Home » የዘፍጥረት መጽሐፍ (Tuesday Sermons) » Tuesday – April 21, 2026

የዘፍጥረት መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ

Last updated on April 21, 2026 - by Pastor Tariku Eshetu

7ኛው ሳምንት፡ የአብርሃም ጥሪ እና የተስፋው ቃል

የታሪክ እጥፋት፦
ዘፍጥረት 12 በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የለውጥ ምዕራፍ ነው። ከኃጢያት መስፋፋት፣ ከጥፋት ውሃ እና ከባቤል ግንብ አመጽ በኋላ፣ እግዚአብሔር የማዳን መንገድ መስመሩን መዘርጋት የጀመረበት ነው። ስለሆነም እግዚአብሔር አሕዛብን ሁሉ ይባርክ ዘንድ አንድ ሰው መረጠ።ለዚህ ነው አዲስ ኪዳን ወንጌልን ለማስረዳት በተደጋጋሚ ወደዚህ ክፍል የሚመልሰን። በዚህ ሽግግር እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባው ቃል ኪዳን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን ሒደቶች ሁሉ አንድ ቅርጽ እንዲሰጥ አድርጎአል።
ዘፍጥረት 12፡1-9
ሥነ-መለኮታዊ ጭብጦች፡ ምርጫና፣ ቃል ኪዳን ዋናው ሐሳብ፡ በእግዚአብሔር ሉዓላዊ ምርጫ አንድን ሰው እግዚአብሔር መረጠ እርሱም አብርሃም ይባላል፣ በእርሱም አሕዛብን ሁሉ ለመባረክ የማዳን እቅዱን እግዚአብሔር ይጀምራል።

ዘፍጥረት 12:1— ጥሪ (ምርጫ)

እግዚአብሔር አብራም አገሩን፣ ቤተሰቡን እና የአባቱን ቤት ለቆ እርሱ ወደሚያሳየው ምድር እንዲሄድ ነግሮታል። ይህም ንጹህ መለኮታዊ ተነሳሽነት ነው።ምክንያቱም አብራም እግዚአብሔርን አልፈለገም ነገር ግን እግዚአብሔር አብራምን መረጠው እንጂ። በዚህ ምርጫ ውስጥ ለአብራም የተሰጠው ትዕዛዝ መፈጸም ጠንካር እምነትን መኖርን ያካትታል ምክንያቱም አብራም እንዲሄድ ተጠየቀው፡- የእርሱ ሀገሩን(ደህንነት) ፣ቤተሰቡን (ማንነት) ፣ትቶ መውጣትን የሚጠይቅ ስለነበር። ስለእርሱ የወደፊት ሁኔታ (እርግጠኝነት) አልነበርውም ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለ መድረሻው በዝርዝር አልነገረውም ቃል ኪዳን ብቻ ገባለት እንጂ።

ሥነ-መለኮታዊ አጽንዖት (ምርጫ)

የእግዚአብሔር ምርጫ ፀጋ ነው እንጂ በሰው ጥረት ወይም መልካም ስራ የተገኘ አይደለም። ምርጫ ከመታዘዝ ይቀድማል አብራም ታዘዘ ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለመረጠው። ይህ እውነት በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚታየውን አብነት ያስቀምጣል ማለትም እግዚአብሔር አስቀድሞ ይጠራል ከዚያም በጊዜ ሂደት እቅዱን ይገልጣል የሚለውን።

ዘፍ12:1 ከአዲስ ኪዳን ጋር ያለው ግንኙነት

ሮሜ 4፡ የአብርሃምን መጠራትና በኋላም የጸደቀው በስራ ሳይሆን በእምነት መሆኑን በማርጋገጥ የክፍሉን አዲስ ኪዳናዊ ትርጉም ወይም ብርሀን ይሰጠናል።ይህም የሚያርጋግጠው መዳን የሚጀምረው በሰው ጥረት ሳይሆን በእግዚአብሔር ተነሳሽነት ነው የሚለውን እውነት ነው።። የእግዚአብሔር ጥሪ ሁልጊዜ ከመታዘዛችን ይቀድማልና።

ዘፍጥረት 12:2—እግዚአብሔር ለአብራም የተገባው ተስፋ

እግዚአብሔር አብራምን ታላቅ ሕዝብ እንደሚያደርገው፣ እንደሚባርከው፣ ስሙንም ታላቅ እንደሚያደርግ ቃል ገብቷል። ቁልፍ ዝርዝሮችና ሶስት ዋና ተስፋዎች፡- አብራም ልጅ ባይኖረውም ታላቅ ሕዝብ እንድሚሆን ተነገርው → የግል በረከት → የእግዚአብሔር ሞገስ፣ ጥበቃ እና አቅርቦት ከእርሱ ጋር እንደሚሆን ተነገርው። ታላቅ ስም እንደሚኖርው ተነገርው ይህም→ ከባቤል (ዘፍጥረት 11) ጋር ይቃረናል፣ እሱም ሰዎች ለራሳቸው ስም ለማስጠራት ሲሞክሩ ነበር።

ሥነ-መለኮታዊ አጽንዖት (ተስፋ)

የእግዚአብሔር ተስፋዎች የሰውን የማይቻል ነገር ያሸንፋሉ። በረከት ለአብራም ጥቅም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ዓላማም አለው። እግዚአብሔር የሰውን ትዕቢት በመለኮታዊ ጸጋ ይቀየራል።

ከአዲስ ኪዳን ጋር ያለው ግንኙነት

የእግዚአብሔር ዓላማ አሕዛብን ሁሉ መቤዠት ነው። ገላ 3፡8፡ ይህ የቅዱሳት መጸሕፍት የንባብ ክፍል ለአብርሃም ወንጌል አስቀድሞ በእግዚአብሔር እንደተሰበከልት ይነግርናል። ወንጌል በዘፍጥረት በዘር መልክ ተነግሯል።ለዚህ ነው የብሉይ ኪዳን ተስፋ የአዲስ ኪዳን ወንጌል የሆነው።

አብርሃም በተስፋ አመነ።ሮሜ 4፡18-21፡ ምንም እንኳን በውቅቱ በነበሩት ሁኔታዎችና እግዚአብሔር ለአብርሀም በተናገርው ቃል መካከልትቃርኖ ቢኖርም አብርህም በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ሳይጠራጥር እንዳመነ ይህ ክፍል ያርጋግጥልናል።ከዚህ እንደምንመለከተው እምነት በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ መተማመን እንጂ በሚታዩ ማስረጃዎች ላይ መተማመን ማለት አይደለም።

ዘፍጥረት 12:3 — የተስፋው ቃል ዓለም አቀፍ ወሰን

እግዚአብሔር አብራምን የሚባርኩትን እንደሚባርክ፣ አብራምን ሚቃወሙት ወይም የሚርግሙት ደግሞ እንደሚርግም፣እዲሁም በእርሱ አሕዛብን ሁሉ እንደሚባርክ ቃል ገብቷል። ቁልፍ ዝርዝሮች አብራም ተወካይ ሆነ -አብራም እንድ እርሱ ለእግዚአብሔር በእምነት ምላሽ ለሚስጡ ሰዎች ውኪልን ምልክት ሆነ።በዚህ ተስፋ ውስጥ የመጨረሻው ሐረግ ወሳኝ ነው: "የምድር ሕዝቦች ሁሉ" የሚልው።ምክንያቱም ይህ የእግዚአብሔር ተልእኮ ለአሕዛብ የመጀመሪያው ግልጽ መግለጫ ነውና።

ሥነ-መለኮታዊ አጽንዖት (ቤዛነት)

የእግዚአብሔር እቅድ በአንድ ህዝብ ብቻ የተገደበ አይደለም። ይህ ቁጥር ስለ ወደፊት የሚያመለክተው፡-በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የእስራኤል ሚና ምን እንደሆነ፣ይህ ተስፋ በመጨረሻ የተፈጸመው የአብርሃም ዘር በሆነው በኢየሱስ ነው።ይህም የሚያስገነዝብን ምርጫ ተልእኮዊ እንጂ በአንድ ህዝብ ብቻ ይተገደበ አለመሆኑን ነው።

በክርስቶስ ፍጻሜ ያገኘው የተስፋው ዓለም አቀፍ ወሰን (ሮሜ እና ገላትያ)

ሀ. በእምነት መጽደቅ ሮሜ 4፡3፡ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጻድቅም ሆኖ ተቆጠረለት። መዳን ሁል ጊዜ በእምነት እንጂ ህግን በመጠበቅ የሚገኝ አይደለም።

ለ.እውነተኛ የአብርሃም ልጅነት በገላ 3፡7 እንደተገለጸው የአብርሃም አይነት እምነት ያላቸው የአብርሀም ልጆች ናቸው እንጂ በስጋ አይሁድ የሆኑት ሁሉ የአብርሀም ልጆች አይደሉም። የእግዚአብሔር ቤተሰብነት የሚገለጸው በመንፈሳዊ እውነት እንጂ በስጋ አይሁዳዊ በመሆን አይደለምና።

ሐ. ክርስቶስ እንደ ተስፋው ቃል ዘር ገላትያ 3፡16፡ ለአብርሀም የተነገርው የተስፋው ቃል ዘር የሚያመለክተው ክርስቶስ ኢየሱስን ነው። አብርሃም ሊጠብቀው የሚችለው ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ ፍጻሜ አግኝቷል። ኢየሱስ የዘፍጥረት 12 ፍጻሜ ነውና።

ትልቁ የሥነ-መለኮትሥዕል

ምርጫ፡ እግዚአብሔር አብራምን የቃል ኪዳኑ እቅድ መነሻ አድርጎ መረጠው።
የተስፋ ቃል፡- እግዚአብሔር ከአብራም ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ቃል ኪዳን አግርጎአል።
ቤዛነት፡ የእግዚአብሔር አላማ አለም አቀፋዊ ነው— በዘፍጥረት 3 ላይ የጠፋውን በረከት ወደ ነበረበት መመለስ።
ጸጋ፡- እግዚአብሔር ዓለምን መፈወስ ለመጀመር አንድ ፍጽምና የጎደለውን ሰው ይጠቀማል።

ማጠቃለያ

በዘፍ 12 እግዚአብሔር አብራምን መጥራቱ የሚያሳየው የድነት ታሪክ የሚጀምረው በእግዚአብሔር ቸር ምርጫ እና በተስፋዎቹ በኩል መሆኑን ነው።ለአብርሀም የተሰጠው የተስፋ ቃል ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ህዝቦች በረከትን እንደሚያመጣ ነው።ይህ የእግዚአብሔርን የማዳን እቅድ ያስተዋውቃል።በአዲስ ኪዳን ደግሞ የሮሜ መጸሐፍ ያ እቅድ እንዴት እንደሚሰራ ያብራራል። የገላትያ መጸሐፍ ደግሞ ያንን እቅድ የሚቀበለው ማን እንደሆነ ያርጋግጥል።በአጠቃላይ እግዚአብሔር በዘፍ 12:1-3 ለአብርሃም የሰጠው ተስፋ ፍጻሜውን ያገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ ነውና።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.