አራተኛው ሳምንት፡ የኃጢአት መስፋፋት እና የጸጋው ቀጣይነት ዘፍጥረት 4-5
መግቢያ
ኃጢአት በሰው መውደቅ ላይ ብቻ አላቆመም። ዘፍጥረት 3 ኃጢአት ወደ ዓለም እንዴት እንደገባ ያሳየናል። ዘፍጥረት 4 እና 5 ደግሞ ተመሳሳይ የሆነ ጠቃሚ ነገር ያሳዩናል ኃጢአት ትንሽ አልነበረም ወይም ደግሞ በዘፍ 3 ላይ ተወስኖ አልቀረም ነገረ ግን ተስፋፍቷል። እነዚህ ምዕራፎች ኃይለኛ እውነትን ያሳያሉ እርሱም ኃጢአት ይበዛል ጸጋው ግን ከዚያ ይልቃል።
ሥነ-መለኮታዊ ጭብጦች፡ የኃጢአት መስፋፋት እና የጋራ ጸጋ (የጋራ ጸጋ ዓለም በኃጢአት ሥር እራሷን ስታ እንዳትወድቅ የሚከለክለው እና ሰዎች ሁሉ የእርሱን ቸርነት እንዲለማመዱ የሚያደርግ የእግዚአብሔር ለጋስ ቸርነት ነው።) የሚለው እውነት ነው። ኃጢአት ቢበዛም፣ እግዚአብሔር የማዳን እቅዱ የሚቀጥልበትን ታማኝ መስመር ይጠብቃል አያቋርጥም።
ዘፍ 4-5 ሁለት ወሳኝ ጥያቄዎችን ይመልሳል፡-እርሱም ከውድቀት በኋላ በሰው ልጅ ላይ ምን ይሆናል? ኃጢአት ሲበዛ እግዚአብሔር እቅዱን ይተዋል? የሚሉትን ነው። መልሱ ግልጽ ነው። ይህም እግዚአብሔር ታማኝ ሆኖ ይኖራል የሚልስ ነው። ይህንንም ቀጠለን እንመለክታልን።
I. የኃጢአት መስፋፋት በሰው ልጆች ታሪክ (ዘፍ 4)
1. የመጀመርያው የነፍስ ግድያ በቃየን እና በአቤል መካከል (ዘፍ. 4፡1–16)
ቃየንና አቤል ሁለቱም ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አመጡ። እግዚአብሔር የአቤልን መስዋዕት ተቀብሎ የቃየንን መስዋዕት ግን አልተቀበለም። ለምን? ምክንያቱን አቤል በእምነት ስላቀረበ ነው ብሎ የዕብራውያን ጸሐፊ ነግሮናል ዕብ 11:4።በዚህ ጊዜ ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ ተቆጣ። እግዚአብሔርም ቃየንን “ኃጢአት በደጅ እንዳደፈጥች”በማሳየት አስጠነቅቀው(4፡7)ቃየንም ንስሐ በመግባት ፈንታ በቅናት እና በንዴት ለእግዚአብሔር ምላሽ ሰጠ። ወንድሙንም ገድለው። ኃጢአት ንቁ እና አደገኛ ነው።ስልሆነም ሰዎች ለምርጫቸው ተጠያቂ ናቸው። ቃየን አቤልን ገደለው የመጀመሪያው የሰው ልጆች ግድያ ሆነ።ውጤቱም፡- ከእግዚአብሔር መለየት ፣የተበላሹ ግንኙነቶች መቀጠል፣ የስቃይ መጨመር ሆነ። ጸጋ ግን አልተጓደለም ነበር ስለዚህ እግዚአብሔር ቃየንን ከሞት ይጠብቀው ዘንድ ልክምት አደረገበት (4፡15) ።
2. በኀጢአት ምክንያት የመጣው የብልሹነት እድገት (The Growth of Corruption) (ዘፍ. 4፡17–24)
የቃየን ዘሮች ከተማዎችን ገነቡ እና የኀጢአትን ባህልን እሳደጉ። የሰዎች ስኬታማነት ጨመረ (ሙዚቃ፣ የማምረቻ፣ መሳሪያዎችና የእንስሳት እርባታ) ። የሥነ ምግባር ብልሹነት ጨመረ ላሜህ በግፍ ባለመታዘዝ ይመካል ኃጢአት የተለመደና የሚከበር ተግባር ሆነ።ይህ ሁኔታ ኃጢአት በማህበረሰብ እና በትውልድ ላይ እንዴት እንደሚስፋፋ ወይም እንደተስፋፋ ያሳያል።
II. በወደቀው ዓለም ውስጥ የእግዚአብሔር የጋራ ጸጋ
የጋራ ጸጋ(የጋራ ጸጋ ዓለም በኃጢአት ሥር እራሷን ስታ እንዳትወድቅ የሚከለክለው እና ሰዎች ሁሉ የእርሱን ቸርነት እንዲለማመዱ የሚያደርግ የእግዚአብሔር ለጋስ ቸርነት ነው።) የእግዚአብሔር ቸርነት ለሰው ሁሉ፣ ለኃጢአተኞችም ጭምር ተሰጥቶ ነበር። ማስረጃውም በዘፍጥረት 4 ለቃየን የተደረገለት ጥበቃ የሰው የባህል ዕድገት ዓመፀኛ ቢሆንም የሰውን ሕይወት ማቆየት ግን ተችሎ ነበር። እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ወዲያውኑ አላጠፋም።
III. የታማነው የድኅነት መስመር ስይበላሽ መጠበቅ (ዘፍ 4:25–5:32)
1. የሴቴ የዘር ሐርግ መስመር (ዘፍ. 4፡25–26) እግዚአብሔር አምላክ ለአዳምና ለሔዋን ሌላ ልጅ ሰጣቸው ስሙም ሴት ይባላል።የሴቴ የዘር ሐርግ መስመር ከቃየን የዘር ሐርግ መስመር ጋር ይቃረናል። “በዚያን ጊዜም በእዚአብሔር ስም መጠራት ተጀመር” (4፡26) ተብሎ የተነገርለት የዘር ሐርግ መስምር ነው።
2. በሴት የዘር ሀረግ ውስጥ የሕይወት ታሪክ አካሔድ (ዘፍ 5)
የሰው ልጅ የሕይወት ታሪክ አካሔድ ሕይወትን፣ በረከትን እና የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አጽንዖት ይሰጣል።በዚህ ታሪክ ውስጥ የምንሰማው አንድ ተደጋጋሚ ሐረግ አለ እርሱም “ሞተም” የሚለው → የኃጢአት ውጤት የሆነ ቃል ነው። ነገር ግን ህይወት በዚህ ታሪክ ውስጥ የእግዚአብሔር እቅድ አልቆመም። ሄኖክ ጎልቶ ደግሞ በዚህ ታሪክ ውስጥ ይታያል"ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም እግዚአብሔር ወስዶታልና።"(5:24) ሄኖክ የተለመደው ሞት አላጋጠመውም ወይም አልሰለጠነበትም ይህ ታሪክ በኖህ የሚቀጥለውን የእግዚአብሔርን ትልቅ የቤዛነት ተግባር በመጠቆም ያበቃል።
IV. ቁልፍ ነጥቦች
ከውድቀት በኋላ ኃጢአት በፍጥነት እና በጥልቀት ተስፋፍቶ ነበር። በዚህ ምክንያት የእግዚአብሔር ፍርድ የማይቀርና እውነት ነው፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ጸጋ ሙሉ ጥፋትን ይገድባል። እግዚአብሔር ሁል ጊዜ ታማኝ ሆኖ ሰዎችን ይጠብቃል። የሰው ውድቀት የእግዚአብሔርን የማዳን እቅድ አይሽረውም።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.