Home » Sunday sermon – August 11, 2024

የእግዚአብሔር ወንጌልና አስከትሎቱ

Last updated on August 11, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

ዓላማ:-

- በእግዚአብሔር ወንጌል የማመን አስፈላጊነትን ማመላከት።
- በእግዚአብሔር ወንጌል ካመንን በህይወታችን ውስጥ የማይቀሩ ሶስት ነገሮችን ማመላከት።
- በእግዚአብሔር ወንጌል ማመን የማነት መለወጥ እንጂ የቤተ እምነት ለውጥ አለማድርግ መሆኑን ማሳሰብ።

መግቢያ:-

የእግዚአብሔር ወንጌል የእግዚአብሔር ፅድቅ የተግለጠበት ብቸኛ መንገድ ነው። ይህም ወንጌል ስለ ልጁ ብቻ ነው። ስለዚህ አንድ ሰው በወንጌል ሲያምን በኃጢአተኛነት ምትክ ፃድቅ ይሆናል።ስለዚህም የሚከተሉት እውነቶች በህይወቱ የማይቀሩ ክስተቶች ናቸው።እንዚህ ክስተቶች በእግዚአብሔር ወንጌል የመዳን ምልክቶች ናቸው።

1: የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆን።

1:1 በሌሎች የሚመሰከርለት የእምነት ኑሮ በመመኖር።
1:2 በልጁ ወንጌል እግዚአብሔር በማገልግል።
1:3 የእግዚአብሔርን ፈቃድ በመኖር
1:4 የፀሎት ሰው በመሆን።
1:5 አማኞችን የሚወድና የሚያስብላቸው በመሆን።
1:6 በአማኞች የሚገለገል አማኝ በመሆን።

2:የወንጌል ባለእዳ የሆነ አማኝ መሆን ያስከትላል

2:1 በወንጌል ፍሬ ማፍራትን ያስባል
2:2 ወንጌል ላልሰሙ ሁሉ ሀላፊነት ይወስዳል
2:3 ወንጌልን ለመስበክ ይዘጋጃል

3: በወንጌል አያፍርም! ለምን?

3:1 ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር የመዳን ኃይል የተገለጠበት ነውና።
3:2 የእግዚአብሔር ፅድቅ በእምነት የሚገለጥበት ብቸኛ መንገድ ነውና።

ማጠቃለያ:-

የእግዚአብሔር ወንጌል ስለ ልጁ ብቻ ነው። ስለዚህ በልጁ የሚያምን ሁሉ ይፀድቃል። የፀደቀ ሁሉ በወንጌል
ባገኘው ፅድቅ ምክንያት የእግዚአብሔር አገልጋይ ይሆናል ። በመሆኑም ዘውትር ስለ ወንጌል በፀሎት እና በእምነት የህይወት ስርዓት በመኖር የወንጌልን እዳ ወንጌልን ለሰው ሁሉ በመናገር እየክፈለ ይኖራል። በወንጌል ያመነ ከዚህ ውጪ ሊኖር አይችልም ።

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.