በአስጨናቂው ዘመን በእውነት ላይ መቆም
መግቢያ
ጳውሎስ 2 ጢሞቴዎስን ከእስር ቤት ሆኖ በህይወቱ መጨረሻ ላይ የጻፈው መልእክት ነው። ሐዋርያው ስደት እየበዛ የሀሰት ትምህርት እየተስፋፋ መሆኑን ያውቃል። ስለዚህ ለጢሞቴዎስ እንዲህ ብሎ ያሳስበዋል ጸንታችሁ ቁሙ። እውነትን ያዙ። ከአለም ጋር አታመቻምቹ/አትቀላቀሉ።ይልዋል ይህ መልእክት ዛሬ በዚህ ዘመን ላለነው አማኞች አስቸኳይና አስፈላጊ መለእክት ነው።
I. አስጨናቂው ዘመን ከየት ይመጣል? (ቁ. 1-5)
ጳውሎስ እንዲህ ይላል፦ “በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እውቅ” ይህም ከፖለቲካ፣ከማህበርዊ ቀውስ፣ከኤኮነሚ ችግር ወይም ከጦርነት የተነሳ የሚመጣ ሳይሆን በቤተክርስቲያን ውስጥ ካለና ካልተለወጠ ልብ የሚመጣ ችግር ነው።ይህንንም ለማሳየት ጳውሎስ የሰዎችን ሁኔታ ይገልፃል፦
ሰወች እራሳቸውን እና ገንዘብን የሚወዱ ይሆናሉ
ሰወች ኩሩዎች፣ የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ ይሆናሉ
ሰወች ያለ ፍቅር ወይም ራስን ባለመግዛት የሚኖሩ ይሆናሉ
ሰወች ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ
ሰወች የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል/ይክዳሉ
እነዚህ ሰዎች አሁንም ሃይማኖተኛ ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን ልባቸው አልተለወጠም። እኛም ከእነዚህ ስወች ለመለየት እንድንችል እርሳችንን እንዲህ ብለን መጠየቅ አለብን፡- ከተድላና ከመደሰት ይልቅ እግዚአብሔርን እወዳለሁ? የእኔ እምነት ውጫዊ የሀይማኖት መልክ ብቻ ነው ወይስ እውነተኛ የልብ መስጠት? ምክንያቱም የጳውሎስ ማስጠንቀቂያ ግልጽ ነው ባዶ ሃይማኖተኛ አትምሰሉ የሚል ነው።
II.የአስጭናቂ ዘመን ሰወች ከየት መጡ? (ቁ. 6–9)
ከሕሰት ትምህርት ውስጥ ነው የመጡት።ለዚህ ነው ሐዋርያው ከስውር የሐሰት ትምህርት ተጠንቀቁ በማለት ያስጠነቀቀው። ጳውሎስ ስለነዚ ሰወች አደገኛነት ሲናገር ወደቤት ሾልከው ይገባሉ ይላል።ከዛም በመንፈሳዊ ህይወታቸው የደከሙትን/ኀጢአታቸው የተከመርባቸውን፣በልዩ ልዩ ምኞት የሚወሰዱትን ሁል ጊዜ እየተማሩ እውነትን ወደማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ይይዛሉ።ዘመኑን አስጨናቂ የሚያድርጉትም የነዚህ የሐሰት አስተማሪዎች ውጤት የሆኑ እውነትን መማርም ሆነ ማወቅ ከቶ የማይችሉ ሀይማኖተኞች ናቸው።
የአስጨናቂው ዘመን ትውልድ በቤተክርስቲያን እንዲከሰት የሚያደርጉን የሀሰት አስተማሪዎች አደገኛነት ለማሳየት ሐዋርያው ሙሴን ከተቃወሙት ኢያኔስና ኢያንበሬስ ጋር አመሳስሏቸዋል።በርግጥ የውሸት ትምህርት አስደናቂ ሊመስል ይችላል ነገር ግን በእግዚአብሔር እውነት ፊት መቆም አይችልም።
በስህተት ትምህርት ተጠልፈን ይህን ትውልድ እንዳንቀልቀል ክርስቲያን ነኝ የሚል ድምፅ ሁሉ ስለ ክርስቶስ እንደማይናገር ማወቅ አለብን። ሁሉንም ትምህርቶች በቅዱሳት መጻሕፍት መፈተሽ አለብን ።ምክንያቱም ታዋቂነት ፣ ስሜት ቅስቃሽነት ወይም የተለይ ስብዕና መላበስም የእውነት ምረጋጫ አይደለምና።
III.በአስጨናቂው ዘመን በእውነት ለመቆም ምን እናድርግ? (ቁ. 10–13)
የታማኝ አማኞችን ምሳሌ መከተል ብቸኛው አማራጭ ነው። ለዚህ ነው ጳውሎስ ጢሞቴዎስን“ትምህርቴን፣አኗኗሬን፣አሳቤንም፣ እምነቴንም፣ ትዕግሥቴንም፣ ፍቅሬንም፣ ጽናቴንም፣ስድቴንም፣መከራዬንም ተከትለህ…” በማለት ጢሞቴዎስ የጳውሎስን ስቃይ አይቶ አሁንም ታማኝ እንዲሆን ያሳስበው። ከዚያም ጳውሎስ እንዲህ ይላል።"በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ስለስሙ ይሰደዳሉ።
በርግጥ በእውነት መቆምና ታማኝነት ዝናን፣ ምቾትን ወይም እድሎችንና መልካም አጋጣሚዎችን ሊያስከፍለን ወይም ሊያሳጣን ይችላል።ነገር ግን የእግዚአብሔርን ይሁንታ ወይም ተቀባይነት ግን ያመጣልናል። ምሳሌ ታማኝነት በዓለም ላይ ያለንን እድገት ሊቀንስ ይችላል ነፍሳችንን ግን በእግዚአብሔር ፊት ያጸናል ይህንን እንዴት ነው የምንኖረው?ያልን እንደሆነ በእውነት ላይ መቆም ሁሉንም ነገር በቅዱሳት መጻሕፍት በመለካት የሚል ነው መልሱ።
ልባችንን በመጠበቅና ታዛዥነት የጎደለውን “ሃይማኖታዊ ሕይወት” እምቢ በማለት።ይህን ስናደርግ አንዳንድ ተቃውሞዎችን እንጠብቅ ምክንያቱም ታማኝነት ውድ ነው ነገር ግን ዋጋ ያለው የሕይወት እሴት ነው። በእግዚአብሔር ቃል ዙሪያ ልምምዶቻችን እንገንባ። የግል ንባብ፣ የቤተሰብ አምልኮ እና መጽሐፍ ቅዱስን ያማከለ የቤተክርስቲያን ሕይወት ይኑረን።
IV. በእውነት ለመቆም መልሕቃችን የእግዚአብሔር ቃል ነው (ቁ. 14-17)
ጳውሎስ ይህን እውነት አጥብቆ ያሳስባል፡-"በተማርከውና በተረዳህበት ነገር ጸንተ ኑር" ለምን? ቃሉ ወደ መዳን ይመራልና፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር እስትንፋስ ናቸውና፣ቃሉ ያስተምራል፣ ይገሥጻል፣ ያስተካክላል፣ ያሰለጥናል። ለበጎ ስራ ሁሉ ያስታጥቃል።
ስልዚህ 2026 ጠንካራ አማኞችን፣ ጠንካራ ቤተሰቦችን፣ ጠንካራ አብያተ ክርስቲያናትን ማየት ከፈለግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሥር መስደድ አለብን።ለዚህ ደግሞ በትህትና ቃሉን አናንብብ ፣ቃሉን እንታዘዝ በቃሉ ዙሪያ አገልግሎት እና ህይወታችንን እንገንባ።
ማጠቃለያ
የምንኖረው በአስቸጋሪ ዘመን ውስጥ ነው ነገር ግን ያለ ተስፋ አይደለንም። እግዚአብሔር ግልጽ ማስጠንቀቂያዎችን የመምሰል ምሳሌዎችንና የቃሉም ጽኑ መሠረት ስጥቶናል። ስለዚህ 2026 እንዲህ እንበል፡- በእውነት ላይ እንቆማለሁ። ከአለም ይልቅ እግዚአብሔርን እወዳለሁ። ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍል በቃሉ እምናለሁ።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.