Home » Sunday sermon – May 31, 2026

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር

Last updated on May 31, 2026 - by Pastor Tariku Eshetu

የእግዚአብሔርን መንግሥት በመጸሀፈ ነህምያ

የእግዚአብሔርን መንግሥት ተሃድሶ፣ በድፍረትና በታዛዥነት መገንባት

ምንባብ፦ ነህምያ 1:1–11፤ 2:17–20፤ 4:14, 17–18፤ 6:15–16፤ 8:1–12፤ 9:1–3, 33

መግቢያ

የነህምያ መጽሐፍ ከቅጥር ግንባታ ፕሮጀክት ያለፈ ትርጉም አለው። እርሱም የእግዚአብሔር መንግሥት ታሪክ ነው። የኢየሩሳሌም ቅጥሮች ፈርሰው፣ ሕዝቡ ተስፋ ቆርጦ፣ ከተማዪቱም በውርደት ውስጥ ነበረች፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከኪዳኑ ሕዝብ ጋር ያለው ታሪክ ግን አላበቃም ነበር።በዚህ ምክንያት የፈረሰውን እንዲገነባ፣ የተተወውን እንዲያድስ፣ እና የጠፋውን መልሶ እንዲያቋቁም ነህምያን አስነሳው። በዚህ ትምህርት ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ስንናገር፣ ስለ እግዚአብሔር ገዥነት፣ ስለ ሥልጣኑ እና በሕዝቡ መካከል ስላለው ሥራ እየተናገርን ነው። በነህምያ መጽሐፍ ውስጥ፣ መንግሥቱ የሚታየው የነገሥታት ዙፋን ባለበት አዳራሽ ውስጥ ሳይሆን በጸሎት ክፍል፣ በከተማ ቅጥሮች፣ በቃሉ ሕዝባዊ ንባብ፣ በንስሐ እና በታማኝ አገልግሎት ውስጥ ነው።የነህምያ መጸሀፍ መልእክቱ ግልጽ ነው እግዚአብሔር በሚገዛበት ቦታ ሁሉ፣ መታደስና መመለስ ይከተላል የሚል ነው።

1. የመንግሥቱ ተሀድሶ የሚጀምረው ከእግዚአብሔር በሚሰጥ ሸክም ነው (ነህ 1:5–11)

የነህምያ መጸሀፍ ታሪክ የሚጀምረው ኢየሩሳሌም በችግር ውስጥ መሆኗንና ቅጥሮቿም መፍረሳቸውን በሰማ ጊዜ ነህምያ የሰጠውን ምላሽ በመዘገብ ነው።የነህምያ የመጀመሪያ ምላሽ ማጉረምረም፣ መሸሽ ወይም ሌሎችን መውቀስ አልነበረም።ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጠ፣ አለቀሰ፣ ጾመ፣ ጸለየም።ምክንያቱ የመንግሥቱ ሥራ የሚጀምረው እግዚአብሔር በልባችን ላይ በዚህ ሂደት ውስጥ በሚያስቀምጠው ሸክም ነው ።በምዕራፍ 1 ላይ ያለው የነህምያ ጸሎት በአክብሮት፣ በኑዛዜ እና በኪዳን እምነት የተሞላ ነው። የእግዚአብሔርን ታላቅነት ያውጃል፣ የተስፋ ቃሉንም ያስባል። ሕዝቡ ንጹሕ እንደሆኑ አያስመስልም፤ የራሱንና የአባቱን ቤት ኃጢአት ጨምሮ የእስራኤልን ኃጢአት ይናዘዛል። ይህ ለመንግስቱ ተህድሶ በጣም አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በኩራት ላይ አይገነባም። የሚገነባው በእግዚአብሔር ፊት በሚሆን ትሕትና ላይ ብቻ ነው። ከእግዚአብሔር ዘንድ ሸክም ያለው ሰው ስብራትን የሚያየው በተለየ መንገድ ነው። ሌሎች ፍርስራሹንና ተስፋ መቁረጥን ብቻ ሲያዩ፣ የመንግሥቱ ሰዎች ግን ፍርስራሹን አይተው፣ “እግዚአብሔር እንድንገነባው እየጠራን ያለው ምንድን ነው?” ብለው ይጠይቃሉ።

ተግባራዊ ተዛምዶ፦

እግዚአብሔር በልባችን ላይ ሸክም ካኖረ፣ ቸል አንበል።ምናልባት እግዚአብሔር የመንግሥቱን ሥራ በሕይወታችን ውስጥና በሕይወታችን በኩል መስራርት የሚጀምርበት ሊሆን ይችላል።

2. የመንግሥቱ ተሀድሶ በእምነት ላይ የተመሠረተ ራዕይ ያስፈልገዋል (ነህምያ 2:17-20)

ነህምያ ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ፣ የቅጥሩንና የከተማውን የመውደም እውነታ ከህዝቡ አልደበቀም። ቅጥሮቹን በጥንቃቄ ተመለከተ፣ ከዚያም ለሕዝቡ የማበርታቻ ቃል እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦ “ኑ፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ። ”ነገር ገን ሥራው በቀላል የሚከናወን እንደሚሆን ቃል አልገባላቸውም። ነገር ግን በእርሱ ላይ ወዳለችው የእግዚአብሔር እጅ አመለከታችው ወይም “ስለ መልካሚቱ የአምላኩ እጅ” ነገራቸው።ነህምያ ያደርገው የእግዚአብሔር መንግሥት ራዕይ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ እውነት ነው።ነህምያ ያደርገው ችግሩን መካድ አይደለም፣ነገር ግን በሰው ኃይል ላይ አለመታመንን ማረጋገጥ እና በሰማይ አምላክ ላይ መታመንን ማጽናት ነው። ነህምያ እግዚአብሔር ሰለጠራቸው፣ እግዚአብሔር ደግሞ እንደሚደግፋቸው አመነ።በዚህ ጊዜ ጠላት በፍጥነት በፌዝና በዛቻ መጣ። ሰንባላጥና ጦብያ ግንበኞቹን በማሸማቀቅ ስራውን ለማስቆም እየሞከሩ ሥራውን አናናቁ። ነህምያ ግን በመፍራት ሳይሆን በእምነት መለሰላቸው። የእግዚአብሔር መንግሥት በስድብ ወይም በማስፈራራት ሊፈርስ እንደማይችል ያውቅ ነበርና።

ተግባራዊ ተዛምዶ፦

አማኞች ሁኔታዎችን በሰው ደካማነት መለካት አቁመው በእግዚአብሔር ታማኝነት መለካት ሲጀምሩ የመንግሥቱ ተሀድሶ ወደ ፊት ይገሰግሳል።

3. የመንግሥቱ ተሀድሶ በግልሰብ ሳይሆን በብዙ እጆች ይገነባል (ነህምያ 3:28)

የነህምያ መጽሐፍ ምዕራፍ 3 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ካሉት እጅግ ውብ የእግዚአብሔር መንግሥት ትብብር ከሚያያሳዩ ሥዕሎች አንዱ ነው። ካህናት፣ ገዢዎች፣ ቤተሰቦች፣ አንጥረኞች፣ ነጋዴዎችና ተራ ሠራተኞች ሁሉ ለቅጥሩ መታደስ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። አንዳንዶቹ በሮቹን ጠገኑ፣ አንዳንዶቹ ቅጥሩን አደሱ፣ አንዳንዶቹ በገዛ ቤታቸው አጠገብ ያለውን የቅጥሩን ስራ ሠሩ፣ ሌሎቹ ደግሞ ለረጅም ክፍሎች ኃላፊነት ወሰደው ሰሩ።ይህ ምዕራፍ የሚያስተምረን የእግዚአብሔር መንግሥት በአንድ ታዋቂ መሪ ብቻ እንደማይገነባ ነው።ነገር ግን የሚገነባው እያንዳንዳቸው ድርሻቸውን በሚወጡና አንድነታቸው በተጠበቀ ሕዝቦች ነው።በህብረት ውስጥ እያንዳንዱ ሰው ዋጋ አለው። እያንዳንዱ የአገልግሎት ክፍል ዋጋ አለው። እያንዳንዱ የታማኝነት ተግባር ትርጉም አለው። ሕዝቡ ሁሉ አንድ ዓይነት ሥራ አልሠሩም፣ ነገር ግን ሁሉም ያገለግሉት የነበረው አንዱን ጌታ ነበር። ይህ ለቤተክርስቲያን ታላቅ ምሳሌ ነው። የእግዚአብሔር ሕዝብ እርስ በርሱ መወዳደር አቁሞ በታዛዥነት መተባበር ሲጀምር የመንግሥቱ ተሀድሶ እንደሚያድግ ያሳያል።

ተግባራዊ መግለጫ፦

በግላችን ሙሉውን ቅጥር ላንጠግን እንችላለን፣ ነገር ግን በእኛ እጣ ክፍል ላይ ታማኝ ሆነን ከቀጠልን፣ የመንግሥቱን መታደስ እየረዳን ነው።

ማጠቃለያ

የነህምያ መጸህፍ የመጀመሪያው ክፍል የሚያሳየን እውነት የእግዚአብሔር መንግስት መታደስ የሚጀምረው በስው ፍላጎት ሳይሆን እግዚአብሔር ሸክምን በሰጣቸው ስወች መሆኑን እንዲሁም የመንግስቱ ተሀድሶ ስራ በእምነት ላይ የተመሰረተ ራዕይ እንደሚያስፈልገውና ይህ ራዕይ ድግሞ በአንድ ሰው ጥረት የሚፈጸም ሳይሆን የመንግስቱን ህዝቦች ሁሉ የሚያሳትፍ መሆኑን ነው።ስለዚህ እያንዳንዱ የመንግስቱ ዜጋ በመንግስቱ ተሀድሶ ውስጥ ጠቃሚና ተፍላጊ ሰው መሆኑን በመቀበል የሚሰራውን ድርሻ መውሰድና ከሌሎችጋር በመተባበር መንግስቱን ለማደስ መነሳታ አለበት።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.