Home » Sunday sermon – July 28, 2024በወንጌል የተገለጠውን ጽድቅ እንቀበል!!!
Last updated on July 28, 2024 - by Pastor Tariku Eshetuየንባብ ክፍል:- ሮሜ 1:1-7
ዓላማ:- ለሰወች የእግዚአብሔር ጽድቅ የሚገኝበትን ብቸኛ መንግድ መጠቆም።
የእግዚአብሔር ጽድቅ የተገለጠብትን ወንጌል ማረጋገጥ።
የእግዚአብሔር ጽድቅ የሚገኘው በወንጌል በማመን ብቻ መሆኑን በቃሉ ማረጋገጥ።
መግቢያ
መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚያረጋግጠው ሰወች ሁሉ ኃጢአተኞች ናቸው።በዚህ ምክንያት ደግሞ የዘላለም ፍርድ እዳ አለባቸው። እርሱም ሞት ነው። ከዚህ ነጻ ልመሆን የሚችሉት ደግሞ ጻድቅ ሆነው ከተገኙ ብቻ ነው። ስለዚህ ሰወች ለመጽደቅ እንዲችሉ በወንጌል የተገለጠውን የእግዚአብሔር ፅድቅ ያስፈልጋቸዋል።ይህን በተመለከተ የቃሉን እውነት እንማራለን።
1: የእግዚአብሔር ጽድቅ የሚገኝበት ወንጌል
1:1 ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው።
1:2 የሐዋርያት ስብከትና አገለገሉት ነው
1:3 የብሉይ ኪዳን ነቢያትና መፀሐፍት የመሰከሩለት ነው።
1:4 በስጋ ከዳዊት ዘር የተወለደው ክርስቶስ ነው።
1:5 እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን የተነሳው ክርስቶስ ነው
1:6 በሀይል የእግዚአብሔር ልጅ. መሆኑ የተገለጠው ክርስቶስ ነው።
2: ወንጌሉ በጳውሎስ ህይወት የክሰተው እውነት
2:1 ሐዋርያዊ ጥሪን ፀጋን ሰጥቶታል።
2:2 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ አድርጎታል።(ባሪያ አገልጋይ)
2:3 የወንጌል ሰባኪ(መልክተኛ) አድርጎታል።
3: ወንጌል እና የሮም ክርስትያኖች
3:1 ከእምነት የሚነሳ መታዘዝ ውስጥ ከቶአቸዋል።
3:2 የክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ አድርጎቸዋል።
3:3 የእግዚአብሔርን ፍቅር አካፍሎአቸዋል
3:4 የቅድስና ጥሪን እንዲቀበሉ አድርጎል።
ማጠቃለያ:
የእግዚአብሔር ጽድቅ የሚገኝበት ወንጌል ባለቤቱ እግዚአብሔር ነው። ከዚህ ወንጌል ውጪ የእግዚአብሔር ጽድቅ የሚገኝበት መንገድ የለም። ይህን ወንጌል መቀበል የሚቻለው ደግሞ በእምነት ብቻ ነው። በእምነት ወንጌልን የተቀበለ ሁሉ የክርስቶስ ብቻ ይሆናሉ:: እንዲሁም ቅድስና የተጠሩለት ኑሮአቸው ይሆናል።አንዲህ በተቆጠረላቸው ፅድቅ ምክንያት ከእምነት በሚነሳ መታዘዝ በቅዱስ ኑሮ የሚጠብቁት ጌታ ሲመጣ በትንሳኤ ሙታን ይከብራሉ። ስለዚህ በወንጌል የተገለጠውን ፅድቅ እንቀበል።
Source: https://cmaeec.com/s...