Home » የዘፍጥረት መጽሐፍ (Tuesday Sermons) » Tuesday – January 6, 2026

የዘፍጥረት መጽሐፍ ታሪካዊ ዳራ

Last updated on January 6, 2026 - by Pastor Tariku Eshetu

ዓላማ

Ø የዘፍጥረት መጸሐፍ ምን እንደሚያስተምር ማወቅ
Ø የዘፍጥረት መጸሐፍ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ማርጋግጥ
Ø የዘፍጥረት መጸሐፍ ለዚህ ዘመን ያለወን መልዕክት ማወቅ

1) የዘፍጥረት መጸሐፍ ርዕስ እና ትርጉም፦

የመጸሐፉ መጠሪያ ወይንም ርዕስ በዕብራይስጥ በረሺት ሲሆን ትርጉሙሙም “በመጀመሪያ” የሚል ነው። የግሪክ/የእንግሊዘኛ አቻ ትርጉሙ ደግሞ፡ “መነሻ፣” “ልደት” ወይም “መጀመሪያ” የሚል ነው።

የዘፍጥረት መጸሐፍ የመጀመሪያ ነግርሮችን ያብራል፡-
- የአጽናፈ ዓለምን ጅማሬ
- የሰብአዊነት ጅማሬ
- የኀጢአት ጅማሬ
- የህዝብ በምድር መበተን ጅማሬ
- በእግዚአብሔር ስለተመረጠው ሕዝብ (እስራኤል) ጅማሬ
- የእግዚአብሔርን ዓለምን የመቤዠት እቅድ (የቤዛዎተ እግዚአብሔርን ዕቅድ) ጅማሬ

2) የዘፍጥረት ጸሐፊ ማን ነው?

የተለመደው አመለካከት ማለትም (የአይሁድ እና የክርስትና እምነት) በጋር የሚቀበሉት ሙሴ የዘፍጥረት ጸሐፊ መሆኑ ነው። ለብዙ ሺህ ዓመታት የአይሁድ እምነትም ሆነ የክርስትና እምነት ሙሴ የዘፍጥረት መጸሐፍ ጸሐፊ መሆኑን ያምናሉ። ሙሴ ዘፍጥረትን ከዘጸአት፣ ከዘሌዋውያን፣ከዘኁልቅ እና ከዘዳግም ጋር እንደጻፈው ይታመናል። (ብዙውን ጊዜ ሕግ ወይም ኦሪት ተብሎ የሚጠራውን) ማለት ነው።

መጽሐፍ ቅዱሳዊው ማስረጃውም ብዙውን ጊዜ የሙሴን ጸሐፊነት አጻንኦት ይሰጣል።
1፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሙሴ የሕጉን አንዳንድ ክፍሎች እንደጻፈ ይናገራል "እግዚአብሔርም ሙሴን ይህን በመጽሐፍ ጻፍ አለው።" (ዘጸ 17:14) “ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ጻፈ። ( ዘጸ 24:4 )
2፡ኢየሱስና ሐዋርያቱ ሙሴን የሕጉ ጸሐፊ ብለው ይጠሩታል። ሙሴን ብታምኑት እኔን ባመናችሁ ነበር እርሱ ስለ እኔ ጽፎአልና። ( ዮሐ 5:46-47) "ሕጉ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር" ( ዮሐ 1:17)

3) ፔንታቱክ እንደ አንድ የተዋሃደ ሥራ ይቆጠራል።

ዘፍጥረት ከዘፀአት– ዘዳግም የቀጠለውን ታሪክ ያስተዋውቃል፣ስለዚህ ትውፊት ሙሴ ያዘጋጀው በእግዚአብሔር ተመስጦ/inspiration ነው ይላል። ትውፊታዊው አስተምህሮ እግዚአብሔር ለሙሴ ታሪክን እንደገለጠ እና ሙሴም በታማኝነት መዝግቦታል ብሎ ይቀበላል።

ዘመናዊው የምሁራን ሙግት ብዙ የዘመናችን የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ዘፍጥረት ከቀደምት የጽሑፍ እና የቃል ምንጮች የተጠናቀረ ሲሆን የስነጽሁፍ መልክና ቅርጽ የተሰጠው በመጨረሻው ሊሆን ይችላል ብለው ያምናሉ (አንዳንድ ጊዜ ዘጋቢ መላምት ይባላል ) ብለው ይከራከራሉ። ይህ ሙግታቸውም መሰረት የሚያደርገው፦
• ዘፍጥረት የተለያዩ የአጻጻፍ ስልቶች አሉት የሚል ነው።
• አንዳንድ ታሪኮች ከተለያዩ ልዩነቶች ጋር ተደጋግመው ይታያሉ (ለምሳሌ፡ የፍጥረት ትረካዎች)።
• ሙሴ ከመወለዱ ከረጅም ጊዜ በፊት የተከናወኑ ሁኔታዎች መኖራቸውን ይገልጻሉ።

ነገር ግን፣ ይህን ሃሳብ የሚቀበሉ ብዙ ሊቃውንትም እንኳ አሁንም ሙሴ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፣ መጽሐፉ በእግዚአብሔር አመራር ሥር የቆየ ነው እና እስራኤል አስተማማኝ ታሪካዊ ወጎችን ጠብቃለች ብለው ያምናሉ።

የጸሐፊውን ማንነት ለማሰብ ጠቃሚው መንገድ

የእምነት አመለካከት፡- ሙሴ እግዚአብሔር ለህዝቡ የፍጥረትን፣ የቃል ኪዳኑን እና የአጽናፈ ዓለሙን የጅማሬ ታሪክ ለህዝቡ ለመስጠት የተጠቀመበት በመንፈስ መሪነት የተጻፈ የእግዚአብሔር ቃል የሚል ነው።
ወሳኝ-ታሪካዊ እይታ፡- የዘፍጥረት መጸሐፍ ሲጻፍ እግዚአብሔር ቀደምት መዛግብትን፣ ታሪኮችን፣ ወይም የዘር ሐረግ ዝርዝሮችን ተጠቅሞ ሊሆን ይችላል፣ ሙሴ ወይም የኋላ የመጸሐፉ አዘጋጆች አሁን እኛ ያለንን መጽሐፍ አደራጅቷቸዋል ይላሉ። ሁለቱም አመለካከቶች ዘፍጥረት መሰረታዊ የቅዱሳት መጻሕፍት ትምህርት እንደሆነ ይስማማሉ፡-
• እግዚአብሔር ዓለምን ፈጠረ
• የሰው ልጅ በኃጢአት ወደቀ
• በአብርሃም ቤተሰብ በኩል የእግዚአብሔር የቤዛነት ተስፋ ተሰጠ።

ባጠቃላይ በትውፊት እንደሚታመነው ሙሴ ዘፍጥረትን የጻፈው በእግዚአብሔር ተመስጦ/God’s inspiration ነው ተብሎ ነው ። እንደ ዘመናዊዎች ምሑራን ድግሞ ሙሴ ቀደም ሲል የነበሩትን ምንጮች ተጠቅሞ ሳይሆን አይቀርም የጻፈው ይላሉ። ሆኖም ጽሑፉ ግን በጊዜ ሂደት ተቀርጾ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ክርስቲያኖች እና አይሁዶች ግን እግዚአብሔር እውነተኛው የዘፍጥረት ጸሀፊ ነው ብለው ስለሚያምኑ አካሄዱንና ሂደቱን የመራው እርሱ ነው ይላሉ።የተጻፈበትም ጊዜ ምናልባት የእስራኤል ህዝብ በምድረ በዳ በሚጓዝበት ወቅት 1400-1200 አካባቢ እንድሆነ ይታመናል።

3) ቀዳሚ ተደራሲዎች

ዘፍጥረት በዋነኝነት የተጻፈው ለእስራኤል ሕዝብ ነው። ይህም እግዚአብሔር ማን እንደሆነ እንዲረዱ፣ እነርሱ ከየት እንደመጡ በማወቅ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ተስፋዎች እንዲያምኑ እና በአረማውያን ሕዝቦች መካከል በእግዚአብሔር እንደ ተመረጠ ሕዝብ መኖር እንዳለባቸው ሊያስታውሳቸው የተጻፈ ነው። እንዲሁም ታሪካችሁ የጀመረው በእግዚአብሔር እንጂ በግብፅ ጣዖታት ወይም በሰው ነገሥታት አይደለም የሚል መልዕክትን ሊያስተላፍላችው የተጻፈ ነው።

4) የዘፍጥረት ዓላማ

1. እግዚአብሔርን ፈጣሪ አድርጎ መግለጥ ነው።
እግዚአብሔር በሥርዓት፣ በዓላማ እና በመልካም ፈጠረ (ዘፍ 1–2)።

2. የኃጢአትን እና የመከራን አመጣጥ ለማስረዳት
የሰውን ውድቀትና በዓለም ውስጥ ያለውን ስብራት ያብራራል (ዘፍ 3)።

3. የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት እና ባህሪ ለማሳየት
እግዚአብሔር ቅዱስ፣ ታማኝ፣ መሐሪ እና በታሪክ ሁሉ ላይ ሉዓላዊ ነው።

4. የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን እቅድ ለማስተዋወቅ
እግዚአብሔር ማዳንን በመጀመር ቃል ገብቷል፡-
አዳምና ሔዋን - የአዳኙን ተስፋ ተቀበሉ (ዘፍ 3:15)
ኖኅ - ሕይወትን የማዳን ኪዳን ተቀበል (ዘፍ 9)
አብርሃም - ለአሕዛብ ሁሉ በረከት የመሆንን ተሳፋ ተቀበል (ዘፍ 12: 1-3)

5. የእስራኤልን አመጣጥ ለማብራራት
የአብርሃምን ቤተሰብ ለቤዛነት ዓላማው እግዚአብሔር እንዴት እንደመረጠ ያሳያል።

6. እምነት እና ታዛዥነትን ለማስተማር
እንደ አብርሃም፣ ዮሴፍ እና ሌሎች በአምላክ የመታመንን አርአያ የሚሳሳዩ ታሪኮች ።

7. አንባቢዎችን ለቀሪው የቅዱሳት መጻሕፍት ንባብ ለማዘጋጀት
ዘፍጥረት የመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ-መለኮት መሠረት ነው።

5) አጽንዖት የተሰጠባች ዋና ዋና ጭብጦች

• እግዚአብሔር ፈጣሪ አምላክ ነው
• የሰው ክብር/ክቡርነት (በእግዚአብሔር መልክ ተፈጠረ)
• የሰው አመፅና ኃጢአት
• የእግዚአብሔር ፍርድ እና ምሕረት
• ቃል ኪዳን እና የተስፋ ቃል
• እግዚአብሔር በተሳሳቱ/በወደቁ ሰዎች በኩል ይሠራል የሚሉ ናቸው።

6) ስነ-ጽሁፍ ዘይቤ

ዘፍጥረት የትራኬን ስነ-ጽሑፋዊ ዘውግ የሚከተል ነው።ነገር ግን ጥልቅ ሥነ-መለኮታዊ ፋይዳ አለው።የዘፍጥረት መጸሐፍ እውነተኛ ሰዎችን እና ክስተቶችን የዘር ሐረግ (የቤተሰብ መስመሮችን) ጊዜን ምሳሌያዊ ቋንቋና የእግዚአብሔርን ተሳትፎ የሚያሳዩ በጥንቃቄ የተዋቀሩ ታሪኮችን በመዘገብ የሆነውን መናገር የሚናገር ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር በታሪክ ውስጥ የሚያደርገውን ስራውንም ያሳያል እንዲሁም የእግዚአብሔርን የታሪክ ባለቤትነትም ያረጋግጣል።

8) ቀላል የሆነ የዘፍጥረት መዋቅር

ምዕ. 1-11 - ዓለም
ፍጥረት • ውድቀት • ጎርፍ • ባቤል
ምዕ. 12–50 - የተስፋው ቤተሰብ
አብርሃም • ይስሐቅ • ያዕቆብ • ዮሴፍ

9) ቁልፍ ቃላት እና ሀሳቦች

"በረከት" - እግዚአብሔር ለፍጥረታቱ መልካም ነገር ይፈልጋል
"ዘር" - ስለወደ ፊቱ አዳኝ ይጠቁማል
“ቃል ኪዳን” - የእግዚአብሔር አስገዳጅ ተስፋን ያመለክታል

10) ታሪካዊ ዳራ ለምን አስፈለገ?

የዘፍጥረት መጸሐፍን ታሪካዊ ዳራውን መረዳታችን ዘፍጥረትን እንደ እግዚአብሔር የመሠረት ታሪክ እንድናነብ ይረዳናል። የዘፍጥረት መጸሐፍ ልብ ወለድ ወይም ተረት አይደለም ነገር ግን ሥነ-መለኮታዊ ታሪክ ነው። ስለዚህም እግዚአብሔርን፣ እራሳችንን፣ ኃጢአትን፣ እምነትን፣ እና ድነትን እንዴት ልናየውና ልንገነዘበው እንድሚገባ ይወስንልናል። እንዲሁም የቀረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለመረዳት ያዘጋጀናል።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.