በእምነት ብቻ መጽደቅ
ኦሪት ዘፍጥረት 15
ጭብጥ፡ በእምነት መጽደቅ
ቁልፍ ቃል፡ ዘፍጥረት 15፡6
መግቢያ
አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ትክክል/ጻድቅ ሊሆን የሚችለው እንዴት ነው? በዚህ ጉዳይ ላይ ትውልድ ሁሉ ተመሳሳይ መንፈሳዊ ጥያቄ ይጠይቃል ኃጢአተኛ ሰው እንዴት በቅዱሱ አምላክ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል? ሃይማኖታዊ መመሪያዎችን በማክበር ነው? በመልካም ሥራ ነው? በመንፈሳዊ ጥረት ነው? እያለ ይወዛገባል። ቅዱስ ቃሉ ግን ግልጽ የሆነ ትምህርትን በዚህ ጉዳይ ከመጀመሪያ ጀምሮ እንደሚያስተምር እንመለክታልን ለዚህ ጥያቄ ዘፍጥረት 15 ቀደም ብሎ መልስ ይሰጣል። ይህም ከሕጉ በፊት የእግዚአብሔር ማዳን በእምነት ብቻ መሆኑን በግልጽ በማረጋገጥ። በእምነት ስለመጸድቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ተጠቅሶ የምንመለከተው በዚህ ክፍል ነው። "አብራምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት። ”ይለናል እንዴት ይህ እንደተከናወነ ቀጠልን እንመልክታልን
I. እግዚአብሔር አስቀድሞ ይናገራል (ዘፍጥረት 15፡1)
"ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ...ይህ ቃል እነደሚያሳየው እግዚአብሔር ግንኙነቱን ከአብራም ጋር በቃሉ በኩል ይጀምራል። አብራም እግዚአብሔርን ፈልጎ አላገኘውም ነገር ግን እግዚአብሔር እራሱን በቃሉ ገለጠለት እንጂ። እግዚአብሔር የአብራም ፍርሃት ላይ ትኩረት በማድርግ ቃሉን መናገር ይጀምራል "አትፍራ...እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፥ ዋጋህም ታላቅ ነው። ትክክለኛው እምነት የሚጀምረው በሰው ድፍረት ሳይሆን በእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው ።
የአዲስ ኪዳን ብርሃን
ሮሜ 10:17፡— እምነት የሚመጣው በእግዚአብሔር ቃል ከመስማት ነው።
ዕብ 1፡1-2 - እግዚአብሔር የሚናገረው ቁርጥ ያለ ነገር ነው።ስለዚህ እምነት ሁል ጊዜ የመገለጥ ምላሽ ነው።
II. እውነተኛ እምነት በሰው ድካም /አለመቻል ላይ ይገለጣል (ዘፍጥረት 15:2-3)
ከእግዚአብሔር ዘንድ በቃሉ በኩል ለምጣለት እንዲህ ለሚለው “አትፍር፣እኔ ለአንተ ጋሻ ነኝ፣ዋጋህም እጅግ ታላቅ” መገለጥ አብራም በቅንነት መለሰ፡-"አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ምን ተሰጠኛለህ?"እኔም ያለ ልጅ እሄዳለሁ......።ይህ ጥያቄው አመጽ አይደለም። በታማኝነት እምነት የመታገል ነው። አብራም አንድ አስፈላጊ ነገር ያውቃል ይህም የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያለ እግዚአብሔር ኃይል የማይቻል መሆኑን የሚያመለከት ነው።
የአዲስ ኪዳን ብርሃን
ሮሜ 4:19— አብርሃም የድካሙን እውነታ ተጋፈጠ።
2ኛ ቆሮንቶስ 12:9፡— የእግዚአብሔር ኃይል በሰው ድካም ይፈጸማል። እምነት እውነታውን አይክድም ነገር ግን በችርሩ መካከል ቆሞ በእግዚአብሔር ይታመናል።
III. እግዚአብሔር የገባውን ቃል አረጋግጧል (ዘፍጥረት 15፡4-5)
ለአብራም ጥያቄ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-“ይህ ሰው አይወርስህም…” እግዚአብሔርም አብራምን ወደ ውጭ ወሰደው፡-"ሰማዩን ተመልከት እና ከዋክብትን ቁጠር..." እግዚአብሔር የአብራምን የትኩረት አቅጣጫ ለወጠው ካለበት ከራሱ ሁኔታ → ወደ ሰማይ በዙሪያው ካለው አስቸጋሪ ከሁኔታዎች →ወደ እግዚአብሔር ወደገባለት ቃል ኪዳን።
የአዲስ ኪዳን ብርሃን
ሮሜ 4:18፡— አብርሃም በተስፋ አመነ።
ዕብ 11:12 - ዘሮች እንደ ከዋክብት የበዙ ናቸው። እምነት በሚታዩ ማስረጃዎች ላይ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ላይ ነውየሚመሰርተው።
IV. የወንጌል ልብ (ዘፍጥረት 15:6)
"አብራምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት።” ይህ ጥቅስ በእምነት መጽደቅን በብሉይ ኪዳን መጸሀፍ ውስጥ ያብራራል። አብራም በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታማኝነት ላይ መሰረት አድርጎ እግዚአብሔርን አመነ፣ እግዚአብሔርም ይህን እምነቱን ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት። ቆጠርለት የሚልው ቃል የሂሳብ ወይም የህጋዊነት ቃል ነው። አብራም በስራው ፍጹም አልነበርም በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛ ሆኖ በእምነት ቆመ። ስልዚህ ጻድቅ ተብሎ ግን ተጠርቷል ወይም ጻድቅ መሆኑ ተበስሮአል። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ እምነቱ ነበር።
የአዲስ ኪዳን ብርሃን
ሮሜ 4:3-5፡— እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን በእምነት ያጸድቃል።
ገላ 3:6—9፣ ከእምነት የሆኑት የአብርሃም ልጆች ናቸው።
ፊል 3:9፡— ጽድቅ በእምነት እንጂ በሕግ አይደለም። መጽደቅ የእግዚአብሔር ፍርድ ውጤት እንጂ የእኛ ስኬት/ጥርት ውጤት አይደለም።
V. በእምነት የመጽደቅ ዋስትና በእግዚአብሔር ጸጋ ላይ የተመሰረተ ነው (ዘፍ 15፡7-8)
ምንም እንኳን ለረጅም ዘመን ቢጠብቅም በገባለት ቃል ኪዳን መሰርትእግዚአብሔር አብራምን አስቦታል፡ እግዚአብሔር የገባለትን ቃል ኪዳን በተመለከተ አብራም እንዲህ ሲል ይጠይቃል"እንዴት ማወቅ እችላለሁ?" ይህ ጥርጣሬ አይደለም ነገር ግን የእምነትን እርገጠኝነት መፈለግ ነው። እግዚአብሔርም የሰጠው መልስ ከዑር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ የለፈውን እውነት ያስታውሰዋል ። ምክንያቱ የእምነት ዋስትና የሚገነባው ባለፈው ጸጋ ላይ ነው።
የአዲስ ኪዳን ብርሃን
1 ዮሐ 5:13—የዘላለም ሕይወት እንዳለን ማወቅ እንችላለን።
ዕብ 6:11— ሙሉ የተስፋ ማረጋገጫ። እግዚአብሔር አብራምን አልገሠጸውም። ይልቁንም ያበረታታዋል እንጂ።
VI. የጸጋ ቃል ኪዳን (ዘፍ 15፡9–17)
እግዚአብሔር ከአብራም ጋር ለተጋባው የቃል ኪዳን ሥነ ሥርዓት እንስሳት ተሰውተዋል። በተለምዶ በእንዲህ አይነቱ ቃል ኪዳን ውስጥ ሁለቱም ወገኖች በቃል ኪዳኑ ወቅት በመሰዋዕቱ መካከል ያልፋሉ።ነገር ግን አብራም ግን ከባድ እንቅልፍ ወሰደው። በቁራዎቹ መካከል ያለፈው እግዚአብሔር ብቻ ነው።ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል"ይህ ቃል ኪዳን ካፈረሰ እርግማኑን እሸከማለሁ" የሚል ነው።
የአዲስ ኪዳን ብርሃን
ዕብ 6፡13-18 - እግዚአብሔር በራሱ ይምላል።
ገላ 3:13፡— ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆነ።
2ኛ ቆሮ 5:21 - ክርስቶስ ኃጢአታችንን ተሸከመ። መዳን የሚገኘው በእኛ ሳይሆን በእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ ነው።
VII. የማይሻሩ ተስፋዎች (ዘፍጥረት 15:18–21)
እግዚአብሔር ቃል ኪዳኑን በትክክል ያጸናል።ምክንያቱም ተስፋው የተረጋገጠ አስተማማኝ በማየዋሸው እግዚአብሔር የተረጋገጠ ነው።
የአዲስ ኪዳን ብርሃን
ሮሜ 11፡29 - የእግዚአብሔር ስጦታዎች(ጸጋውና ጥሪው) የማይሻሩ ናቸው።
ዕብ 10:23 - እግዚአብሔር ለገባው ቃል ታማኝ ነው።
መደምደሚያ
በዘፍጥረት መጸሐፍ መሠረት ወንጌል በተመለከተ ዘፍጥረት 15 እንዲህ በማለት ያስተምረናል።መዳን ሁል ጊዜ በእምነት ነው። ጽድቅ የተቆጠር እንጂ በሰው ጥረት የተገኘ አይደለም። እግዚአብሔር ብቻ መዳንን ይጠብቃል (አስተማማኘ ይሆናል) ። አብርሃምን በእምነት ያጸደቀው ያው አምላክ ዛሬም ኃጢአተኞችን በእምነት ያጸድቃል። የመጨረሻ የወንጌል መገለጫ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን በጸጋ ብቻ፣ በእምነት ብቻ፣ በክርስቶስ ብቻ ያድናል የሚል ነው። በዚህ መሰረት ዘፍጥርት 15 ጌታን እመኑ—እናም ጻድቅ ያደርግላችኋል የሚለው እውነት ከመጀመሪያ ጀምሮ በአድህኖት እግዚአብሔር እቅድ ውስጥ የማይለውጥ መርህ መሆኑን ያረጋግጥልናል።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.