ንባብ:- 1:18-32
ዓላማ
- የእግዚአብሔር ፅድቅ በወንጌል አማካይነት የተገለጠበትን ምክንያት ማመልከት ።
- ሰው ሁሉ በአንድ መንገድ ብቻ እንደሚፀድቅ ማረጋገጥ።
- ፅድቅ የእግዚአብሔር ስጦታ እንደሆነ ማረጋገጥ።
መግቢያ
በቀደመው ትምህርት እንዳየነው ወንጌል አንድ ብቻ ነዉ ።ይህም ወንጌል የእግዚአብሔር ፅድቅ የተገለጠበት ወንጌል ነዉ። የእግዚአብሔር ፅድቅ የተገለጠበት ወንጌል የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው እንደሆነ እና ይህን ወንጌል በእምነት መቀበል አስከትሎት እንዳለው በቃሉ አይተናል ። በዛሬው ትምህርት ደግሞ የእግዚአብሔር ቁጣና ዓመፀኞች ያላቸውን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ፅድቅ መገጥ አንፃር እንመልከት ።
1: የእግዚአብሔር ፅድቅና የአመፀኞች የአሁን ሁኔታ
1:1 ከሰማይ በተገለጠው የእግዚአብሔር ቁጣ ስር ናቸው።
1:2. ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮዎች ሆነዋል።
1:3 እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።
1:4 የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ ታልፈው ተሰጥተዋል።
2: ዓመፀኞች ለምን በዚህ ሁኔታ ተገኙ?
2:1 እውነትን በአመፅ ስለከለከሉ
2:2 እግዚአብሔርን በልኩ ስላላከበሩት።
2:3 እግዚአብሔርን በልኩ ስላላመሰገኑት።
2:4 የእግዚአብሔርን ክብር በሚጠፋ ፍጡር ስለለወጡ።
2:5 እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ።
3: የዓመፀኞች መጨረሻ ሞት ነዉ ።
3:1 መንፈሳዊ ሞት
3:2 አካላዊ ሞት
3:3 የዘላለም እሳት ባህር ቅጣት።
ማጠቃለያ
መፀሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምርው ኃጢአት ሁሉ ዓመፅ ነው ዓመፅም ሁሉ ኃጢአት ነው። እንዲሁም ሁሉ ኃጢአትን
ሰርተዋል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል ስለሚል ሁሉ አመፀኞች ናቸው። ስለዚህ ሁሉም ከእግዚአብሔር ቁጣ ስር የሚድኑበትም መንገድ የላቸውም ። ስለዚህ ከዚህ ቁጣ እንዲድኑ በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ
ያስፈልጋቸዋል ።ይህንንም በልጁ ሲያምኑ ያገኙታልና በልጁ ሊያምኑ ይግባል ምክንያቱም በርሱ በሚያምን አይፈረድበትምና።
Source: https://cmaeec.com/w...
John 3:16
Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.