Home » Sunday sermon – December 14, 2025

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር

Last updated on December 14, 2025 - by Pastor Tariku Eshetu

ትምህርት አስራ ሰባት፦ የእግዚአብሔር መንግስትና ጸሎት

በየቀኑ በእግዚአብሔር ላይ የመደገፍ ጽሎት

መግቢያ

ማቴዎስ 6:11-13
ጌታችን ኢየሱስ የመንግስቱን ጸሎት ባስተማረ ጊዜ ወደ ማን መጸልይ እንዳልብን፣ እንዴት መጸለይ/ምን መጸለይ እንዳልብን እና እንዴት መኖር እንዳለብን አስተምሮናል።በዚ እውነት መሰረት ጌታ ካስተማርው የመንግስቱ ጸሎት የመጨረሻውን ክፍልና በየቀኑ በእርሱ ላይ መደገፋችንን የሚያረጋግጡትን በዕለት ተዕለት አስፈልጎቶቻችንን ላይ አተኩረን እንድንጸልይ ያስተማርወን እውነት በዚህ ትምህርት እንመለከታል። እነርሱም ዕለታዊ አቅርቦት ይቅርታና - ጥበቃ የሚሉ ናቸው።

I. ዕለታዊ አቅርቦት

 “የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን” (ቁ.11) በመንግስቱ ውስጥ እግዚአብሔር ፈጣሪያችን ብቻ ሳይሆን አኗሪያችንና መጋቢያችን ነው ወይም የአስፈልጎታችን ሰጪና አቅራቢያችን ነው።

 "ዕለታዊ"ልመና ራስን መቻልን ሳይሆን ጥገኛነትን ያስተምራል።የእርሱ ጥገኛ ስለሆንን እየሰራንና ገንዝብ እያገኘን ይህን ጸሎት እንጸልያልን።ምክንያቱም የስራችንም ሆነ የገንዘባች ጥገኛ ሳንሆን በመንግስቱ የሚያኖርን የእግዚአብሔር ጥገኞች ስለሆንን ነው።

 “የዕለት እንጀራ” የሚለው ቃል የሚያመልክትው ለህይወታችን አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ ነው ። (ምግብ, ሥራ, ጤና, ጥንካሬ.......) ይህ እውነት (ዘጸ. 16) የእስራኤልን ሕዝብና በምድረ በዳ የበሉትን መና ያሳስበናል።እነርሱ ለዕለት ብቻ የሚበቃቸውን እንዲለቅሙ ወይም በየቀኑ በእግዚአብሔር እንዲያምኑ ነበር የተጠየቁት ከዚህ እውነት አነጻር የዚህ ጸሎት ቁልፍ እውነት እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን በአስፈላጊው ጊዜ በየዕለቱ ለዕለቱ ይሰጠናል የሚል ነው።ይህም እኛን የእርሱ ጠገኛ ያደርገናል።የመንግስቱ ጸሎት የእግዚአብሔር ጥገኝንታችንን የሚያረጋግጥ ነው።

 ስለዚህ ዛሬ ላይ ያለን አማኞች፡-በችግር ጊዜ ብቻ ሳይሆን በየቀኑ ይህን ጸሎት መጸልይ ያስፈልገናል።እንዲሁም ስለ ዛሬ ዛሬ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለብን ማለት ነው በተጨማሪም ለነገ መጨነቅን አስወግደን በእርሱ ላይ መታመን ግድ ይለናል (ማቴ. 6፡34) ምክንያቱም የመንግስቱ ጸሎት ከመንግስቱ መርህ ጋር ስልሆነ የሚስራው።

II. ዕለታዊ ይቅርታ

 "የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን" (ቁ.12) ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ዕዳን ይፈጥራል።ስለዚህ አማኞች አሁንም በየቀኑ ይህን ጸሎት በመጸለይ በይቀኑ መንጻት ያስፈልጋቸዋል (1ኛ ዮሐ 1፡9)። የእግዚአብሔር ይቅርታ በእኛ ውስጥ ይፈስሳል እንጂ በእኛ ብቻ የሚቆም አይደለም።ስለዚህ ይቅርታ አለማድረግ ከእግዚአብሔር እና ከሌሎች ጋር ያለውን ህብረት ይጎዳል።ከዚህ አንጻር የዚህ ጸሎት ዋናው እውነት ይቅር የተባሉ ሰዎች በየዕለቱ ሌሎችን ይቅር ማለት አለባቸው የሚል ነው።

 ይህ ጸሎት ዝም ብሎ የሚደገም ንግግር ሳይሆን ኃጢአትን በተግባርና በቅንነት በየዕለቱ መናዘዝን የሚጠይቅ ጸሎት ነው።በተጨማሪም በሰወች ላይ ያለንን ምሬትና ንዴት መልቀቅ/መተውን የሚጠይቅ የመንግስቱ ጸሎት ነው።እንዲሁም ከበቀል ይልቅ የእግዚአብሔርን ጸጋ የመምረጥ ውሳኔ ነው።

III. ዕለታዊ ጥበቃ

 "ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን" (ቁ.13) የመንግስቱ መንፈሳዊ ሕይወት መንፈሳዊ ጦርነት ማድረገን ያጠቃልላል።ምክንያቱም ከክፉ መንፈሳዊ ዓለም የሚሰነዘር የተደራጀ መንፈሳዊ ጥቃት ያለማቋረጥ በመንግስቱ አማኞች ላይ ስለሚካሄድ። ኤፌ 6:10-13።

 “ወደፈተና አታግባን” ይህን ቃል በትክክል መርዳት በጣም አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ማንንም በክፉ አይፈትንምና ነገር ግን በክፉ እንዳንፈተን ይመራናል ይጠብቀናል (ያዕ 1፡13)። ፈተናን ማስወገድ መቋቋምና ከክፉ መዳን መንፈሳዊ ጥንካሬንና መንፈሳዊ ጥበብን ይጠይቃል መንፈሳዊ ጥበብና ጥንካሬን ለማግኘት ደግሞ ጸሎት ይጠይቃል። ከዚህ አንጻር የዚህ ጸሎት ቁልፍ እውነት ድል የሚገኘው በሰው ኃይል ሳይሆን በእግዚአብሔር ኀይልና ጥበቃ ነው የሚል ነው።

 በዚህ ዘመን ያሉ የመንግስቱ አማኞች ከመንፈሳዊ ውጊያ ነጻ አይደሉም ስለዚህ በክፉ ፈተና እንድይጎዱ በየቀኑ ምሪትንና ጥበቃን ለማግኘት መጸልይ አልባችው።እንዲሁም ለፈትና የሚያጋልጧቸውን አጓጊ ካባቢዎች ማስወገድም አለባችው።ደግሞም መንፈሳዊ ውጊያን በብቃት ለመፈጸም በእግዚአብሔር ኃይል ላይ መመካት አለባቸው።ስለዚህ ይህ ጸሎት ከለማድ ጸሎት የተለየና በመርህ የሚደረግ የመንግስቱ ጸሎት በመሆኑ በየዕለቱ ልንጸልየው ይገባል።

ማጠቃለያ

የመንግስቱ የክርስትና ሕይወት የዕለት ተዕለት የእግዚአብሔር ጥገኝነት ነው።ስለዚህ እግዚአብሔር የየዕለት አቅርቦትን ለህዝቡ ይሰጣል፣እግዚአብሔር ዕለት ዕለት በልጁ ደም አማካይነት የህዝቡን ኀጢአት ይቅር ይላል።እንዲሁም እግዚአብሔር ህዝቡን ከክፉ ፈተና ይጠብቃል።ስለዚህ የመንግስቱ ጸሎት ከአባታችን ጋር እንድንገናኝና በየዕለቱ የእርሱ ጠገኛ እንድንሆን ያደርገናል።በዚህ አግባብ የመንግስቱን ጸሎት የሚጸልይ አማኝ የእግዚአብሔር ጥገኛ ነው፣ ጥገኛ አማኝ ደግሞ ጠንካራ አማኝ ነው።ጸሎትና የእግዚአብሔር መንግስት ያላቸውም ግንኝነት ይህ ነው።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.