሆኑን ማረጋገጥ።
የእግዚአብሔር መንግሥት ጽንሰ-ሐሳብ በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ድረስ አንድ ወጥ ጭብጥ ሆኖ ነው የሚሄደው። ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር መንግስት የመጸሐፍ ቅዱስ ዋና ትምህርት መሆኑን ተገንዝበን ለርዕሰ ጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት እንድንሰጥ የሚያሳስበን ይሆናል።ስለዚህ የእግዚአብሔርን መንግስት ርምድታዊ ሂድት ለማየት የሚረዳ ግልጽና የተዋቀረ አጠቃላይ እይታን በዚህ ትምህርት እንመለከታለን።
1:1 እግዚአብሔር እንደ ንጉስ በፍጥረት ላይ አገዛዙን መስርቶአል ዘፍ 1-2 1:2 እዚአብሔር አገዛዙን በእራኤል ላይ አድርጎአል ዘጸአት 19:6 1:3 እስራኤል የሰው ልጅ መንግስት ብትጠይቅም ንጉሳቸው መሆኑን አሳስቦአቸዋል 1 ሳሙ 8–10 1:4 የሰውልጅ የዘላለም መንግስት እንደሚቀበል በትንቢት ታወጀ መዝ103:19፣ዳን 7፡13–14
2:1 ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት ሰበክ ማቴዎስ 4:17 2:2 ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግስት አስተማር ማቴዎስ 4:17 2:3 ኢየሱስ በሞቱና በትንሳኤው ሰወችን ወደ አባቱ መንግስት ቆላስይስ1:13, 2:4 ኢየሱስ የመንግስቱን ስብከት ለቤተክስቲያን ሰጠ, የሐዋ ሥራ 1:1-5, 28:31 2:5 ሐዋርያቱ የመንግስቱን ፍጻሜና የወደፊት አገዛዝ አስተማሩ ራእይ 11:15
የእግዚአብሔር ሉዓላዊነት በነገሮች ሁሉ ላይ ነው። እግዚአብሔር የሚገዛው በሰማይና በምድር ያሉትን ሁሉ ነው። እግዚአብሔር ገዢነት በአሁኑና ወደፊት ባሉ ነገሮች ሁሉ ላይ ነው። ይህ የእግዚአብሔር አገዛዝ ማለት የእርሱ የላቀ ሥልጣን፣ ኃይል እና ቁጥጥር ማለት ነው። በእግዚአብሔር መንግሥት ትምህርት አውድ ውስጥ ይህ በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን ውስጥ የምናገኘው ዋናው እውነት ነው።ይህን ስንርዳ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት በመቀበል፣ በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር የኛን ኃላፊነት በመወጣት፣የንስሐ እና የእምነት ግብዣን አክብረን በክፉ ላይ የሚፈጸመውን የመጨረሻ ድል እና ሙሉ የፍጥረት መታደስ በመናፍቅ እንኖራልን።
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.