መግቢያ
ልንጠይቃቸው ከምንችላቸው በጣም አስፈላጊ ጥያቄዎች አንዱ ህይወቴን ለመንግስቱ መስጠት ምን ዋጋ አለው? የሚለው ነው፣ ምክንያቱም ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ዘመናቸውን ለተለያዩ ጉዳዮች ማለትም ለስራ፣ ለቤተሰብ፣ እና ለስኬት..... ወዘተ ይሰጣሉ ። ጌታችን ኢየሱስ ከሁሉም የሚበልጠውና ሁሉም ነገራችን የሚገባው አንድ እውነታ እንዳለ ይነግረናል እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት። ከዚህ አንጻር በማቴዎስ 13፡44-52፣ ኢየሱስ ያስተማርውን የእግዚአብሔርን መንግሥት እውነት ምንነት የሚያሳዩ ምሳሌዎችን እንመለክታልን።
I. የተደበቀው መዝግብ ትርጉም፦ "መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተደበቀ መዝገብ ትመስላለች። ማቴ 13:44 ምን ማለት ነው?
የተደበቀው መዝገብ የእግዚአብሔር መንግሥት ነው። ይህ መዝገብ በእግዚአብሔር አገዛዝ ሥር ያለውን ሕይወት ማለትም፦ መዳንን፣ የኃጢአት ይቅርታን፣ በክርስቶስ የሚገኘውን አዲስ ሕይወት እና የዘላለም ተስፋን ይወክላል። ልብ በሉ ኢየሱስ እየተናገረ ያለው ስለ ሃይማኖት፣ ስለ ሥነ ምግባር ወይም የቤተክርስቲያንን ፕሮግራም ስለመካፈል አይደለም። የእግዚአብሔር መንግስት በህይወታችሁ ውስጥ እየገዛ ስለመሆኑ እየተናገረ ነው።
መዝገቡ ተደብቋል ስለዚህ ሁሉም ሰው የመንግሥቱን ዋጋ በቀላሉ ማየት አይችልም። አንዳንዶች በየቀኑ በውስጡ ይመላለሳሉ ግን በጭራሽ አያስተውሉትም። አንዳንዶች ወንጌልን ይሰማሉ ነገር ግን ግድየለሾች ሆነው ይቀራሉ ኢየሱስ ቀደም ሲል እንደተናገረው፡-"እያዩ ስለማያዩ እየሰሙ ስለማይሰሙ" ማቴ 13:13
በደስታ እጅ መስጠት/ መገዛት ምላሹ ነው። ሰውየው ሁሉንም ነገር “በደስታ” ይሸጣል። ይህ የግዳጅ መስዋዕትነት አይደለም።ይህ አስደሳች ልውውጥ ነው። ጳውሎስ በፊል 3፡8 ላይ ይህንን እንዲህ ሲል አስተጋባ።" ከሁሉ ይልቅስ ለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታዬ እውቀት ነገር ሁሉ ጉድት እንዲሆን እቆጥራለሁ”።
II. የታላቅ ዋጋ ዕንቁ ትርጉም ማቴ 45–46
እንቁ ነጋዴው እንቁ እየፈለገ ነው።
ይህ ሰው ከመጀመሪያው ሰው በተለየ ሁኔታ ሆን ብሎ የእንቁ ፍልጋ እያደርገ ያለ ሰው ነው።ይህ የእንቁ ነጋዴ የሚከተሉትን ሰዎች ይወክላል ጥልቅ ጥያቄዎችን የሚጠይቁ፣እውነትን የሚፈልጉ፣ለሕይወት ትርጉም ማግኘት የሚናፍቁ እና እግዚአብሔርን በቅንነት የሚፈልጉ ሰወችን ይወክላል። እግዚአብሔር በቅንነት የሚፈልጉትን ያከብራል።”እናንተ ትሹኛላችሁ በፍጹም ልባችሁም ካሻችሁኝ ታገኙኛላችሁም ።”ኤር 29:13
ዕንቁው የተለይ መሆኑ ታውቋል
ነጋዴው ዕንቁውን ሲያየው ወዲያውኑ አይነቱንና ዋጋውን ያውቃል።ምክንያቱም እውነት ሁሉ እኩል አይደለም።እንዲሁም ሁሉም ሃይማኖቶች አንድ አይደሉም።ነገር ግን ክርስቶስ ብቻውን ተለይቶ ቆሟል መሳይ የለውም።በእውነት የሚፈልጉት ሁሉ ያገኙታል።
ዋጋው አንድ ነው
እንቁውን ስለመግዛት ያለውን ሁሉ ይሸጣል።ይህ ማለት ዕንቁው ፍጹም፣ ዋጋ ያለው ሆኖ ስላገኘው፣ በባለቤትነት የያዛቸውን ዕንቁዎች ሁሉ ዋጋ ቢስ ያአደረጋቸዋል ማለት ነው። ያለምንም ማመንታት ያን አንድ ዕንቁ ለመግዛት ሁሉንም ስብስቦ ይሸጣል። ይህን በማድርጉ ለአንድ ሰከንድ አይጸጸትም። ምክንያቱም እውነተኛውን የዕንቁ ዋጋ ይገነዘባልና ከሌሎቹ ሁሉ አንዱን ዕንቁ ይመርጣል።ኢየሱስ እንዲህ አለ “መንግሥተ ሰማያት እንዲሁ ናት!!!!
III. መንግሥቱ አሁን ለሁሉም ክፍት ነው በመጨረሻ በፍርድ መለያየት ያበቃል። ማቴ 13:47-50
"መንግሥተ ሰማያት ወደ ባሕር የተጣለ መረብን ትመስላለች"
መረቡ ሁሉንም ዓይነት ዓሦች ይሰበስባል። ይህ የሚያመለክተው ሰፊውንና ሁሉን አቀፍ የወንጌል ጥሪን ነው።ነገር ግን በፍርድ መለያየት በመጨረሻ ላይ ይከሰታል። ኢየሱስ ስለ ፍርድ በግልጽ ተናግሯል መላእክት ጻድቃንን ከኃጥኣን ይለያሉ። ፍርዱ እውነተኛ እና የመጨረሻ ነው።
ቁልፉ እውነት የመንግሥቱ ዜጋ መሆን ነው።የመንግስቱ ዜጎች አጠገብ/አጥቢያ ውስጥ መሆን የክርስቶስ መሆን ማለት አይደለም። ለምሳሌ ብዙዎች በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ይገኛሉ ፣ ግን ኮርሱን ያጠናቀቁ ብቻ ዲፕሎማውን ያገኛሉ።ከተመራቂዎቹ መካከል መሆንን ማረጋገጥ ይጠይቃል። በቤተ ክርስቲያን መገኘት፣ በጥሩ ሥነ ምግባር መኖር፣ ወይም ሃይማኖታዊ ቋንቋን ማወቅ አያድንም። ማቴ 7፡21" ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። ይህ እውነት መጠቀሱ ለማንቃት እንጂ ተስፋ ለማስቆረጥ አይደለም።
IV. የመንግሥቱ ደቀ መዛሙርት ሀላፊነት ማቴ 13:51-52
"ይህን ሁሉ አስተዎላችሁ?" እነሱም “አዎ” ብለው መለሱ።
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ምሳሌዎቹን በትክክል እንደተረዱት ጠይቃቸው ምክንያቱም የመንግስቱን እውነት ከመረዳት ጋር ሃላፊነት አብሮ ይመጣልና። እውነተኛ ደቀ መዝሙር የእግዚአብሔርን መንግስት የማስተማር ሐላፊነት አለበት።
ደቀ መዝሙር ሲያስተምርም፡-ብሉይ ኪዳንን ከመንግስቱ አንጻር ይረዳል ያስርዳል“አሮጌው” የኢየሱስን ትምህርት እና ወንጌልን ከመንግስቱ አንጽር ይረዳል ያስረዳል“አዲሱ” እውነተኛ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር እና አስተማሪ ብሉይ ኪዳንንም ሆነ አዲስ ኪዳንን በታማኝነት ያስተምራል፣ ይህም የብሉይ ኪዳን የመንግስቱ እውነቶች በክርስቶስ እንዴት እንደተፈጸሙ እና እንደተጠናቀቁ ያሳያል።
ማጠቃለያ
ጌታ ኢየሱስ የመንግሥቱን እውነት አሳይቶናል።ከመንግስቱ አንጻር ሁሉም ነገር ዋጋ አለው። ስለዚህ የግል ምርጫ ማድረግ ያስፈልገዋል።ከመንግስቱ ጋር የሚኖረን ግንኙነት ለፍርድ ያበቃል። የመንግስቱን እውነት መረዳት ታማኝና ኀላፊነት ያለበት ደቀ መዛሙር ያደርጋል። ስለዚህ ጥያቄው መንግሥቱ ጠቃሚ ነው ወይስ አይደለም የሚልው ሳይሆን መዝገቡን አግኝተነዋል?ዕንቁውን መርጠናል? ለመጨረሻ ፍርድስ ዝግጁ ነን? እንደ ደቀመዝሙር እየኖርን ነው? የሚል ይሆናል።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.