ይህ ጥያቄ በብዙ ወገኖች ዘንድ ያለ ጥያቄ ነው። ደግሞም በተወሰነ መልኩ ብዙ ወገኖች ግራ የሚጋቡበትና መልስ የሚሹለት ጥያቄም ነው።ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ መልስ የሚሆነን እውነት በግልጽ ያስተምረናልና። ይህንንም ቀጥለን እንመልክታልን።
ጸሎት የሚጸልየው ወደ አብ ነው ።በቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት መሰረት ጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ነው።በዚህ መቅረብ ውስጥ የጸሎት ተደራሲ ወይም የጸሎታችን አቅጣጫ ወደ እግዚአብሔር አብ ነው። ጌታችን ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱን እንዴት መጸለይ እንዳለባቸው ባስተማራቸው ጊዜ ያረጋገጠው ይህንን እውነት ነው። ፦ “እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ” ። ማቴዎስ 6:9
ጸሎት ወደ አብ መጸለይ እንዳልበት ያስተማርው ጌታችን ኢየሱስ ወደ አብ የምንጸልይውን ጸሎት ደግሞ በስሙ መጸለይ እንዳለብን አስተምሮናል። " እኔ ወደ አብ እሄዳለሁና አብም ስለ ወልድ እዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋልሁ”። ዮሐ 14:13-14 “ስለዚህም ወደ አብ በኢየሱስ ስም እንጸልያለን”።
አዲስ ኪዳን በስፋት ከሚያስተምራቸው መሰረታዊ ትምህርቶች መካከል መንፈስ ቅዱስ ከአማኝ ጋር ስላለው ግንኙነት የሚናገረው ቀዳሚው ትምህርት ነው። ከዚህ እውነት አንጻር የአማኝን የጸሎት ልምምድ ስንመለከት ጸሎት በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ/ኀይል እና ምሪት የሚደረግ መንፈሳዊ ልምምድ እንደሆነ እንገነዘባለን።
ይህን እውነት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል።" እንደዚሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል”። ሮሜ 8:26-28 ይሁዳ 20 “በመንፈ ቅዱስም እየጸለያችሁ....” ስለዚህ፣ ጸሎት ሦስቱንም የመለኮት አካላት ያካትታል ማለት ነው። ይህም ማለት ወደ አብ ፣በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንጸልያለን ማለት ነው።
ትክክለኛው የጸሎት መንገድ፦ ወደ አብ በአክብሮትና በምስጋና በመቅረብ በኢየሱስ ስም መጸልይ ነው፣ ምክንያቱም እርሱ አማላጃችን እና ተስፋችን ነውና።እንዲሁም በሚመራን እና ድካማችንን በሚያግዘው በመንፈስ ቅዱስ ኀይል መጸልይ ነው።በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ወደ አብ እንጸልያለን።
Source: https://cmaeec.com/w...
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.