Home » Sunday sermon – Oct 20, 2024

ፀጋ እንዲበዛ በኃጢአት ፀንተን እኑርን?

Last updated on October 20, 2024 - by Pastor Tariku Eshetu

የንባብ ክፍል ሮሜ. 6:1—11

ዓላማ

- ፀጋ ምን ማለት እንደሆነ በቃሉ መሰረት መረዳት
- በፀጋ መዳን በኃጢአት ፀንተን የመኖር ፈቃድ ማግኘት አለመሆኑን በቃሉ ማረጋገጥ።
- በፀጋ የዱኑ ሁሉ በኃጢአት ፀንተው የማይኖሩበትን ምክንያት በቃሉ ማረጋገጥ

መግቢያ

በቀደመው ትምህርት በአዳም ምክንያት ከሆነብን ይልቅ በክርስቶስ የተደርግልን እንደሚበልጥ አይተናል።
ደግሞም ኃጢአት በበዛበት ፀጋ አብልጦ የተትረፈረፈ መሆኑን በቃሉ መስፈርት አይተናል።በዛሬው ትምህርት
ደግሞ የስነ-ምግባርን ህግ በቃወም ክርስቲያን በክርስቶስ ባገኘው የእግዚአብሔር ፀጋ ምክንያት በኃጢአት ፀንቶ መኖር የለበትም የሚለውን በቃሉ መሰረት እንመለክታለን።

1: ፀጋና ኃጢአት ያላቸው ግንኙነት ምንድን ነው?

1:1 የኃጢአት ምንነት እና ውጤቱ

1:1:1 ኃጢአት ዓመፅ ነው ዓመፅም ኃጢአት ነው።1ዮሐ 3:4, 5:17
1:1:2. ኃጢአት በኢየሱስ ክርስቶስ አለማመን ነው። ዮሐ 16:9
1:1:3 የኃጢአት ውጤት ሞት ነው። ኤፌ 2:1-3,ዘፍ 4:8,ራዕይ 21:8።

1:2 የፀጋ ምንነትና ውጤቱ

1:2:1 ፀጋ ከእግዚአብሔር እንዲያው የተቸረን በጎነትና መልካምነትና የእግዚአብሔር ደግነት መግለጫ ነው።
ት.ሚል 1:9 ዮሐ 1:14-17
1:2:1 የፀጋ ውጤት ድህነት ፣ከኃጢአት ባርነት ነፃ መውጣት….ወዘተ ናቸው። ኤፌ 2:10,2ጢሞ 1:9 ሮሜ
6:14።

2: በኃጢአት ፀንተን መኖር የማንችልበት ምክንያቶች:-

2:1 ለኃጢአት ስለሞትን/ስለማንችል። ሮሜ6:1-2
2:2 ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ጋር ስለተባበርን።ሮሜ 6:3-5
2:3 አሮጌው ሰዎችን ከክርስቶስ ጋር ስለተሰቀለ። ሮሜ 6:6
2:4 ከክርስቶስ ጋር እንደ ሞትን ስለምናምንና ስለምናውቅ ሮሜ 6:7-9
2:5 በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ህያዋን እንደሆን ራሳችንን ስለምንቆጥር። ሮሜ 6:10-11

ማጠቃለያ

በፀጋ መዳን በኃጢአት የመኖር ፈቃድ ማግኘት ሳይሆን ከክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ጋር መተባበር ነው። እንዲሁም አሮጌውን ሰው ከክርስቶስ ጋር በመስቀል አዲስ ህይወትን ለእግዚአብሔር መኖር ነው። ስለዚህ ፀጋ እንዲበዛ በኃጢአት መኖር ሳይሆን በዝቶ በተትረፈረፈው ፀጋ ለእግዚአብሔር አዲስ ህይወትን መኖር ነው የቃሉ ትምህርት። እኛስ ዛሬ በፀጋ እየኖርን ነው ወይስ በኃጢአት??

Source: https://cmaeec.com/w...

the cross
Jesus is Lord
John 3:16

Whoever believes in him shall not perish but have eternal life.