የእግዚአብሔር መንግሥት በዘፀአት
መግቢያ
በዘፀአት ውስጥ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ሃሳብ በዘመናዊ ቋንቋ በስም አልተሰየመም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር እስራኤልን እንዴት እንደሚያድንና ፣ እስራኤልን የእርሱ መንግስት አድርጎ እንደሚመሰርታት እንዲሁም በመካከሏ በማደር እንደሚገዛ፣ በግልፅ ተብራርቶአል። የዘጸአት ትልቁ ምስል ምን እንድሆነ በዚህ ትምህርት እንመልክታልን።
1. በዘጸአት እግዚአብሔር ራሱን እንደ ንጉሥ ይገልጣል
ዘጸ 5–12 - እግዚአብሔር በግብፅ አማልክት ላይ ኃይሉን በማሳየትና መቅሰፍቶችን በማድርግ ፈርዖንን ገጠመው። በግብጽ ምድር የተክሰቱ እንዚህ መቅሰፍቶችና የቀይ ባሕር መከፈል ተአምራት ብቻ አይደሉም። እግዚአብሔር አምላክ ንጉሥ ነኝ ከሚለው ፈርዖን እንደሚበልጥ የሚያሳዩ ንጉሣዊ የፍርድ ድርጊቶች ናቸው እንጂ። እነዚህ ሁነቶች እውነተኛው የዓለም ገዥ ፈርዖን ሳይሆን ያህዌ መሆኑን የሚያርጋግጡ ናቸው ።
ለዚህ ነው ዘጸ 15፡1-18 (የሙሴ መዝሙር) እግዚአብሔር ለዘላለም የሚነግሥ ተዋጊ ንጉሥ ሆኖ የተመሰገነው። ”እግዚአብሔር ለዘላለም ይነግሣል” (15፡18)። ፈርዖን ንግሥ ነኝ ቢልም እግዚአብሔር ግን እውነተኛ ገዥ ወይም ንጉስ መሆኑን መሆኑን አረጋግጧል።
2. በዘጸአት እግዚአብሔር ሕዝቡን ሊያድናቸውና የእርሱ ሊያድርጋችው ወርዶአል።
ዘጸ 6፡6–7 እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚቤዣቸው እና እንደ ህዝቡ እንደሚወስዳቸው ቃል ገብቷል። በዘጸ 12-14 የተደረገው ፋሲካ እና የቀይ ባህር መከፈል በእግዚአብሔር ኃይል ብቻ መዳንን እንደሆነ ያሳያሉ። የመንግሥቱ ሐሳብ እግዚአብሔር ሰዎችን ከባርነት ነፃ አውጥቶ ወደ አገዛዙ ያስገባልና።
3. በዘጸአት እስራኤል የእግዚአብሔር መንግሥት መሆንዋ ታወጀ ።
ዘጸ 19፡4-6 እግዚአብሔር እስራኤል የእርሱ ውድ ርስት ፣ቅዱስ ሕዝብና የካህናት መንግሥት እንደምትሆን አበሰር። ይህ በዘፀአት መጸሕፍ ውስጥ ውስጥ በጣም ግልፅ የሆነው የእግዚአብሔር መንግስት መግለጫ ወይም አዋጅ ነው።
4. በዘጸአት እግዚአብሔር የመንግሥቱን ሕግ ለህዝቡ ሰጠ
ዘጸ 20 - አስርቱ ትእዛዛት ወይም የሞራል ህግ ዘጸ 21–23 ደግሞ ህዝቡ ከሌሎች ህዝቦች ጋር እና እርስ በርሳችው የሚኖራቸውን የህይወት መስተጋብር፣ደግሞም የመቅደስ አምልኮ ስርዓትን የሚወስኑ ስለ ፍትህ፣ ስለምሕረት እና ስለአምልኮ የሚናገሩ ህጎችን ሰጠ። እነዚህ ህጎች ሰዎች እግዚአብሔር ንጉሣቸው ሲሆን እንዴት እንደሚኖሩ የሚገልጹ እንጂ መዳንን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል የሚያሳዩ አይደሉም።ነገር ግን እግዚአብሔር ንጉስህ ሲሆን ህይወት ምን እንደሚመስል ያሳያሉ።
5. በዘጸአት ንጉሡ እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል ይኖራል
ዘጸ 25:8 እግዚአብሔር በመካከላቸው ያድር ዘንድ መቅደስን እንዲሰሩለት ህዝቡን ያዝዛል። ዘጸ 40፡34-38 የእግዚአብሔር ክብር የማደሪያውን ድንኳን ሞላው። የጥንት ዘመን ነገሥታት ከቤተ መንግሥታቸው ሆነው መንግስታቸውን ወይም ህዝባቸውን ይገዙ ነበር። እግዚአብሔርም እንዲሁ ከሕዝቡ ጋር መኖርን ይመርጣል ወይም ይፈልጋል።
በአዲስ ኪዳን ኢየሱስ ስለ “እግዚአብሔር መንግሥት” ሲናገር በዘፀአት መሪ ሃሳቦች ላይ በመመስረት ነበር። ይህም በክርስቶስ ኢየሱስ ከባርነት ነፃ መውጣት፣ በቃል ኪዳን ግንኙነት ለእግዚአብሔር መገዛትና የእግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል ማደር ነው።የሚለው ነው።
ማጠቃለያ
በዘጸአት ውስጥ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንዲህ ተገልጦአል፡- በኃይላት ሁሉ ላይ የሚገዛ እግዚአብሔር (ዘጸ 15) እግዚአብሔር ሕዝብን ለራሱ ያድናል (ዘጸ 6፣ 12–14) እግዚአብሔር እስራኤልን የእርሱ መንግሥት መሆናቸውን አውጆአል (ዘጸ 19) እግዚአብሔር በሕጉ አምካኝነት ህዝቡን ይገዛል (ዘጸ 20) እግዚአብሔር በሕዝቡ መካከል የሚኖር ንጉስ ነው። (ዘጸ 40)በአጭሩ የዘፀአት መጸሐፍ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚያስተዋውቀን እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያድን፣ ህዝብን በሕጉ የሚገዛና በህዝቡ መካከል እንደ ንጉሣቸው ሆኖ የሚኖር አምላክ መሆኑን ነው።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.