ትምህርት አራት፦ ንሰሐ የመንግስቱ መርህ
አላማ
• የንሰሀን ምንነት ማወቅ እና መተግበር የሚያስፈልግበትን ምክንያት በቃሉ መሰረት ማሳየት።
• ንስሀና የእግዚአብሔር መንግስት ያላቸውን ግንኙነት በቃሉ መሰረት ማሳየት።
• ንሰሀ የመንግስቱ የመጀመሪያ መርህ የሆነበትን ምክንያት በቃሉ ማሳየት።
መግቢያ
የእግዚአብሔር መንግሥት መርህ በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት ብቻ የሚወሰን ነው።በመሆኑም የመንግስቱ የመጀመሪያ መርህ የሆነውን ንስሐንና ከንሰሀ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን መርሆች በዚሀ ተምህርት እንመልከታለን።
1: መጽሐፍ ቅዱሳዊ የንስሐ ትርጉም
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረው ንስሐ መግባት ማለት ሥር ነቀል የልብ፣ የአስተሳሰብ እና የአቅጣጫ ለውጥ ማድረግ ማለት ሲሆን ይህም ከኃጢአት መራቅ እና ወደ እግዚአብሔር መዞር/መመለስ ማለት ነው።
አዲስ ኪዳን በተጻፈበት የመጀመሪያ የግሪክ ቋንቋ ንስሐ የሚለው ቃል “ሜታኖያ” ሲሆን ትርጉሙም፦"የአስተሳሰብ ለውጥ" ማድረግ ማለት ሲሆን ይህም በተለየ መንገድ ከማሰብ የበለጠ ጥልቅ ነው።
ንሰሀ የልብ ለውጥ ስለ ኃጢአት ማዘንንና የአእምሮ ለውጥ ማድረግን ፣ ኃጢአትን እግዚአብሔር በሚያየው መንገድ ማየትና የሕይወት ለውጥ ማድረግን እንዲሁም ከኃጢአት መመለስ እና ለቅዱስ ቃሉ ሙሉ በሙሉ በመታዘዝ መሄድን ያካትታል። (2ኛ ቆሮንቶስ 7:10)
2፡የንስሐ ሦስት ቁልፍ ክፍሎች
2:1 መናዘዝ
ኃጢአትህን በእግዚአብሔር ፊት በሐቀኝነት መቀበል። "በኃጢአታችን ብንናዘዝ ይቅር ሊለን የታመነና ጻድቅ ነው" (1ኛ ዮሐንስ 1:9)
2:2 ማዘን
ለኃጢያት አምላካዊ ሀዘን መሰማት። "እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ወደ መዳን የሚያደርሰውን ንስሐ ያመጣል..." (2ኛ ቆሮንቶስ 7:10)
2:3 መለወጥ
አቅጣጫ መቀየር እና ወደ እግዚአብሔር መመለስ"እንግዲህ ንስሐ ግቡ ኃጢአታችሁም ይደመሰስ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ" (የሐዋርያት ሥራ 3:19)
3:ከንስህ ጋር የሚገናኙ የእግዚአብሔር መንግስት መሰረታዊ መርሆች
1. እምነት
ንስሐ ለእምነት መሬቱን ያጸዳል።በራሳችን፣ ወይም በአለም ላይ ከመታመን እንመለሳለን፣ በእግዚአብሔር ወደመታመን እንሄዳለን። በማርቆስ 1፡15 ኢየሱስ እንዲህ ይላል።“ንስሓ ግቡ በወንጌል እመኑ!”ንስሃ እና እምነት የማይነጣጠሉ ናቸው።በእምነት የሚደረግ ንሰሀ አንዱ ከቀደመው መንገድ መመለስ ነው ሌላኛው ወደ እግዚአብሔር አገዛዝ መዞር ነው።
2. መታዘዝ
እምነት በተፈጥሮአችን ላይ ታዛዥነትን ይፈጥራል።እግዚአብሔርን እንደ ንጉሥ ስናመ፣ የተናገረውን እናደርጋለን ይህም በፍርሃት ሳይሆን በፍቅር እና በታማኝነት የሚሆን ነው።ምክንያቱም የሚያድነው እምነት በመታዘዝ የሚገለጥ ስለሆነ።ያእቆብ 2፡17 ከስራ የተለየ እምነት የሞተ መሆኑን ያሳስበናል። በመንግሥቱ ውስጥ፣ እውነተኛ እምነት ራሱን በመታዘዝ ይገጣል።
3. ጽድቅ
በማቴዎስ 6፡33 ላይ ኢየሱስ እንዲህ ይላል።" አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል”።ጽድቅ ሁለት ገጽታዎች አሉት የመጀመሪያው በክርስቶስ ኢየሱስ አዳኝነት በማመን ብቻ የሚቆጠርልን የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው።ሁለትኛው ገጽታው ድገሞ በእምነት ስለጸደቅን የእግዚአብሔርን ቃል በመታዘዝ ባህሪያችንና ኑሮአችን ወደ ጽድቅ የህይወት ስርዓት መቀየሩ ነው።
4. የመንግሥቱ ሕይወት
ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስ የሆነ ደስታን መለማመድ ነው። ይህ የህይወት ስራት ለሌሎች ምስክር ይሆናል እናም ወደ ንጉሡ ይስባቸዋል። ሮሜ 14፡17
ማጠቃለያ
ንስሐ መግባት በበደል ማዘን ብቻ አይደለም። ወደ እግዚአብሔር መንግሰት መጨመርና ወሳኝ የሆነ የማንንነትና የባህርይ ለውጥ ማድረግ ነው። ንሰሀ በመንግሥቱ ውስጥ የእምነት፣ የለውጥ እና የዜግነት በር ይከፍታል። በሌላ አባባል በመንግሥቱ መሠረታዊ ሥርዓቶች ከመኖርህ በፊት በመጀመሪያ ለንጉሡ መገዛትን መምረጥን ይጠይቃል። የእግዚአብሔር መንግስት በሩ ንስሐ ነው። መድረሻውም ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር አገዛዝ ስር ያለ ህይወት ነው። ንስሐ → እምነት → መታዘዝ → ጽድቅ → የመንግሥቱ ሕይወት የመንግስቱ ቀዳሚ መርህ ነው።
Source: https://cmaeec.com/w...

John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.