Home » Sunday sermon – June 29, 2025

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ መኖር

Last updated on June 29, 2025 - by Pastor Tariku Eshetu

ትምህርት አንድ፦ የእግዚአብሔር መንግሥት ፍቺ/ትርጉም

አላማ

- አማኞች የእግዚአብሔርን መንግስት ትርጉም በቃሉ መሰረት ማስገንዘብ።
- የእግዚአብሔርን መንግስት አሁናዊ እውነታ በቃሉ መሰረት ማስገንዘብ።
- ወደእግዚአብሔር መንግስት የመግባትን አስፈላጊነትና የመንግስቱን የወድፊት ተስፋ በቃሉ ማመላክት።

መግቢያ

አማኞች ውጤታማ መንፈሳዊ ህይወት በምድር ላይ ሊኖሩ የሚችሉት የእግዚአብሔርን መንግስት በቃሉ መሰረት መረዳት ከቻሉ ብቻ ነው።ምክንያቱም የእግዚአብሔር ዘለአለማዊ እቅድ ሰውን ወደ መንግስቱ መመለስ ነውና። ቅዱሳት መጻህፍት ደግሞ የእግዚአብሔርን ሉዓላዊ አገዛዝ፣ አሁን ያለውን መንፈሳዊ ተፈጥሮ እና የወደፊት ፍጻሜውን በማጉላት ስለ እግዚአብሔር መንግሥት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ፍቺ ይሰጣሉ።ይህን እውነት በዚህ ትምህርት እንመለከታለን።

1. የእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ መገለጫዎች መዝ 103: 1ኛ ዜና 29፡11-1219

1:1 እግዚአብሔር ዙፋኑ በሰማይ የጸና ነው።
1:2 መንግሥቱም ሁሉን ትገዛለች።
1:3 ታላቅነትና ኃይል የእርሱ ብቻ ነው።
1:4 የመንግሥቱ ባለቤት እርሱ ብቻ ነው።

2. የመንግሥቱ አሁናዊ እውነታ ።ሉቃ 17፡20-21 ሮሜ 14፡17

2:1 የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም
2:2 የእግዚአብሔርመንግሥት በመካከላችን ናት።
2:3 የእግዚአብሔር መንግሥት የመብልና የመጠጣት ጉዳይ አይደለም።
2:4 የእግዚአብሔር መንግስት ጽድቅና ሰላም በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ደስታ ናት።

3.ወደ መንግሥቱ ለመግባት ። ዮሐንስ 3፡3ማቴዎስ 7፡21

3:1 ዳግመኛ መወለድ።
3:2 የአብን ፈቃድ ማድረግ።

4. መንግሥቱ እንደ የወደፊት ተስፋ ዳንኤል 2:44

4:1 የማትፈርስ መንግስት ናት።
4:2 ለሌላ ህዝብ የማትሰጥ ናት።
4:3 ሌሎች መንግስታትን ሁሉ ታጠፋለች።
4:4 ብቻዋን ለዘላለም ትቆማለች።

ማጠቃለያ

መጸሀፍ ቅዱስ እንደሚያስተምር እግዚአብሔር ሰውን በመጀመሪያ ሲፈጥረው ለመንግስት እንደፈጠረው እንመልከታለን። ሰው በኀጢአት ምክንያትም ካጣው ነገሮች መካከል አንዱ የእግዚአብሔር መንግስት ነው። ኢየሱስ ክርስቶሰም ሰውን የተቤዠው ወደ እግዚአብሄር መንግስት ሊያፈልሰው ነው። ስለዚ አማኝ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ትርጉም በቃሉ መሰርት ማውቅ አለብት ይህም የእግዚአብሔር ሉዓላዊ አገዛዝ መገለጫዎች፤የመንግሥቱ አሁናዊ እውነታ፤ወደ መንግሥቱ ለመግባት፤መንግሥቱ እንደ የወደፊት ተስፋ ማወቅ ማለት ነው።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.